Get Mystery Box with random crypto!

ዓለምአቀፉ የማዕድን ኤክስፖ በሚሊንየም አዳራሽ ተከፈተ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ህዳር 3 ቀን 20 | ሰሌዳ | Seleda

ዓለምአቀፉ የማዕድን ኤክስፖ በሚሊንየም አዳራሽ ተከፈተ፡፡

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ኤክስፖ  ከ270 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ:: የማዕድን ኩባንያዎች፣ የጌጣጌጥ አምራቾችና ላኪዎች፣ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾችና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት የኤክስፖው አካል ናቸው::

ኤክስፖው አምራቾችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ገዢዎች ጋር በቀጥታ ያገናኛል ነው የተባለው:: እንዲሁም  ከውጪ የሚመጡ የማዕድን ኩባንያዎች በኤክስፖው ላይ መሳተፋቸው በኢትዮጵያ  ያለውን የማዕድን ኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲመለከቱና የማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

በዚህ ኤክስፖ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾች መሳተፋቸው ደግሞ  ለኢትዮጵያ  የማዕድን ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን የመተዋወቅ እድል ይፈጥራል መባሉት ከማዕድን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡