Get Mystery Box with random crypto!

ከሕዳር 15 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር ተገለጸ | ሰሌዳ | Seleda

ከሕዳር 15 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር ተገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በሳምንቱ በተከናወኑ ዲፕሎማሲያዊ ኹነቶች ላይ ትላንት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከሕዳር 15/2015 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት ጋር የኤሌትሪክ ኃይል ለመሸጥ ስምምነት ማድረጓ የሚታወቅ ሲሆን፤ ወደ ኬንያ የሚላከው የኤሌትሪክ ኃይልም በተደረገው ስምምነት መሰረት መሆኑን አምባሳደሩ በማብራሪያቸው መናገራቸውን ዋልታ ዘግቧል።

የኢትዮ- ኬንያ የሀይል ማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ስቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ በ2008 የተጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ እስከ 2000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡