Get Mystery Box with random crypto!

የማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ምዘናና የምርምር ላቦራቶሪ ለመገንባት ከኤስ ጂ ኤስ ግሩፕ ጋር ተፈራረ | ሰሌዳ | Seleda

የማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ምዘናና የምርምር ላቦራቶሪ ለመገንባት ከኤስ ጂ ኤስ ግሩፕ ጋር ተፈራረመ።

ላቦራቶሪው በ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ማዕከሉ የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ችግርን የሚፈታና የሀገራችን የማዕድን ጥራትን በማሳደግ በዓለም የማዕድን ገበያ ተፎካካሪነትን የሚጨምር ነው ተብሏል።

የማዕድን ሚኒስቴር ትናንት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ በተከፈተው በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እያካሄደው ባለው ኤክስፖ ከ270 በላይ ኩባንያዎች እየተሳተፉ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ዛሬ ኤክስፖውን ጎብኝተዋል።