Get Mystery Box with random crypto!

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆነ። የእን | ሰሌዳ | Seleda

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆነ።

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ  የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በተገኙበት ይፋ ሆኗል:: መማሪያው በትምህርት ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን ከተማሪዎችና መምህራን በተጨማሪ ሁሉም የማህበረሰብ አካል ሊጠቀምበት እንደሚችል ተጠቁሟል::

የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በበኩላቸው ትውልድን የመገንባት ሃላፊነት የጋራ በመሆኑ መማሪያው ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋችን ማህበራዊ ሃላፊነታችንን የምንወጣበት አንዱ ማሳያ ነው  ያሉ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉትን የለውጥ ስራዎች ኢትዮ ቴሌኮም እንደሚደግፍ ተናግረዋል።