Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 145

2022-11-10 13:17:46
የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሰሩ መፈቀዱ የፋይናንስ ተወዳዳሪነትን በማነቃቃት የዘርፉን ተደራሽነት ይጨምራል - ኤርሚያስ አመልጋ

በኢትዮጵያ እስከ 1970ዎቹ ድረስ የጣሊያንና የህንድን ጨምሮ የሌሎች አገራት ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በአገር ውስጥ ይንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም በወቅቱ ኢትዮጵያ ትከተለው በነበረው ርዕዮተ ዓለም ምክንያት የውጭ አገራት ዜጎች ባንኮቻቸውን ዘግተው ወደ አገራቸው ለመመለስ ተገደዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ አካላት ዝግ እንደሆነ ቆይቷል።

የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያው ኤርሚያስ አመልጋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ለውጭ ባንኮች ዝግ ሆኖ መቆየቱ የፋይናንስ ስርዓቱ እና የምንዛሬ ግብይቱ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን አንስተዋል።
በአሁኑ ወቅት የውጭ አገራት ባንኮች በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የተከፈተው እድልም እንደ አዲስ ሊታይ እንደማይገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ዘግይታም ቢሆን ወደነበረችበት የፋይናንስ አሳታፊ ስርዓት መመለሷ በቴክኖሎጂ፣ በዓለም አቀፍ ንግድና በፋይናንስ መሰረተ ልማት ዕድገት ላይ ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ከስራ ዕድል ባለፈ የተሻለ የፋይናንስ ተወዳዳሪነትን ይፈጥራል ብለዋል።

via - ENA
5.3K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 11:07:25
ከአራት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ከአራት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት ጀምሯል። የመታውቂያ ዕድሳት አገልግሎት አሰጣጡ ለሕግ ወጥ ድርጊት ተጋልጦ የነበረ በመሆኑ እና የተለያዩ የሰላምና ፀጥታ ስጋት ጭምር በመፍጠሩ አገልግሎቱ መቋረጡ ይታወሳል።

አገልገሎቱ ተድቅኖበት የነበረውን ችግር በማረም እና በማስተካከል ዳግም የመታውቂያ እድሳት በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።
5.5K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 10:32:21
ዓለምአቀፉ የማዕድን ኤክስፖ በሚሊንየም አዳራሽ ተከፈተ፡፡

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ኤክስፖ  ከ270 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ:: የማዕድን ኩባንያዎች፣ የጌጣጌጥ አምራቾችና ላኪዎች፣ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾችና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት የኤክስፖው አካል ናቸው::

ኤክስፖው አምራቾችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ገዢዎች ጋር በቀጥታ ያገናኛል ነው የተባለው:: እንዲሁም  ከውጪ የሚመጡ የማዕድን ኩባንያዎች በኤክስፖው ላይ መሳተፋቸው በኢትዮጵያ  ያለውን የማዕድን ኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲመለከቱና የማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

በዚህ ኤክስፖ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾች መሳተፋቸው ደግሞ  ለኢትዮጵያ  የማዕድን ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን የመተዋወቅ እድል ይፈጥራል መባሉት ከማዕድን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
5.7K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 09:35:05
ከሕዳር 15 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር ተገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በሳምንቱ በተከናወኑ ዲፕሎማሲያዊ ኹነቶች ላይ ትላንት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከሕዳር 15/2015 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት ጋር የኤሌትሪክ ኃይል ለመሸጥ ስምምነት ማድረጓ የሚታወቅ ሲሆን፤ ወደ ኬንያ የሚላከው የኤሌትሪክ ኃይልም በተደረገው ስምምነት መሰረት መሆኑን አምባሳደሩ በማብራሪያቸው መናገራቸውን ዋልታ ዘግቧል።

የኢትዮ- ኬንያ የሀይል ማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ስቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ በ2008 የተጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ እስከ 2000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
5.7K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 18:59:21
የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ 11 ሺ ሰራተኞቹን አሰናበተ።

ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ሜታ ከጠቅላላ ሰራተኞቹ 13 በመቶውን ቀንሷል። ከ87 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ኩባንያው የጠበቅኩት እድገት ባለመሳካቱ ነው እርምጃውን የወሰድኩት ብሏል። እንደ ቲክቶክ ያሉ አጫጭር ምስሎችን ማጋሪያ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለግዙፉ ትስስር ገፅ ክስረት መነሻ መሆናቸው ተነግሯል። 

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ "በገጠመን ከባድ ችግር ምክንያት ለቀነስናችሁ ሰራተኞቻችን ይቅርታ እጠይቃለሁ" የሚል መግለጫ አውጥቷል። ትዊተርም መሰል ችግር ገጥሞት ከሰሞኑ ከ3 ሺ በላይ ሰራተኞቹን መቀነሱ ይታወሳል።

via - Alain
7.0K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 17:03:24
ቤቶች ኮርፖሬሽን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኪራይ ቤቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ ጥናት ማድረጉን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለ ብርሃን ዜና፣ በተያዘው ዓመት ዕቅዱን ለማሳካት የምክር ቤቱን ዕገዛ እንደሚፈልግ መናገራቸውን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የማስተካከያ ጭማሪ ባለመደረጉ፣ በቀጣይ በሚካሄደው ጥናት ላይ ከቤት ባለቤቶችና ከሚመለከታው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት በኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ቦርድ ፀድቆ እንደሚተገበር ተነግሯል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በባለቤትነት ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ውስጥ የመንግሥት ተቋማትና ኃላፊዎች ኪራይ ሳይከፍሉ እየተጠቀሙባቸው ስላሉ፣ ምክር ቤቱ ዕገዛ እንዲያደርግና የገንዘብ ሚኒስቴር በጀት ይዞላቸው ተቋማቱ ኪራይ እንዲከፍሉ እንዲደረግም ተጠይቋል፡፡
7.1K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 15:46:06
አልሳም ግሩፕ ‹‹አልሳም መንደር›› የተሰኘ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረ

አልሳም ግሩፕ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት መንግሥት ባስቀመጠው የመንግሥትና የግል ትበብር መርህ መሠረት ለማሟላት በከተማዋ ‹‹አልሳም መንደር›› በሚል መጠሪያ የሪል ስቴት ልማት ለማከናወን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። 

‹‹አልሳም መንደር›› በሚል መጠሪያ የሚገነባው የሪል ስቴት ልማት ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ሕንፃ ጀርባ በሚገኝ 1460 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ እንደሆነ የተናገሩት የአልሳም ግሩፕ ተወካይ አቶ ካሚል ሳቢር፣ ይዞታውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ በሊዝ መረከባቸውንና በዚህ ይዞታ ላይም 200 መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩት ባለ 30 ወለል ከፍታ ሕንፃ እንደሚገነባ አስታውቀዋል።

በአልሳም ግሩፕ ሥር በሚገኙ ሁለት እህትማማች ኩባንያዎች በ2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሁለት የመኖሪያ ሕንፃዎችን (አፓርትመንቶች) ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመረቁ ሲሆን፣ ከንቲባዋ የአልሳም መንደር የሪል ስቴት ግንባታ ለማስጀመርም የመሠረት ድንጋይ ማይኖራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
6.9K views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:01:45
የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ሀብት ቆጠራና የዋጋ ትመና ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ መሠረተ ልማት ብዛትና ወቅታዊ ዋጋ በተመለከተ ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ቆጠራው የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ምን ያህል ምሰሶዎች እንዳሉት፣ የት እንደሚገኙ፣ ከምሰሶዎች አቅራቢያ ምን ያህል ቤቶች እንደሚኖሩ፣ በአንድ ምሰሶ ምን ያህል ሰዎች እንደሚጠቀሙ፣ የተበላሹ ቆጣሪዎች ምን ያህል እንደሆኑ፣ ትራንስፎርመሮች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ፣ ማርጀት አለማርጀታቸውንና የመቼ ዘመን ሥሪት እንደሆኑ የሚለይበት ነው ተብሏል።

ጥናቱ በዓይነቱ ለመጀመርያ ጊዜ የተደረገ ሲሆን ተቋሙ ከዚህ ቀደም በግምታዊ የሀብት ቆጠራ ምን ያህል ሀብት እንዳለው እንደሚያውቅ፣ በዚህ ወቅት የሚደረገው ሀብቱን በአካል ተገኝቶ መቁጠር ብቻ ሳይሆን የኔትወርኩን የጥራት ደረጃ የሚፈተሽበት መሆኑም ተመላክቷል፡፡

via - reporter
7.1K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 11:26:26
ኮካኮላ ስኳር ፋብሪካ ለመግዛት እያጠና ነው

ኮካኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ከፍተኛ የስኳር እጥረት በመመልከት መንግስት ከሚሸጣቸው የስኳር ፋብሪካዎች መካከል አንዱን ለመግዛት ጥናት እያደረገ እንደሆነ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

የለስላሳ መጠጥ አምራቹ ስኳርን እንደ በግብአትነት የሚጠቀም ሲሆን በሀገር ውስጥ በተፈጠረው የስኳር ምርት እጥረት የተነሳ የስኳር ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ከውጪ ለማስገባት ተገዷል፡፡ ይህም በሀገሪቱ ካለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተዳምሮ በኩባንያው ላይ ጫና መፍጠሩ ታውቋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት የኩባንያው ማኔጅመንት መንግስት ለጨረታ ካቀረባቸው የስኳር ፋብሪካዎች መካከል አንዱን ለመግዛት ጥናት እያካሔደ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ እቅዱ በኩባንያው ቦርድ ተቀባይነት ካገኘ ወደ ግዢ ሂደት እንደሚገባ ታውቋል፡፡ የኮካኮላ ፤ ፋንታ እና ስፕራይት አምራች የሆነው ኮካኮላ ቤቨሬጅስ በቅርቡ አዳዲስ የተለያየ ጣዕም ያላቸው ጁስ ምርቶች አምርቶ ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
7.1K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 10:21:39
የቱሪዝም ሚኒስቴር የ2015 ዕቅድ በፓርላማ ውድቅ ተደረገ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓም. ከቱሪዝም ሚኒስቴር የቀረበለትን የ2015 ዓ.ም. የዘርፉን ዕቅድና የመጀመርያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ካዳመጠ በኋላ፣ ሁለቱንም ውደቅ አድርጓል፡፡ ሚኒስቴሩ የዓመቱን ዕቅድና የሩብ ዓመቱን አፈጻጸም ሪፖርት እንደገና አዘጋጅቶ በማኔጅመንት አፀድቆ እንዲያመጣ ታዟል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ሚኒስቴሩ ሦስት ዓይነት የተለያዩ ግቦችን ማቅረቡና በሰነድ የቀረበው ሪፖርትና ገለጻ የተደረገው ልዩነት ስላለው ለመገምገም አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ገልጸዋል። የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ስለሺ ግርማ ግን ሪፖርቶቹን ሲያቀርቡ፣ ሰነዶቹ ማለፍ ያለባቸውን ሁሉ ሒደቶች ያላለፉ መሆናቸውን ጠቅሰው ነበር፡፡  

via - Reporter
7.1K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ