Get Mystery Box with random crypto!

አልሳም ግሩፕ ‹‹አልሳም መንደር›› የተሰኘ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረ። | ሰሌዳ | Seleda

አልሳም ግሩፕ ‹‹አልሳም መንደር›› የተሰኘ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረ

አልሳም ግሩፕ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት መንግሥት ባስቀመጠው የመንግሥትና የግል ትበብር መርህ መሠረት ለማሟላት በከተማዋ ‹‹አልሳም መንደር›› በሚል መጠሪያ የሪል ስቴት ልማት ለማከናወን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። 

‹‹አልሳም መንደር›› በሚል መጠሪያ የሚገነባው የሪል ስቴት ልማት ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ሕንፃ ጀርባ በሚገኝ 1460 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ እንደሆነ የተናገሩት የአልሳም ግሩፕ ተወካይ አቶ ካሚል ሳቢር፣ ይዞታውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ በሊዝ መረከባቸውንና በዚህ ይዞታ ላይም 200 መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩት ባለ 30 ወለል ከፍታ ሕንፃ እንደሚገነባ አስታውቀዋል።

በአልሳም ግሩፕ ሥር በሚገኙ ሁለት እህትማማች ኩባንያዎች በ2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሁለት የመኖሪያ ሕንፃዎችን (አፓርትመንቶች) ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመረቁ ሲሆን፣ ከንቲባዋ የአልሳም መንደር የሪል ስቴት ግንባታ ለማስጀመርም የመሠረት ድንጋይ ማይኖራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።