Get Mystery Box with random crypto!

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ሀብት ቆጠራና የዋጋ ትመና ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ። የኢትዮጵያ | ሰሌዳ | Seleda

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ሀብት ቆጠራና የዋጋ ትመና ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ መሠረተ ልማት ብዛትና ወቅታዊ ዋጋ በተመለከተ ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ቆጠራው የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ምን ያህል ምሰሶዎች እንዳሉት፣ የት እንደሚገኙ፣ ከምሰሶዎች አቅራቢያ ምን ያህል ቤቶች እንደሚኖሩ፣ በአንድ ምሰሶ ምን ያህል ሰዎች እንደሚጠቀሙ፣ የተበላሹ ቆጣሪዎች ምን ያህል እንደሆኑ፣ ትራንስፎርመሮች በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ፣ ማርጀት አለማርጀታቸውንና የመቼ ዘመን ሥሪት እንደሆኑ የሚለይበት ነው ተብሏል።

ጥናቱ በዓይነቱ ለመጀመርያ ጊዜ የተደረገ ሲሆን ተቋሙ ከዚህ ቀደም በግምታዊ የሀብት ቆጠራ ምን ያህል ሀብት እንዳለው እንደሚያውቅ፣ በዚህ ወቅት የሚደረገው ሀብቱን በአካል ተገኝቶ መቁጠር ብቻ ሳይሆን የኔትወርኩን የጥራት ደረጃ የሚፈተሽበት መሆኑም ተመላክቷል፡፡

via - reporter