Get Mystery Box with random crypto!

ኮካኮላ ስኳር ፋብሪካ ለመግዛት እያጠና ነው ኮካኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው | ሰሌዳ | Seleda

ኮካኮላ ስኳር ፋብሪካ ለመግዛት እያጠና ነው

ኮካኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ከፍተኛ የስኳር እጥረት በመመልከት መንግስት ከሚሸጣቸው የስኳር ፋብሪካዎች መካከል አንዱን ለመግዛት ጥናት እያደረገ እንደሆነ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

የለስላሳ መጠጥ አምራቹ ስኳርን እንደ በግብአትነት የሚጠቀም ሲሆን በሀገር ውስጥ በተፈጠረው የስኳር ምርት እጥረት የተነሳ የስኳር ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ከውጪ ለማስገባት ተገዷል፡፡ ይህም በሀገሪቱ ካለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተዳምሮ በኩባንያው ላይ ጫና መፍጠሩ ታውቋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት የኩባንያው ማኔጅመንት መንግስት ለጨረታ ካቀረባቸው የስኳር ፋብሪካዎች መካከል አንዱን ለመግዛት ጥናት እያካሔደ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ እቅዱ በኩባንያው ቦርድ ተቀባይነት ካገኘ ወደ ግዢ ሂደት እንደሚገባ ታውቋል፡፡ የኮካኮላ ፤ ፋንታ እና ስፕራይት አምራች የሆነው ኮካኮላ ቤቨሬጅስ በቅርቡ አዳዲስ የተለያየ ጣዕም ያላቸው ጁስ ምርቶች አምርቶ ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ይታወቃል፡፡