የቱሪዝም ሚኒስቴር የ2015 ዕቅድ በፓርላማ ውድቅ ተደረገ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓም. ከቱሪዝም ሚኒስቴር የቀረበለትን የ2015 ዓ.ም. የዘርፉን ዕቅድና የመጀመርያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ካዳመጠ በኋላ፣ ሁለቱንም ውደቅ አድርጓል፡፡ ሚኒስቴሩ የዓመቱን ዕቅድና የሩብ ዓመቱን አፈጻጸም ሪፖርት እንደገና አዘጋጅቶ በማኔጅመንት አፀድቆ እንዲያመጣ ታዟል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ሚኒስቴሩ ሦስት ዓይነት የተለያዩ ግቦችን ማቅረቡና በሰነድ የቀረበው ሪፖርትና ገለጻ የተደረገው ልዩነት ስላለው ለመገምገም አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ገልጸዋል። የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ስለሺ ግርማ ግን ሪፖርቶቹን ሲያቀርቡ፣ ሰነዶቹ ማለፍ ያለባቸውን ሁሉ ሒደቶች ያላለፉ መሆናቸውን ጠቅሰው ነበር፡፡ via - Reporter 7.1K views07:21