Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 142

2022-11-16 13:07:03
ከሳተላይቶች ጋር በኅብረት የምትሠራ ሌላ ሳተላይት ለማምጠቅ መታቀዱ ተገለጸ

ለመሬት ምልከታ የሚያገለግሉ ሳተላይቶችን ካመጠቀ ኩባንያ ጋር ውል በመግባት የኢትዮጵያን ሁለተኛ ሳተላይት አምጥቆ፣ በኅብረ ሳተላይት (satellite constellation) በጋራ መረጃ ለመሰብሰብ ማቀዱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከሌሎች ሳተላይቶች ጋር በኅብረት የምትሠራ የመሬት ምልከታ ሳተላይት በተያዘው የ2015 በጀት ዓመት ለማምመጠቅ ዕቅድ እንደያዘና የኢትዮጵያን ሳተላይት በህብረ ሳተላይት ውስጥ የሚያካትት ኩባንያ የሚመረጥበት ጨረታ ለማውጣት በዝግጅት ላይ እንደሆነ፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ኅብረ ሳተላይት ለአንድ ዓላማ ተልከው ምድርን የሚዞሩ ሳተላይቶች ስብስብ ሲሆን፣ ከአንድ የምድር አካባቢ መረጃ ለማግኘት አንድ ሳተላይት ዞሮ እስከሚመለስ ለመጠበቅ ሳያስፈልግ ተተኪ ሆኖ ያንን አካባቢ ከሚዞር ሌላ ሳተላይት መረጃ መቀበል ይቻላል፡፡

via - Reporter
6.9K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 10:44:02
የኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ ድርሻ ለግል ሊዛወር ነው።

አርባ በመቶ የሚሆነው የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ ወደ ግል ሊዛወር መሆኑን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። ለዚህም ሲባል ሶስተኛ ፍቃድ ለመስጠት ዛሬ ምክክር እየተካሄደ ይገኛል።

via - capital
7.1K views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 08:19:53
በመዲናዋ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት የተጀመረው እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት የተጀመረው እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት 14ኛው 20/80 እንዲሁም 3ኛው 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል።

የከተማው ህዝብ ዋነኛ ጥያቄ የሆነውን የቤት ችግር ለማቃለል ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮችን ገቢራዊ እያደረገ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ ከዚህ አኳያ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ቤቶችን ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል። ለአብነትም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ያለው የ10 ሺህ ተገጣጣሚ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

via - ena
7.7K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 20:04:12
የኬንያ ጫት ላኪዎች ለሱማሊያ ገበያ ጫት ከኢትዮጵያ እየገዙ እያቀረቡ መሆኑ ተገለፀ።

የኬንያ ጫት ላኪዎች ለሱማሊያ ገበያ ጫት ከኢትዮጵያ እየገዙ እያቀረቡ መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ኬንያዊያን ጫት ላኪዎች ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ጫት ያዞሩት፣ የኬንያ ጫት ዋጋው ከፍተኛ በመሆኑ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።

የኬንያ ላኪዎች በቀን ወደ ሱማሊያ ከሚልኩት 19 ቶን ጫት 40 በመቶውን እየገዙ ያሉት ከኢትዮጵያ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ኬንያዊያኑ ጫት ላኪዎች ከኬንያ ጫት ወደ ሱማሊያ ለመላክ፣ ለደላላ እና ለአየር ትራስፖርት በእያንዳንዷ ኪሎ ግራም በትንሹ 10 ዶላር ይከፍላሉ።

via - Addis standard
8.5K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 17:13:37
የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለዕድለኞች ዝርዝር በጋዜጣ እንደሚታተም ተገለፀ።

የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የአዲስ አበባ የጋራ መኖርያ ቤቶች የእጣ አወጣጥ ሂደት ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተደረገ መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል። የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ሂደቱ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተደረገ ተደርጓል።

በስነ ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው የመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ፣ ሴቶች 30 በመቶ፣ አካል ጉዳተኞች 5 በመቶ እንዲሁም ቀሪው 45 በመቶ በእጣ ባለእድለኞች እንደተለዩ ተገልጿል። የባለእድለኞቹ ስም ዝርዝር በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ለህዝብ እንደሚሰራጭም ተነግሯል።
8.5K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 14:39:11
#ጥቆማ

ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በቀጥታ እያሰራጨ ይገኛል፤መከታተል ትችላላችሁ።
8.4K views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 14:16:21
በአዲስ አበባ በ500 ቢሊዮን ብር “ሳተላይት ሲቲ” እንደሚገነባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአዲስ አበባ ከተማ ከ400 እስከ 500 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ “ሳተላይት ሲቲ” እንደሚገነባ ተናግረዋል። “ጫካ ሃውስ” የሚል ስያሜ ያለው ይህ ፕሮጀክት፤ ቢያንስ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያስገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ነው። አብይ የ“ጫካ ሃውስ” ፕሮጀክት ጉዳይን ያነሱት፤ ከሰሞኑ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ49 ቢሊዮን ብር ቤተ መንግስት እየገነቡ ነው” በሚል የተሰራጩ ሀሰተኛ ዘገባዎችን በመጥቀስ ነው።

“ልንገነባ ያሰብንው ‘የጫካ ሃውስ’ ይባላል። ልንገነባ ያሰብንው ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ ኩራት የሚሆን ‘ሳተላይት ሲቲ’ ነው። ልንገነባ ያሰብንው የኢትዮጵያን ቤት ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
8.2K views11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 11:37:43
"ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ባለትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት ናት። !!" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በሚመለከት አንድ ኢትዮጵያዊ በነፍስወከፍ 1 ሺህ 212 ዶላር ገቢ ያገኛል ሲሉ ምላስ ሰጥተዋል።

አክለውም በኢኮኖሚዉ የታየዉ ለዉጥ በ2014 በጀት 6.61 ትሪሊዮን ብር ወይንም 126.7 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ገልጸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ 1ኛ፣ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ደግሞ 3ኛ እንደሆነ የአለም ባንክን መረጃ አጣቅሰው ጠቁመዋል።

የአለም ባንክ መረጃ ምን ይላል?

1ኛ: የናይጄርያ GDP= 440.7 ቢልዮን ዶላር
2ኛ: የደቡብ አፍሪካ GDP= 419.9 ቢልዮን ዶላር
3ኛ: የኢትዮጵያ GDP= 111.2 ቢልዮን ዶላር
4ኛ: የኬንያ GDP= 110.3 ቢልዮን ዶላር
5ኛ: የአንጎላ GDP= 72.5 ቢልዮን ዶላር
7.8K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 14:06:21
በቀን ከ30 ሽህ ሊትር በላይ ዘይት የማምረት አቅም ያለው "ዩኒሰን" የምግብ ዘይት ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ።

በባህር ዳር ከተማ በቀን ከ30 ሽህ ሊትር በላይ የማምረት አቅም ያለው "ዩኒሰን" የምግብ ዘይት ፋብሪካ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በተገኙበት ተመርቆ ማምረት ጀምሯል። ፋብሪካው 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጭ የተደረገበትና የሀገር ውስጥ ጥሬ እቃዎችን በመጠቀም የምግብ ዘይት እንዲያመርት ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው።

ፋብሪካው አኩሪ አተር፣ ሱፍ፣ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ለውዝና ሌሎች የሀገርው ውስጥ የቅባት እህሎችን በመጠቀም ማምረት የሚችል መሆኑ ተገልጿል። ፋብሪካው በሰፊው ምርት በማምረት በአቅርቦትም ሆነ በዋጋ የማህበረሰቡን የዘይት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ አላማ ይዞ ስራ የጀመረ መሆኑንም ተመላክቷል። ።

via - ena
2.1K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ