Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት የተጀመረው እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል ተባ | ሰሌዳ | Seleda

በመዲናዋ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት የተጀመረው እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት የተጀመረው እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትላንት 14ኛው 20/80 እንዲሁም 3ኛው 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል።

የከተማው ህዝብ ዋነኛ ጥያቄ የሆነውን የቤት ችግር ለማቃለል ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮችን ገቢራዊ እያደረገ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ ከዚህ አኳያ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ቤቶችን ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል። ለአብነትም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ያለው የ10 ሺህ ተገጣጣሚ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

via - ena