Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 143

2022-11-13 12:11:36
በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሊቋቋም ነው ተባለ።

በኢትዮጵያ ኒውክሌርን ለኃይል ማመንጫነትና በተለያዩ ዘርፎች ለሚሠሩ ሥራዎች የማዋል ኃላፊነትን የሚወጣ፣ የኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ኢንስቲትዩቱን የሚመራ የኒውክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት ሊቋቋም መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

በኒውክሌር ዘርፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚመራው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኢንስቲትዩቱና ምክር ቤቱን የሚያቋቁሙ ሁለት ደንቦችን አዘጋጅቶ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ አገራዊ የኒውክሌር ሳይንስ የሰው ሀብት ጥናት ልየታ በማድረግም ባለሞያዎችን ለሥልጠና ወደ ሩስያና ቻይና መላኩን ጠቁሟል፡፡

ይህ በኒውክሌር ሳይንስ ዘርፍ ተቋም የማቋቋምና የአቅም ግንባታ እያደረገ ያለው ኢትዮጵያና ሩስያ ጥቅምት 2012 ዓ.ም. በሩስያ ሱሺ ከተማ በተፈራረሙት ስምምነት መነሻነት መሆኑን የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አለምነው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
3.2K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 09:10:26
መንግሥት በመጋዘን ውስጥ ለመጠባበቂያ የሚሆን የስኳር ክምችት እንደሌለው ገለጸ

መንግሥት በሩብ ዓመቱ ከ835 ሺሕ በላይ ኩንታል ስኳር ለማሠራጨት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ማሠራጨት የቻለው 284 ሺሕ ኩንታል ስኳር ብቻ መሆኑን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ የተቋማቸውን የ2015 ዓ.ም. የመጀመርያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ለንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በፍራንኮ ቫሉታ ከታክስና ከቀረጥ ነፃ 1.8 ሚሊዮን ኩንታል የስኳር ምርት ወደ አገር ውስጥ እንደገባ ተጠቅሷል፡፡ አክለውም ስኳር ኮርፖሬሽን ባለፉት ወራት ማስገባት የነበረበትን ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ወደ ገበያ ማስገባት ባለመቻሉ፣ ገበያ ላይ እጥረት መፈጠሩንና ለሕዝቡ መድረስ የነበረበት መጠን ሊደርስ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በመንግሥት የተሠራጨውን 835 ሺሕ ኩንታል ስኳር ለዝቅተኛ የማኅበረሰብ ክፍሎች እንዲሆን ታስቦ በኮታ እንዲሠራጭ ወደ ተለያየ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቢሠራጭም፣ ስኳሩን ለመውሰድ ኩፖን ለማይገባው ሁሉ በመስጠቱ ስኳሩን ሲወስደው የነበረው የማይገባው ሰው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ስኳር እጥረት በማጋጠሙ ለዩኒቨርሲቲዎችና ለትምህርት ቤቶች የሚፈለገውን ስኳር ማቅረብ የተቻለው ኮርፖሬሽኑ ከነበረው ክምችት ውስጥ አሟጦ መሆኑን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በተጠናቀቀው ሳምንት በርካታ ስብሰባዎችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በእነዚህ ስብሳባዎች ለተሰብሳቢዎች ሲቀርብ የነበረው ሻይ፣ ቡናና ወተት ያለ ስኳር እንደነበር ሪፖርተር ዘግቧል።
4.4K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 21:34:52
በስፖርት ታሪክ ትልቁ ስፖንቸርሺፕ!

ኤርሊንግ ሃላንድ በቅርቡ በስፖርት ታሪክ ትልቁን የስፖንቸርሺፕ ውል ከአዲዳስ ጋር ይፈራረማል። በፕሪሚየርሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ የሚገኘው እና የማንችስተር ሲቲው የጎል ማሽን በቅርቡ ከአዲዳስ ጋር ዳጎስ ያለ ገቢ የሚያስገኝለትን ስፖንቸርሺፕ እንደሚፈራረም ተገልጻል።
2.7K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 19:02:02
መንግስት የባንክ ዘርፉን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት እንደማያደርግ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ሱፐርቪዥን ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ በባንክ ዘርፍ ለመሳተፍ ለሚመጡ የውጭ ባንኮችን በሙሉ ተቀብሎ ፈቃድ አይሰጥምና ለመነሻነት ውስን የውጭ ባንኮችን ብቻ እንደሚስተናገዱ ገልፀዋል። ለዚህም የውጭ ባንኮችን ለማስተናገድ አራት ቅድመ ሁኔታዎች ተዘጋጅተዋል።

ፈቃድ ማግኘት የሚችሉት ባንኮች በኢትዮጵያ ንዑስ ባንክና ቅርንጫፍ ለማቋቋም የሚጠይቁና ከሀገር ውስጥ ባንኮች እስከ 40 በመቶ አክሲዮን የሚገዙ ናቸው።

ከአገልግሎት አንፃር በተለይ ለግብርና፣ ለቤትና ሌሎች መሰረተ ልማት ግንባታ እንዲሁም ለገጠር አካባቢዎች የተለያዩ አገልግሎት ለመስጠት አልመው የሚመጡ ባንኮች የሚኖራቸው ፋይዳ ጉልህ ነው።

የውጭ ባንኮች መልካም እድል ይዘው እንደሚመጡት ሁሉ ስጋቶች ይኖራሉ ስጋቶችን ለመቀነስም በዘርፉ ያለው ልምድ እየዳበረ እስከሚሄድ ድረስ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የውጭ ባንኮችን ቁጥር በመገደብና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በትኩረት ይሰራል።

ምንጭ - ኢዜአ
4.7K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 16:17:15
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ 42.1 ሚሊዮን ቢር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የኮምኒኬሽን ዘርፍ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በአዲስ አበባ ከጀመረ በኋላ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ 42.1 ሚሊዮን ቢር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። እስከ አሁን ድረስ ኩባንያው 740,000 ደንበኞች ማፍራቱን ካፒታል ዘግቧል።

ኩባንያው ትላንት የግማሽ ዓመት አፈፃፀሙን ሪፖርት በናይሮቢ ባቀረበበት ወቅት በሚቀጥለው ሳምንት አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥር አንድ ሚልየን እንደሚገባ ገልጿል።
5.6K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:18:53
“አሚን አዋርድ” የተሰኘ የሥራ ፈጠራ ውድድር ይፋ ተደረገ

አቢሲኒያ ባንክ “አሚን አዋርድ” የተሰኘ የሥራ ፈጠራ ውድድር ይፋ አድርጓል። ውድድሩ በአቢሲኒያ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኩል የተዘጋጀ ሲሆን የማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ተከናውኗል።

የመነሻ ፋይናንስ ላጡ የስራ ሀሳብ ላላቸው ወጣቶች ከ200 ሺሕ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ ሽልማት የሚያስገኝ ነው ተብሏል። ይህ የስራ ዕድል ፈጠራ ውድድር የተሻለ ሀሳብ ላላቸው እድል እንደሚፈጥር ይታመናል።

via - fbc
5.9K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 12:24:37
ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያ፣ ኤፍቲኤክስ [FTX] መክሰሩን በይፋ አወጀ።

ይህን ተከትሎም የኩባንያው መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወጣቱ ቢሊየነር ሳም ባንክማን-ፍራይድ ሥልጣኑን በይፋ ለቋል። በትንሽ ቀናት ውስጥ ድንገተኛ የገንዘብ እጥረት የገጠመው ወጣቱ የክሪፕቶ ንጉሥ ሳም፣ በገንዘብ የሚታደገው ፋይናንስ ተቋም ለማግኘት ቢጣጣርም አልሆነለትም። 

በዚህም የተነሳ በዓለም ላይ ሁለተኛው ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያ የነበረው ኤፍቲኤክስ በአንድ ጀንበር እንዳልነበረ ሆኖ መንኮታኮቱን ቢቢሲ ፅፏል። ይህ መረጃ ከወጣ በኋላ በርካታ ደንበኞች ክሪፕቶዎቸቸውን ለመመንዘር እሽቅድምድም ውስጥ በመግባታቸው ኩባንያው ኪሳራን በይፋ ለማወጅ ተገዷል።

አሁን በይፋ ኪሳራን በማወጁ ኩባንያው በፍርድ ቤት ክትትል ስር ሆኖ የተወሰነ ሥራ እንዲቀጥልና ራሱን ከወደቀበት እንዲያነሳ ዕድል ይሰጠዋል። ኤፍቲኤክስ እንዳለው በአሁኑ ወቅት ግብ አድርጎ የተነሳው ሁኔታዎችን በስክነት አጥንቶ ያለውን ሃብት ወደ ገንዘብ ቀይሮ የኩባንያውን ባለድርሻዎች ከውድቀት መታደግ ነው።

የኤፍቲኤክስ መንኮታኮት በሌሎችም የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይቶች ጰላይ ጥላውን ጥሏል። ከክሪብቶከረንሲዎች ሁሉ ገናናው ቢትኮይን ለምሳሌ በ20 ከመቶ ዋጋው አሽቆልቁሎ በህዳር ወር በታሪኩ ከፍተኛውን ስኬት ካስመዘገበበት የ70,000 ዶላር ምንዛሬ በመውረድ ዛሬ ላይ አንድ ቢትኮይን 16,764 ዶላር እየተመነዘረ ነው።
6.0K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 10:37:38
በሩብ ዓመቱ 960 ሚሊዮን ዶላር ከኢንቨስትመንት ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የ2015 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት፣ በሩብ ዓመቱ 1 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር ከኢንቨስትመንት ፍሰት ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ 960 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ገልጿል። ሆኖም የተገኘው ገቢ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

በሌላ በኩል በሩብ ዓመቱ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርት ወደ ውጭ ገበያ በመላክ ከሚገኝ ገቢ 34 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ገልጿል። የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም ቅናሽ አለው ያለው ኮሚሽኑ፣ ለዚህ እንደምክንያት የፓርኮቹ ገበያ 90 በመቶው ወደ አሜሪካ በመሆኑና በአጎዋ ገበያ መሰረዝ የተነሳም በተለይ የገበያ መሠረታቸውን አሜሪካ ያደረጉ ኩባንያዎች በመዘጋታቸው ነወ ብሏል።

via - Addis maleda
5.8K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 07:58:30
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እየተቸገረ መሆኑን ገለፀ።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እየተቸገረ መሆኑን መናገሩን ሪፖርተር ዘግቧል። አስተዳደሩ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለተቋራጮች መክፈል የነበረበትን 10 ቢሊዮን ብር መክፈል ባለመቻሉ፣ ተቋራጮች የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን እንዳቋረጡ ዘገባው ጠቅሷል።

ከ200 የፌደራል መንገድ ፕሮጀክቶች መካከል፣ 60 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በጸጥታ መጓደል ሳቢያ እንደተቋረጡ አስተዳደሩ መግለጹን ዘገባው ጨምሮ ገልጧል። አስተዳደሩ ይህን የገለጠው፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።
907 views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 19:10:56
የወዳጅነት አደባባይ የዋጋ ተመን

ጥቅምት 20/ 2015 ዓ.ም በድምቀት ተመርቆ የተከፈተው የወዳጅነት አደባባይ ምዕራፍ 2 ለአንድ ሳምንት ያህል በነፃ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ከነገ ቅዳሜ ህዳር 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት በክፍያ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል። የክፍያ ስርዓቱም በቴሌብር እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፖስ ማሽኖች ብቻ ነው።
5.2K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ