Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 146

2022-11-09 08:05:50
በታክሲዎች ውስጥ ተገጥሞ ማስታዎቂያዎችን ማስተላለፍ የሚችል ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ

“ኤም ቢ ዋይ ኢትዮጵያ” የታክሲ አገልግሎት መስጠት በሚችሉ መኪናዎች የፊት ለፊት ወንበር ጀርባ በሚገጠም ስክሪን የድርጅቶችን ማስታወቂያዎች ለተሳፋሪዎች ማድረስ የሚችል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል፡፡ቴክኖሎጂው ክላውድ ላይ የተመሰረተና በኢንተርኔት የሚሰራ ሲሆን፣ ኢንተርኔት በማይኖርበት ጊዜም መስራት የሚችል ነው፡፡

ይህ ቴክሎጂ ይፋ ከመደረጉ በፊትም በአዲስ አበባ ውስጥ አገልግሎት በሚሰጡ 250 ዘ-ሉሲ ታክሲዎቸ ላይ የማስታወቂያ ስክሪኖች ለሙከራ ተገጥመው 18 ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን መልካም ግብረመልስ እንደተገኘም ተገልጧል፡፡

ኤም ቢ ዋይ ኢትዮጵያ የዚህን ቴክኖሎጂ ተደራሽነት በማስፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ በ5 ሺሕ ታክሲዎች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ያስታወቀ ሲሆን፤ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች፣ በአየር መንገዶች፣ በትምህርት ተቋማት፣ በጤና ተቋማት እንዲሁም በበርካታ ቦታዎች ላይ የሚስፋፋ እንደሆነ ቴክሎጂው ይፋ በተደረገበት ሥነ ስርዓት ላይ ተነግሯል፡፡
7.5K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 18:49:56
በኢትዮ- ኬንያ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሙከራ ሥራ ስኬታማ እንደሆነ ተገለፀ

በኢትዮ- ኬንያ የኮንቨርተር ስቴሽንና የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ላይ ኃይል የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ በዛሬው ዕለት በስኬት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

የኢትዮ- ኬንያ የማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ስቴሽን ፕሮጀክት በ334 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደተገነባ ሲነገር የኤሌከትሪክ ኃይል ኩባንያው እስከ 2000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው ገልጿል።

በኢትዮጵያ በኩል በተገነባው የኢትዮ - ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ላይ 994 የመስመር ተሸካሚ ታወሮች የተተከሉ ሲሆን 440 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የዳታ ሲግናል ማስተላለፊያ ኬብሎችም ተዘርግተውለታል።
8.2K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 16:13:13
ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ስንዴ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ከላኪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጿል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፥ ኢትዮጵያ የእርዳታ ስንዴ ከማስገባት አልፋ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ስንዴ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ወደ ውጭ የሚላከው ስንዴ ከሀገር ውስጥ ፍጀታ የተረፈ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ለዚሁ ይረዳ ዘንድ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ላኪዎችም በፊት ኢትዮጵያ የነበራት ገጽታ ተቀይሮ ከስንዴ አስመጪነት ወደ ላኪነት መሸጋገሯ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው የተጣለባቸውን ሀገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑ መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
8.1K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 12:50:30
ሜታ ኩባንያ በዚህ ሳምንት በርካታ ሰራተኞቹን እንደሚያባርር ተነገረ።

የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ በዚህ ሳምንት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ለማሰናበት አቅዷል ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን ጠቅሶ ዘግቧል። ሜታ በጥቅምት ወር ደካማ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ማስመዝገቡን አሳውቋል። በዚህ ዓመት ከግማሽ ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል የተባለ እሴት እንዳጣም ተናግሯል።

ሮይተርስ እንደዘገበው ውድቀቱ የመጣው ከቀዘቀዘው የአለም ምጣኔ ሀብት እድገት ፣ ከቲክ ቶክ ውድድር እንዲሁም ከአፕል ኩባንያ የግላዊነት ፖሊሲ ለውጦች ጋር ይያያዛል። የሜታ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ሰራተኞቹን የምጣኔ ሀብት ውድቀቱን እንዲያግዙም አስጠንቅቀዋል ።

ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን፣ ትዊተር እና ስናፕን ጨምሮ በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ ስራተኞቻቸውን ከስራ እያሰናበቱ ነወ። የዓለም ምጣኔ ሀብት እድገት በከፍተኛ የወለድ ተመኖች ፣የዋጋ ግሽበት እና በኃይል ቀውስ ሳቢያ እየቀነሰ በመምጣቱ ቅጥርን ቀንሰዋል።
8.1K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 10:14:33
የኢትዮጵያን ደረጃ ያላሟሉ 317 ነጥብ 83 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሩብ ዓመቱ ከ2 ሺህ 396 አስመጪዎች ጥያቄዎችን በመቀበል በ600 ሺህ ሜትሪክ ቶን ገቢ ምርቶች ላይ የፍተሻ ሥራ ለማከናወን አቅዶ በ759 ሚሊየን 491 ሺህ 346 ሜትሪክ ቶን የገቢ ዕቃዎች ላይ የፍተሻ ሥራ ማከናወኑን ገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሦስት ወራት ገቢ ምርቶች ላይ በተደረገ የላቦራቶሪ ፍተሻ እና የቁጥጥርና ፍተሻ ስራ 0 ነጥብ 111 ሜትሪክ ቶን ዘይት፣ 3 ነጥብ 35 ቶን ኤል ኢ ዲ አምፖል፣ 2 ነጥብ 76 ቶን የኤሌክትሪክ ገመድ፣ 54 ነጥብ 51 ቶን የታሸገ ሩዝ እና 257 ነጥብ 1 ቶን የስንዴ ዱቄት ከደረጃ በታች ሆነው በመገኘታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
7.8K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 09:20:10
በ158 ወረዳዎች የስንዴ ዋግ በሽታ መከሰቱን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የስንዴ ዋግ በሽታው በተለይም ስንዴ አብቃይ በሆኑ ክልሎች በደቡብ፣ በሲዳማ፣ በአማራ፣ በቤንሻጉል ጉምዝ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች በአጠቃላይ ከ399 ሺሕ ሄክታር መሬት በላይ በለማ ስንዴ ላይ የተከሰተ መሆኑን ነው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያሳወቀው። በሽታውን ለመከላከል እስካሁን 308 ሺሕ ሊትር የኬሚካል ርጭት መካሄዱን የተገለፀ ሲሆን ሆኖም የኬሚካሉ ዋጋ መወደድ በአርሶ አደሮች ላይ ጫና ሳይፈጥር እንዳልቀረ ተጠቁሟል።

በሽታው በምርት ላይ የሚያደርሰውን የጉዳት መጠን ለመለየት ጥናት እየተደረገ ሲሆን ይህም የመስክ ባለሙያዎች ጥናቱን ሲጨርሱ የሚታወቅ ይሆናል ተብሏል። ከኬሚካል ርጭቱ ባለፈ በሽታ ሊቋቋሙ የሚችሉ የስንዴ ዝርያዎችን አርሶ አደሩ እንዲጠቀም በመደረጉ የጉዳት መጠኑን ሊያቀለው እንደቻለ ተመላክቷል። በምርት ዘመኑ በመኸር ምርት ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይገኛል መባሉ የሚታወስ ነው።

ምንጭ - አዲስ ማለዳ
7.9K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 07:37:19
የመድን ተቋማት ለተሽከርካሪ የመድን ሽፋን ዝቅተኛ አረቦን ጣራ ተግባራዊ አደረጉ።

የመድን ተቋማት በስምምነት ለተሽከርካሪ የመድን ሽፋን ዝቅተኛ አረቦን ጣራ አስቀምጠው ካለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 22 አንስቶ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።

በዚህም እንደተሽከርካሪው የስራ አይነት ከ1.5 በመቶ እስከ 4 በመቶ የሚሆን የተሽከርካሪው ዋጋ መቶኛ ለመድን ሽፋን እንዲከፈል ተስማምተዋል።

Via - capital
7.8K views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 08:05:20
በአዳማ የ5ጂ አገልግሎት የጀመረው ኢትዮ ቴሌኮም በሌሎች ከተሞችም ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

ከአዲስ አበባ ውጭ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎትን በአዳማ ከተማ ያስተዋወቀው ኢትዮ ቴሌኮም፣ በተጨማሪ የክልል ከተሞች ኔትወርኩን ለመዘርጋት የዳሰሳ ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የ5ጂ ኔትወርክ በከተሞቹ ምን ሊሠራ ይችላል? የሚለው አንዱ የዳሰሳ ጥናቱ የሚመለከተው ጉዳይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ከአዳማ ቀጥሎ በየትኛው የክልል ከተማ የ5ጂ አገልግሎት እንደሚያስጀምር አልተገለጸም፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን የ5ጂ ሙከራ ስፔክትረም ምደባ የተደረገለት ለአንድ ዓመት የሙከራ ጊዜ ሲሆን የሙከራ ምደባው የተሰጠውም በአዲስ አበባ፣ በአዳማና በሐዋሳ ከተሞች እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም 99 በመቶ የኔትወርክ ሽፋን ያለው ቢሆንም ከጫፍ እስከ ጫፍ የ5ጂ አገልግሎቱን እንደማያስፋፋ የገለጹት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ በዓላማና በምክንያት የት አካባቢ ቢደረግ ችግር ይፈታል? ዕሴት ይጨምራል? የሚለው እየታየ የሚሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ - ሪፖርተር
2.4K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 22:14:42
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት የክብር ዶክተር አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየ ሲሆን ዛሬ ምሽት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።
1.3K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 17:45:01
በዓለም ከፍተኛ የተባለው 1.6 ቢሊየን ዶላር የሚያስገኘው ሎተሪ በአሜሪካ ወጣ።

ባለፉት ሦስት ወራት አሸናፊ ሳያገኝ የቆየው በአሜሪካ ቀዳሚ የሆነው ሎተሪ፣ ትላንት ባወጣው ዕጣ በዓለም እስካሁን ከታዩት የሎተሪ ዕጣ ሽልማቶች ከፍተኛውን መሆኑ ተነግሯል። ይህን ፓወርቦል የተባለውን የጃክፖት ሎተሪ ዕጣ አሸናፊ የሚሆነው ግለሰብ ለመንግሥት ከሚቆረጥበት ግብር በፊት 1.6 ቢሊየን ዶላር ገንዘብ አሸናፊ ይሆናል።

ይህም የሎተሪ ዕጣ ሽልማት እስካሁን በዓለም ከተመዘገበው ከፍተኛው እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን፣ በዚሁ ተመሳሳይ ሎተሪ ከስምንት ዓመት በፊት በወጣ ዕጣ ሦስት ባለዕድሎች ከፍተኛ የተባለውን ክብረ ወሰን 1.59 ቢሊዮን ዶላር አሸንፈው ተካፍለው ነበር።

ይህ የፓወርቦል የሎተሪ ጨዋታ የጀመረው በአውሮፓውያኑ 1992 ሲሆን፣ ዋና ከተማዋን ዋሽንግተንን፣ የባሕር ማዶ የአሜሪካ ግዛት የሆኑትን ፖርቶ ሪኮን እና ቨርጂን ደሴቶችን ጨምሮ በአሜሪካ 45 ግዛቶች ውስጥ ሎተሪው ይሸጣል።

via - bbc
5.0K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ