Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያን ደረጃ ያላሟሉ 317 ነጥብ 83 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እ | ሰሌዳ | Seleda

የኢትዮጵያን ደረጃ ያላሟሉ 317 ነጥብ 83 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሩብ ዓመቱ ከ2 ሺህ 396 አስመጪዎች ጥያቄዎችን በመቀበል በ600 ሺህ ሜትሪክ ቶን ገቢ ምርቶች ላይ የፍተሻ ሥራ ለማከናወን አቅዶ በ759 ሚሊየን 491 ሺህ 346 ሜትሪክ ቶን የገቢ ዕቃዎች ላይ የፍተሻ ሥራ ማከናወኑን ገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሦስት ወራት ገቢ ምርቶች ላይ በተደረገ የላቦራቶሪ ፍተሻ እና የቁጥጥርና ፍተሻ ስራ 0 ነጥብ 111 ሜትሪክ ቶን ዘይት፣ 3 ነጥብ 35 ቶን ኤል ኢ ዲ አምፖል፣ 2 ነጥብ 76 ቶን የኤሌክትሪክ ገመድ፣ 54 ነጥብ 51 ቶን የታሸገ ሩዝ እና 257 ነጥብ 1 ቶን የስንዴ ዱቄት ከደረጃ በታች ሆነው በመገኘታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡