Get Mystery Box with random crypto!

በ158 ወረዳዎች የስንዴ ዋግ በሽታ መከሰቱን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የስንዴ ዋግ በሽታው | ሰሌዳ | Seleda

በ158 ወረዳዎች የስንዴ ዋግ በሽታ መከሰቱን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የስንዴ ዋግ በሽታው በተለይም ስንዴ አብቃይ በሆኑ ክልሎች በደቡብ፣ በሲዳማ፣ በአማራ፣ በቤንሻጉል ጉምዝ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች በአጠቃላይ ከ399 ሺሕ ሄክታር መሬት በላይ በለማ ስንዴ ላይ የተከሰተ መሆኑን ነው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያሳወቀው። በሽታውን ለመከላከል እስካሁን 308 ሺሕ ሊትር የኬሚካል ርጭት መካሄዱን የተገለፀ ሲሆን ሆኖም የኬሚካሉ ዋጋ መወደድ በአርሶ አደሮች ላይ ጫና ሳይፈጥር እንዳልቀረ ተጠቁሟል።

በሽታው በምርት ላይ የሚያደርሰውን የጉዳት መጠን ለመለየት ጥናት እየተደረገ ሲሆን ይህም የመስክ ባለሙያዎች ጥናቱን ሲጨርሱ የሚታወቅ ይሆናል ተብሏል። ከኬሚካል ርጭቱ ባለፈ በሽታ ሊቋቋሙ የሚችሉ የስንዴ ዝርያዎችን አርሶ አደሩ እንዲጠቀም በመደረጉ የጉዳት መጠኑን ሊያቀለው እንደቻለ ተመላክቷል። በምርት ዘመኑ በመኸር ምርት ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይገኛል መባሉ የሚታወስ ነው።

ምንጭ - አዲስ ማለዳ