Get Mystery Box with random crypto!

ሜታ ኩባንያ በዚህ ሳምንት በርካታ ሰራተኞቹን እንደሚያባርር ተነገረ። የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜ | ሰሌዳ | Seleda

ሜታ ኩባንያ በዚህ ሳምንት በርካታ ሰራተኞቹን እንደሚያባርር ተነገረ።

የፌስቡክ እናት ኩባንያ ሜታ በዚህ ሳምንት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ለማሰናበት አቅዷል ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን ጠቅሶ ዘግቧል። ሜታ በጥቅምት ወር ደካማ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ማስመዝገቡን አሳውቋል። በዚህ ዓመት ከግማሽ ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል የተባለ እሴት እንዳጣም ተናግሯል።

ሮይተርስ እንደዘገበው ውድቀቱ የመጣው ከቀዘቀዘው የአለም ምጣኔ ሀብት እድገት ፣ ከቲክ ቶክ ውድድር እንዲሁም ከአፕል ኩባንያ የግላዊነት ፖሊሲ ለውጦች ጋር ይያያዛል። የሜታ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ሰራተኞቹን የምጣኔ ሀብት ውድቀቱን እንዲያግዙም አስጠንቅቀዋል ።

ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን፣ ትዊተር እና ስናፕን ጨምሮ በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ ስራተኞቻቸውን ከስራ እያሰናበቱ ነወ። የዓለም ምጣኔ ሀብት እድገት በከፍተኛ የወለድ ተመኖች ፣የዋጋ ግሽበት እና በኃይል ቀውስ ሳቢያ እየቀነሰ በመምጣቱ ቅጥርን ቀንሰዋል።