Get Mystery Box with random crypto!

ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ | ሰሌዳ | Seleda

ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ስንዴ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ከላኪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጿል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፥ ኢትዮጵያ የእርዳታ ስንዴ ከማስገባት አልፋ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ስንዴ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ወደ ውጭ የሚላከው ስንዴ ከሀገር ውስጥ ፍጀታ የተረፈ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ለዚሁ ይረዳ ዘንድ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ላኪዎችም በፊት ኢትዮጵያ የነበራት ገጽታ ተቀይሮ ከስንዴ አስመጪነት ወደ ላኪነት መሸጋገሯ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው የተጣለባቸውን ሀገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑ መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡