Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 147

2022-11-06 15:03:18
የታንዛንያዉ አዉሮፕላን በቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ተከሰከሰ።

በታንዛንያ ትልቁና የግል ባለሀብቶች ንብረት የሆነዉ ፕሪስዥን አዉሮፕላን 39 ተሳፋሪዎችን፣ ሁለት አብራሪዎችንና ሁለት የበረራ አባላት ባጠቃላይ 43 ሰዎችን በመያዝ በቪክቶሪያ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኝ አየር ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሐይቁ ዉስጥ መዉደቁ ተገልጿል፡፡

መነሻዉን ታንዛኒያ ዳረሰላም አድርጎ ስበር የነበረዉ አዉሮፕላኑ በ1 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ ባጋጠመዉ ችግርና አስቸጋሪ አየር ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖ ወደ ሐይቁ ወድቋል ነዉ የተባለዉ፡፡ በአዉሮፕላኑ ላይ ከተሳፈሩት 26 ሰዎችን በማግኘት ወደ ሆስፒታል ማድረሳቸዉን የጠቀሱት የአከባቢዉ የፀጥታ አካላት አሁንም የፍለጋዉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን በጉዳቱ ሞት ስለመኖሩ የገለፁት ነገር የለም፡፡

በአደጋዉ ማዘናቸዉን የገለፁት የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሴን የህይወት አድን ስራዉን የሚሰሩ አካላት ስራቸዉን በአግባቡ እንዲሰሩ በፀሎት ማገዝ ያስፈልጋል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
5.8K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 13:40:40
ኅብረተሰቡ በሰማያዊ ፕላስቲክ የታሸገ ውኃ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር የታሸጉ ውኃ አምራቾች ይጠቀሙበት የነበረውን የውኃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙስ ማቅለሚያ (ማስተርባች) በማቆማቸው፣ ኅብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ በነጭ የውኃ ማሸጊያ ብቻ ያሉ ምርቶችን መጠቀም እንዳለበት የኢትዮጵያ ቤቨሬጅስ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር አስታውቋል፡፡

ይህ የተባለው የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌትነት በላይ (ኢንጂነር) ሐሙስ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲሆን ከዚዘዝም በተጨማሪ የታሸገ የውኃ ዋጋን ለመቀነስ ከሽያጭ ላይ ተሰብስቦ የሚከፈለውን አሥር በመቶ ኤክሳይስ ታክስ የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያነሳ መጠየቁን አንስተዋል፡፡

የታሸጉ ውኃ አምራቾች ሲጠቀሙበት የነበረውን የውኃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙስ ማቅለሚያ (ማስተርባች) በማስቀረቱ፣ አምራቾች ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ሲጠቀሙበት የነበረውን በዓመት ውስጥ እስከ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ወጪ እንደሚያስቀር ጌትነት (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡

via - reporter
5.8K views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 12:02:02
ኢት ስዊች ሁሉንም ባንክች የሚያካትት አዲስ የሳይበር ደህንነት ማዕከልን መጠቀም ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

ሁሉም ባንኮች በአንድ ቋት የሚጠቀሙበት አዲሱ ማዕከል የክፍያ ስርአት የሚሳለጥበትና ነገር ግን የሳይበር ጥቃት የሚደርስበትን የፋይናንስ ዘርፍን ከጥቃት ለመከላከል እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡ ይህም ኢት ስዊች ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር ገቢራዊ የሚደርገው መሆኑ ታውቋል፡፡

የኢት ስዊች አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ይለበስ አዲስ የማዕከሉ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በኢንተር ሌክዠሪ ሆቴል ይፋ ሲደረግ የማዕከሉ መመስረት የፋይናንስ ዘርፉ በተበታተነ መንገድ የሳይበር ደህንነት ከማስጠበቅ ይልቅ በአንድ ወጥ አሰራር የሁሉንም ባንኮች የሳይበር ደህንነት ማስተበቅ ያስችላል ብለዋል፡፡

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
5.9K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 10:03:15
የኬንያ አየር መንገድ በረራ ማቆሙ ተነገረ።

የኬንያ መንግሥት ንብረት የሆነው የኬንያ አየር መንገድ ትላንት የዓለማቀፍ እና የአገር ውስጥ በረራዎችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አቋርጦ ውሏል። አየር መንገዱ በረራዎቹን ለማቋረጥ የተገደደው፣ የአውሮፕላን አብራሪዎችና ሌሎች ሠራተኞች የሠራተኛ ማኅበር "የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄያችን አልተመለሰም" በማለት ከትናንት ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ በመጥራቱ ነው።

መንግሥት አድማው "የኢኮኖሚ አሻጥር ነው" በማለት፣ አድመኞቹ ባስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲመለሱ አሳስቧል። አየር መንገዱ በበኩሉ በሃያ አራት ሰአታት ውስጥ ሰራተኞቹ ወደ ስራ ካልተመለሱ የዲሲፕሊን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቋል።

ራሱን የግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተፎካካሪ አድርጎ ይቆጥር የነበረው የኬንያ አየር መንገድ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ በመግባቱ፣ መንግሥት በሚመድብለት ከፍተኛ ድጎማ መንቀሳቀስ ከጀመረ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል።

via - citizen tv kenya
6.2K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 07:28:48
ለውጭ ባንኮች የሚሰጠው የባንክ ሥራ ፈቃድ በቁጥር የተገደበ እንደሚሆን ታወቀ

መንግሥት ባፀደቀው ፖሊሲና ይህንን ተከትሎ በተረቀቀው የባንክ ሥራ አዋጅ ማሻሻያ መሠረት፣ ለውጭ ባንኮች የሚሰጠው የባንክ ሥራ ፈቃድ በቁጥር የተገደበ እንደሚሆንና ለሚመጡት የውጭ ባንኮች በሙሉ ፈቃድ የሚሰጥ እንዳልሆነ ሪፖርተር ዘግቧል።

ይልቁንም ልክ የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ውድድር ክፍት ሲያደርግ፣ ለሁለት የውጭ ቴሌኮም ኩባንያዎች ብቻ ፈቃድ ለመስጠት እንደወሰነው ሁሉ፣ የባንክ ዘርፉንም ለውጭ ውድድር ክፍት ሲያደርግ ለመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት ፈቃድ የሚሰጠው ለተወሰኑ የተመረጡ የውጭ ባንኮች እንደሚሆን ዘገባው አክሏል። 

‹‹አዲስ ፈቃድ ከመስጠት አንፃር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ከሦስት እስከ አምስት ፈቃድ ለውጭ ባንኮች ሊሰጥ ይችላል። በተመሳሳይ ቅርንጫፍ መክፈት ለሚፈልጉ ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ የውጭ ባንኮች ብቻ ሆኖ፣ እያንዳንዳቸው መክፈት የሚችሉት የቅርንጫፍ ብዛትም ከሁለት እስከ አራት ቅርንጫፎችን ብቻ ይሆናል›› ሲል ሪፖርተር ያገኘው የፖሊሲ ሰነዱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ነገር ግን ብሔራዊ ባንክ ከአምስት ዓመታት በፊት ወይም በኋላ በልዩ ሁኔታ አጢኖ ተጨማሪ የንዑስ ባንክ ወይም ቅርንጫፍ ፈቃድ እንዲሰጥ ሊወስን እንደሚችል የፖሊሲ ሰነዱ ይገልጻል። በተጨማሪም የውጭ ዜግነት ያለው የባንክ ሠራተኛ ፖለቲካ ላይ ተሳትፎ ከተገኘ ይሰናበታልም ተብሏል።

via - reporter
6.8K views04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 19:06:27
አይኤምኤፍ (IMF) በኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት መደረጉን ተከትሎ ቀጣይ ፈንድ ለመልቀቅ እያሰበ መሆኑን አስታወቀ።

ብሉምበርግ እንደዘገበው የድርጅቱ የፈንድ ጉዳይን የሚከታተሉ ባለሙያዎች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ውይይት እያረጉ መቆየታቸውን አስታውሶ ይህም አዲስ የፈንድ ፕሮግራም ለማሳካት ያስችላል ብሏል። "ቀጣይ እርምጃዎችን እያሰብን ሲሆን ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንወያያለን" ብሏል ተቋሙ።

ኢትዮጵያ ያለባትን 30 ቢልዮን ዶላር ብድር ለማስተካከል ውይይት ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ የ1 ቢልዮን ዶላር ዩሮቦንድ ሽያጭ ከፍ እንዳለ የተሰማ ሲሆን ይህም ከባለፉት ሶስት ወራት ዲህ ከፍተኛው ጭማሪ ነው ተብሏል። በሰላም ድርድሩ የተነሳ በቀጣይም ኢትዮጵያ ከአጎዋ ተጠቃሚነት የተሰረዘችበት እገዳ እንደሚነሳ ብዙዎች ተስፋ አድርገዋል።

via - Elias Meseret
7.1K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 15:04:30
ኢትዮጵያ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች። 

እ.አ.አ በ2021 ከአፍሪካ ለውጭ ገበያ ከተላከው ቡና 2.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በዚህም ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ፣ ኮትዲቯር፣ ታንዛኒያ እና ኬኒያ አምስቱ ከፍተኛ ቡና ላኪ የአፍሪካ ሀገራት ሆነዋል። ኢትዮጵያ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ከቡና በማግኘት ገበያውን ስትመራ፣ ዩጋንዳ ደግሞ 594.2 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት ትከተላለች።

የቡና መገኛ ከሆነችው አፍሪካ የሚገኙ የቡና ፍሬዎች በልዩ ጣዕማቸው፣ በአሲድ መጠናቸው ተስማሚነት እና በአስደሳች መዓዛቸው በዓለም ቡና ተጠቃሚዎች ዘንድ ይመረጣሉ። ከሌላው ዓለም በተሻለ ብዙ ቡና አምራች ሀገሮች ያሉባት አህጉርም አፍሪካ ናት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ የቡና ተጠቃሚዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ሲሆን እ.አ.አ ከ2021 እስከ 2022 የዓለም ቡና ፍጆታ 170.3 ሚሊዮን ባለ 60 ኪ.ግ ከረጢት መድረሱን የዓለም አቀፉ የቡና ድርጅት ገልጿል።

ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኢ-ኮሜርስ ንግድ ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን፣ ይህ ስምምነትም የአፍሪካ ሀገራት ቡናን ጨምሮ ሌሎች ምርቶቻቸውን ወደ ቻይና እንዲልኩ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

via - ebc
2.8K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 13:20:13
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንጻ መኖሪያ የሕብረት ስራ ማህበር አሰራርና አደረጃጀት ደንብ ስራ ላይ ዋለ፡፡

የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ችግር ለመቅረፍ በሚል የመንግስት ሰራተኞች በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ሰራተኞችን በማደራጀት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስተዳደሩ ከሊዝ ነፃ የሆነ የመሬት ዝግጅት በማቅረብ ዕድሉን ያመቻቸ ሲሆን ይህንኑ ተግባር የሚመራበትን የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንፃ መኖርያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር  የአደረጃጀትና አፈፃፀም ደንብ ቁጥር 129 /2014 በከተማው ካቢኔ ፀድቆ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ አሳውቋል።
3.6K views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 11:34:40
ሩሲያ ስንዴዋን ለድሃ የአፍሪካ ሀገራት በነጻ ልትሰጥ እንደሆነ ተገለጸ።

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ኤርዶሃን ከሩሲያ አቻቸው ቭለድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ሩሲያ በነጻ ስንዴዋን ወደ ድሃ ሀገራት ለማጓጓዝ መስማማቷ ተገልጿል።

የሩሲያን ስንዴ በነጻ ከሚሰጣቸው ሀገራት መካከልም ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን የተጠቀሱ ሲሆን ሀገራቱ የምግብ ችግር እንዳለባቸውም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። በተመድ እና ቱርክ አደራዳሪነት በጥቁር ባህር የጉዞ እና የንግድ መስመር ላይ ከ10 ሚሊዮን በላይ ቶን ስንዴ መጓጓዙ ተገልጿል።

via - Alain
4.4K views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 10:04:19
በ2030 ቻይና የአለም ኢኮኖሚ ቁንጮ ልትሆን እንደምትችል አይ ኤም ኤፍ ጠቆመ።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ.) ሊጠናቀቅ የተቃረበውን የፈረንጆቹን አመት የአለም የኢኮኖሚ ድርሻ በጥናቱ ይፋ ሲያደርግ አሜሪካ አሁንም ትልቁን ድርሻ ይዛለች። በአለም ላይ የተፈጠረው ግጭትና ግርግር እንዲሁም የዋጋ ንረት የዓለም ኢኮኖሚን ወደ 104 ትሪሊዮን ዶላር ከፍ እንዳደረገው ተቋሙ ገልጿል።

እንደ ተቋሙ ጥናት ከሆነ ከመቶ ትሪሊዮን የአለም ኢኮኖሚ አሜሪካ አንድ አራተኛውን ($25.3 ትሪሊዮን) ስትይዝ በቅርብ ርቀት የምትከተላት ቻይና $19.9 ትሪሊዮን ጂዲፒ ማስመዝገቧን አሳውቋል። አሜሪካ የአለም ኢኮኖሚን ከ1871 ጀምሮ በበላይነት ስትመራ መቆየቷን ያነሳው ጥናቱ ይህ ግን ማብቂያው እየተቃረበ ስለመሆኑ ጠቁሟል። ነገሮች በዚሁ ሁኔታ ሚቀጥሉ ከሆነ በ2030 መሪነቱን በቻይና ልትነጠቅ እንደምትችል ነው ያሳወቀው።

ጥናቱ አክሎም በአመቱ አየርላንድ ከአውሮፓ በጣም ፈጣን የተባለውን የኢኮኖሚ እድገት በ5.2 በመቶ ስታስመዘግብ እንደ ቱቫሉ ያሉ የእስያ ክልሎች ደግሞ ዝቅተኛ ጂዲፒን አስመዝግበዋል።

via - IMF
4.9K views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ