Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች።  እ.አ.አ በ2021 ከአፍሪካ ለውጭ | ሰሌዳ | Seleda

ኢትዮጵያ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች። 

እ.አ.አ በ2021 ከአፍሪካ ለውጭ ገበያ ከተላከው ቡና 2.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በዚህም ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ፣ ኮትዲቯር፣ ታንዛኒያ እና ኬኒያ አምስቱ ከፍተኛ ቡና ላኪ የአፍሪካ ሀገራት ሆነዋል። ኢትዮጵያ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ከቡና በማግኘት ገበያውን ስትመራ፣ ዩጋንዳ ደግሞ 594.2 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት ትከተላለች።

የቡና መገኛ ከሆነችው አፍሪካ የሚገኙ የቡና ፍሬዎች በልዩ ጣዕማቸው፣ በአሲድ መጠናቸው ተስማሚነት እና በአስደሳች መዓዛቸው በዓለም ቡና ተጠቃሚዎች ዘንድ ይመረጣሉ። ከሌላው ዓለም በተሻለ ብዙ ቡና አምራች ሀገሮች ያሉባት አህጉርም አፍሪካ ናት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ የቡና ተጠቃሚዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ሲሆን እ.አ.አ ከ2021 እስከ 2022 የዓለም ቡና ፍጆታ 170.3 ሚሊዮን ባለ 60 ኪ.ግ ከረጢት መድረሱን የዓለም አቀፉ የቡና ድርጅት ገልጿል።

ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኢ-ኮሜርስ ንግድ ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን፣ ይህ ስምምነትም የአፍሪካ ሀገራት ቡናን ጨምሮ ሌሎች ምርቶቻቸውን ወደ ቻይና እንዲልኩ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

via - ebc