Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንጻ መኖሪያ የሕብረት ስራ ማህበር አሰ | ሰሌዳ | Seleda

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንጻ መኖሪያ የሕብረት ስራ ማህበር አሰራርና አደረጃጀት ደንብ ስራ ላይ ዋለ፡፡

የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ችግር ለመቅረፍ በሚል የመንግስት ሰራተኞች በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ሰራተኞችን በማደራጀት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስተዳደሩ ከሊዝ ነፃ የሆነ የመሬት ዝግጅት በማቅረብ ዕድሉን ያመቻቸ ሲሆን ይህንኑ ተግባር የሚመራበትን የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንፃ መኖርያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር  የአደረጃጀትና አፈፃፀም ደንብ ቁጥር 129 /2014 በከተማው ካቢኔ ፀድቆ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ አሳውቋል።