Get Mystery Box with random crypto!

የኬንያ አየር መንገድ በረራ ማቆሙ ተነገረ። የኬንያ መንግሥት ንብረት የሆነው የኬንያ አየር መን | ሰሌዳ | Seleda

የኬንያ አየር መንገድ በረራ ማቆሙ ተነገረ።

የኬንያ መንግሥት ንብረት የሆነው የኬንያ አየር መንገድ ትላንት የዓለማቀፍ እና የአገር ውስጥ በረራዎችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አቋርጦ ውሏል። አየር መንገዱ በረራዎቹን ለማቋረጥ የተገደደው፣ የአውሮፕላን አብራሪዎችና ሌሎች ሠራተኞች የሠራተኛ ማኅበር "የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄያችን አልተመለሰም" በማለት ከትናንት ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ በመጥራቱ ነው።

መንግሥት አድማው "የኢኮኖሚ አሻጥር ነው" በማለት፣ አድመኞቹ ባስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲመለሱ አሳስቧል። አየር መንገዱ በበኩሉ በሃያ አራት ሰአታት ውስጥ ሰራተኞቹ ወደ ስራ ካልተመለሱ የዲሲፕሊን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቋል።

ራሱን የግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተፎካካሪ አድርጎ ይቆጥር የነበረው የኬንያ አየር መንገድ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ በመግባቱ፣ መንግሥት በሚመድብለት ከፍተኛ ድጎማ መንቀሳቀስ ከጀመረ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል።

via - citizen tv kenya