Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 141

2022-11-17 19:44:08
በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማእከል ሰራተኞችና በአስተዳደር አካሉ መካከል የተፈጠረው ችግር መፈታቱን ድርጅቱ ገለፀ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን "የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች በሚያስተዳድረው ድርጅት (ISON Xperience) እና በሳፋሪኮም ሠራተኞች መካከል የተፈጠረው የአለመግባባት ተፈትቶ ሰራተኞቹ መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴያቸውን መቀጠላቸውን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ድርጅቱ "በዚህ ወቅት በደንበኞች አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል እንዳይፈጠር እና ደንበኞች እንደቀድሞው እንዲስተናገዱ አስፈላጊው ዝግጅቶች ማድረጉን አዲስ ዘይቤ ዘግባለች።
6.3K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 16:27:40
የአማራ ክልል የሚሰጥ የኢንቨስትመንት መሬት ታገደ።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለን በከተማ ዙሪያ የሚሰጥ የኢንቨስትመንት መሬት ከከተሞች ፕላን ጋር የማይጠረስ መሆኑ ተረጋግጦ ለክልሉ የኢንቨስትመንት ቦርድ ሳይቀርብ እንዳይሰጥ ሲሉ በደብዳቤ አግደዋል።

በከተማ ዙሪያ የሚሰጥ የኢንቨስትመንት መሬት ጋር በተያያዘ በክልሉ ከፍተኛ ችግር መከሰቱን የገለፁት ርዕሰ መስተዳደሩ “በትልልቅ ከተሞች የሚገኝ ወረዳን የሚገኝበትን ከተማ ከማልማት ይልቅ ከፍ ወዳሉ ከተሞች የሚገኝ መሬትን ከፕላን ውጭ መውረር እንዲሁም ከተማና ከከተማ ዙሪያ ብቻ የሚገኝ መሬትን በስጦታ እያስተላለፉ ህጉ ለሚፈቅደውም ሆነ ለማይፈቅድለት የመሬት ባለቤትነት ደብተር ማደል" ዋነኛ ችግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል።

via - addis zeybe
922 views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 14:11:16
በኢትዮ- ኬኒያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዛሬ በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ተጀምሯል።

የኢትዮ- ኬኒያ ባለ 500 ኪል ቮሌት የኃይሌ ማስተላለፊያ መስመር እና የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ በይፋ የኤላክትሪክ ሽያጭ ጀምሯል፡፡
2.8K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 11:21:07
የስቲቭ ጆብስ ያረጀ ጫማ በ 218,000 ዶላር በጨረታ መሸጡ ተሰማ።

አሜርካዊ ቢለየነር ስቲብ ጆብስ በህይወቱ ዘመኑ ያጠለቀው ጥልፍልፍ አሮጌ ጫማ እሁድ በኒው ዮርክ ሲቲ በተደረገ የጫረታ ሽያጭ በ218,750 የአሜሪካ ዶላር ተሸጠዋል።

ከቅርብ ዓመታት በፊት ከጆብስ ጋር የተያያዙ ሌሎች ዕቃዎችም በጨረታ ተሽጠዋል። ግን እንዳሁኑ ባይጋነንም በተመሳሳይ በከፍተኛ ዋጋ የተሸጡ ነበሩ።
4.4K views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 11:01:43
ባለፉት 20 ዓመታት የአዕምሯዊ ንብረት የምስክር ወረቀት ያገኙ የፈጠራ ሥራዎች 103 ብቻ እንደሆኑ ተነገረ

ባለፉት 20 ዓመታት ዓለም ዐቀፍ የማጣራት ሂደትን አልፈው የአዕምሯዊ ንብረት ሰርተፍኬት እንዲያገኙ ማመልከቻ ከቀረበባቸው 671 የፈጠራ ሥራዎች መካከል እስካሁን ዓለም ዐቀፍ የማጣራት ሂደቶችን ያለፉት 103 የፈጠራ ሥራዎች ብቻ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

እስካሁን የምስክር ወረቀቱ ካልተሰጣቸው 568 የፈጠራ ሥራዎች መካከልም ውድቅ የተደረጉ፣ የማጣራት ሂደታቸው በመካሄድ ላይ የሚገኙ እንዲሁም የማጣራት ሂደታቸው ተጠናቅቆ የምስክር ወረቀቱን ለመስጠት በሂደት ላይ የሚገኙ የፈጠራ ሥራዎች እንደሚገኙ የገለጹት ታምሩ፣ ዓለም ዐቀፍ የማጣራት ሂደቶች ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
4.3K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 08:03:16
የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከተቋሙ የሚለቅቁ ሰራተኞች ብዛት አሳሳቢ እንደሆነ ገለጸ።

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት፤ በደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ምክንያት ሰራተኞቹ ከተቋሙ እየለቀቁ መሆኑን የመስሪያ ቤቱ ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ ትላንት የተቋማቸውን የ2015 ዕቅድ እና የሩብ ዓመት አፈጻም ሪፖርት ለተወካዮች ምክር ቤት ለመንግስት ወጪ አስተዳዳር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።

መሰረት በዚሁ ሪፖርታቸው በተቋሙ ዓመታዊ የሰራተኞች ከስራ የመልቀቅ ምጣኔ 12.4 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።  ባለፈው ሩብ ዓመት ብቻ፤ 21 ሰራተኞች ከመስሪያ ቤታቸው መልቀቃቸውን ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ተናግረዋል።

አክለውም መስሪያ ቤቱን ከለቀቁ ሰራተኞች ሶስቱ ብቻ በጡረታ የተገለሉ መሆናቸው የጠቀሱት መሰረት፤ “አብዛኛዎቹ ምክንያታቸው የተሻለ ደመወዝ ነው” ሲሉ ቀሪዎቹ ለስራቸው ከፍ ያለ ክፍያ ወደሚከፍሉ፤ እንደ ባንክ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወዳሉ ተቋማት በየጊዜው እንደሚሄዱ አስረድተዋል።

via - Ethiopia insider
5.1K views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 07:12:00
ልዩ-ዕድል ሎተሪ ትላንት በህዝብ ፊት ወጥቷል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ልዩ-ዕድል ሎተሪን ዕሮብ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም በህዝብ ፊት አውጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች በምስሉ ላይ ተያይዟል። ይመልከቱት
5.0K views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 15:14:58
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንደስትሪ ቡድን አዲስ የስኳር ግዥ ጨረታ ከፈተ

በቅርቡ በተደረገው ዓለምአቀፍ ጨረታ ዝቅተኛ ዋጋ ሰጥቶ የነበረው ድርጅት የሥራ መፈፀም አቅምን የሚያረጋግጥ (ፐርፎርማንስ ቦንድ) ማቅረብ ባለመቻሉ በጉጉት የሚጠበቀውን ስኳር ግዥ በወቅቱ መፈጸም እንዳልተቻለ ካፒታል ዘግቧል።

በመሆኑም የስኳር ኢንደስትሪ ቡድኑ/ግሩፕ ሌላ ጨረታ ለማውጣት መገደዱ ነው የተገለጸው፡፡ ከሳምንት በፊት ውስን ዓለምአቀፍ ጨረታ የወጣ ሲሆን ባሳለፍነው ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን በጨረታው የተሳተፉ 3 ኩባንያዎች የቴክኒክ ሰነድ ተከፍቷል፡፡

በ2014 በጀት አመት የቀድሞው ስኳር ኮርፖሬሽን አሁን ቡድን  እየተባለ የሚጠራው የመንግስት የልማት ድርጅት 200 ሺ ሜትሪክ ቶን ስኳር ከውጭ ለመግዛት ተደጋጋሚ ጨረታ ቢያወጣም ግዥ መፈፀም ሳይችል ቀርቷል፡፡

via - capital
7.2K views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 14:51:20
የሳፋሪኮም ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰማ።

የቴሌኮም ፍቃድ በማግኘት በቅርቡ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ስራ የጀመረው ሳፋሪኮም በትላንትናው እለት በሰራተኞቹ የስራ አድማ እንደተደረገበት ታውቋል።

የስራ አድማው መነሻ ከሰራተኛ መብት አስተዳደር ጋር የተያያዘ መሆኑን የገለፁልን ሰራተኞቹ ድርጅቱ በደምወዝ እንዲሁም በተለይ ሌሊት እና ምሽት ላይ በሽፍት ለሚሰሩ ሰራተኞቹ የተሽከርካሪ ሰርቪስ አገልግሎት ማቅረብ አለመቻሉ ከፍተኛ እንግልት እንደፈጠረባቸው በመግለፅ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለካምፓኒው ጥያቄ ባቀረቡ አባላት ላይ መፍትሄ ከማበጀት ይልቅ በምትኩ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እያደረሰባቸው በመሆኑ የድርጅቱ የጥሪ ማእከል (call center) ጨምሮ የሲም አክቲቬሽን ላይ የሚሰሩ ሰራተኞቹ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ መገደዳቸውን ገልፀዋል።
6.9K viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 14:19:43
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሦስተኛ ደረጃ ሕክምና ለሚሰጡ የጤና ተቋማት ብድር ሊሰጥ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና በውጭ ሀገራት የሚሰጡ የሦስተኛ ደረጃ የሕክምና አገልግሎቶችን በሀገር ውስጥ መስጠት ለሚችሉ የጤና ተቋማት ብድር መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ሦስተኛ ደረጃ (ተርሸሪ ሌቭል) ሆስፒታል ዘመናዊ መሣሪያዎችን አካቶ የተሟላ አገልግሎት ለታካሚዎች የሚሰጥ ሲሆን ከሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ሆስፒታሎች በሪፈር የሚላኩ ታካሚዎችን ተቀብሎ አገልግሎት የሚሰጥ ጤና ተቋም ነው።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት ባንኩ በርካታ ገንዘብ የሚጠይቁና በውጭ የሚደረጉ የሕክምና አገልግሎቶች በሀገር ውስጥ እንዲጀመሩ ለማስቻል የሦስተኛ ደረጃ ሕክምና የሚሰጡ ተቋማትን ለመደገፍ ተዘጋጅቷል፡፡ በዘርፉ ድጋፍ ለማግኘት ጥያቄ ያቀረቡ መኖራቸውን እና ፕሮጀክቱን በቀጣዮቹ አራት ወራት ለማፅደቅ መታቀዱን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
6.6K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ