Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እየተቸገረ መሆኑን ገለፀ። የ | ሰሌዳ | Seleda

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እየተቸገረ መሆኑን ገለፀ።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እየተቸገረ መሆኑን መናገሩን ሪፖርተር ዘግቧል። አስተዳደሩ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለተቋራጮች መክፈል የነበረበትን 10 ቢሊዮን ብር መክፈል ባለመቻሉ፣ ተቋራጮች የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን እንዳቋረጡ ዘገባው ጠቅሷል።

ከ200 የፌደራል መንገድ ፕሮጀክቶች መካከል፣ 60 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በጸጥታ መጓደል ሳቢያ እንደተቋረጡ አስተዳደሩ መግለጹን ዘገባው ጨምሮ ገልጧል። አስተዳደሩ ይህን የገለጠው፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።