Get Mystery Box with random crypto!

8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀመረ። ለአራ | ሰሌዳ | Seleda

8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀመረ።

ለአራት ቀናት የሚቆየው ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት 8ኛው አፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በስካይ ላይት ሆቴል ተጀምሯል።በንግድ ትርዒቱ የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና የቴክኖሎጂ ምርቶች ለእይታ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

የንግድ ትርዒቱን  የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ አምራቾች ማህበር ከመሴ ፍራንክፈርት ግሩፕ ጋር በመተባበር  ነው ያዘጋጁት፡፡ ከ30 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ዓለም አቀፍ አምራቾች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒቱ አምራቹን በዓለም ዙሪያ ካሉ በርካታ የንግድ ባለሙያዎች እና ግብዓት አቅራቢዎች ጋር እንደሚያገናኝ ታምኖበታል።