Get Mystery Box with random crypto!

ከፍተኛ የዋጋ ንረት የታየባቸው የአለም ሀገራት ደረጃ ይፋ ሆነ። በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆ | ሰሌዳ | Seleda

ከፍተኛ የዋጋ ንረት የታየባቸው የአለም ሀገራት ደረጃ ይፋ ሆነ።

በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈረንጆቹ አመት 2022 ከፍተኛ የዋጋ ንረት የታየባቸውን የአለም ሀገራት ጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ዚምባቡዌ 393 በመቶ አመታዊ የዋጋ ንረት በማስመዝገብ ከአለም ሀገራት ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች።

ሌላኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ጋና በሁለተኝነት ስትከተል ኩባ፤ ቱርክና ስሪላንካ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል። እንደ ዩንቨርስቲው ጥናት ከሆነ በአለም ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ካስመዘገቡ ሃያ ሶስት ሀገራት አስራ አንዱ የአፍሪካ አገራት ናቸው።  ከስድስተኛ እስከ ሀያ ሶስተኛ ያሉትን በምስሉ ላይ ይመልከቱ።