Get Mystery Box with random crypto!

ህገወጦችን ህብረተሰቡ እንዲያጋልጥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ በከፍተ | ሰሌዳ | Seleda

ህገወጦችን ህብረተሰቡ እንዲያጋልጥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቆማ እየመጣ መሆኑ ታወቀ፡፡

ከሳምንታት በፊት ኢብባ ዜጎች በህገወጥ የምንዛሬ ገበያ፣ ህገወጥ ሃዋላ፣ ህገወጥ የወርቅ ንግድ፣ የህገወጥ የገንዘብ ህትመት የሚያከናውኑ አካላትን ለሚጠቁም ወሮታ እንዳዘጋጀ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ የመጠቆሚያ ዘዴዎችን ያስተዋወቀ ሲሆን ጥቆማ እየደረሰው መሆኑን ካፒታል ከባንኩ ምንጮች ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡፡ ስለጉዳዩ የመግለጽ ሃላፊነት የሌላቸው አንድ ሃላፊ እንዳሉት ከኢብባ ጥሪ በኋላ ጥቆማ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ማእከላዊ ባንኩ እየመጣ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

via - Ethiopian Business Daily