Get Mystery Box with random crypto!

በሀገረ ብራዚል የተጧጧፈው አዲስ 'የታማኝነት ፈተና' ስራ መነጋገሪያ ሆኗል። በብራዚል በማራኪ | ሰሌዳ | Seleda

በሀገረ ብራዚል የተጧጧፈው አዲስ "የታማኝነት ፈተና" ስራ መነጋገሪያ ሆኗል

በብራዚል በማራኪ ሴቶች ባሎች ለትዳራቸው ምን ያህል ታማኝ ናቸው በሚል የተጀመረው አዲስ "የታማኝነት ፈተና" ስራ ከብራዚል አልፎ አለምን እያነጋገረ ይገኛል። የብራዚል ታማኝነት ተቆጣጣሪዎች (loyalty inspectors) እንደ ቲክ ቶክ እና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ የሚዲያ አውታሮች ተፈላጊነታቸው እየጨመረ መጥቷል።

ብዙውን ጊዜ ወጣት እና ማራኪ ሴቶች በመጠቀም ስራው የሚከናወን ሲሆን ባሎቻቸውን ለመፈተን የሚፈልጉ ሚስቶች ከ4 ዶላር እስከ 30 ዶላር መክፈል ይጠበቅባቸዋል። እነዚሁ የታማኝነት ተቆጣጣሪ ሴቶች በዋትስአፕ እና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ በኩል ወንዶቹን ማውራት ይጀምራሉ።

በንግግራቸው እና የተለዋወጡትን ፎቶዎች በማስረጃ በማያያዝ ለሚስቶች ያስረክባሉ። በዚሁ የታማኝነት ፈተና በቻይና በ2021 ዓመት ለመፈተን የሄደት አንዲት ግለሰብ ከተፈታኙ ጋር በፍቅር ወድቀው ከትዳር አጋሩ ጋር የተለያየበት አጋጣሚ ነበር።