Get Mystery Box with random crypto!

ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ወደ ባንክ ራሳቸውን እንዲያሳድጉ  ጥሪ | ሰሌዳ | Seleda

ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ወደ ባንክ ራሳቸውን እንዲያሳድጉ  ጥሪ አቀረበ።

ባንኩ ጥሪውን ያቀረበው በአለም አቀፍ ደረጃ ለ74ኛ ጊዜ ፤ በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እና በአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለ5ኛ ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ቀን "የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ለተጠናከረ የፋይናንስ አቅም" በሚል መሪ ቃል በተከበረበት ወቅት ነዉ።

ባለፉት አራት አመታት የፋይናንስ ዘርፉ በእጥፍ ቢያድግም ካለው ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ መሆን እንዳልቻለ የብሔራዊ ባንክ ም/ል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል። ብሔራዊ ባንክ አካታች የፋይናንስ ስርአት ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰለሞን የብሔራዊ ዲጂታል ክፍያ ስርአትን ጨምሮ ሌሎች ስትራቴጂዎችን ቀርጾ ወደ ስራ መግባቱን አስታውሰዋል።

አቶ ሰለሞን አክለውም ማህበራቱ ወደ ባንክ እና ኢንሹራንስ የማደግ ፍላጎት ካላቸው በብሔራዊ ባንክ በኩል ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጁነት መኖሩን አረጋግጠዋል። ፍላጎት ያላቸው ማህበራት ለብሔራዊ ባንክ ፍላጎታቸውን በመግለጽ እና መስፈርቶቹን በማሟላት ማደግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ