Get Mystery Box with random crypto!

አየር መንገዱ 'ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ' ሽልማት 2022 ተሸላሚ ሆነ። የኢትዮጵያ አየር | ሰሌዳ | Seleda

አየር መንገዱ "ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ" ሽልማት 2022 ተሸላሚ ሆነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን ሽልማት ከቢዝነስ ትራቭለር ሪደርስ አዋርድ ሲያገኝ ይህ ለተከታታይ ሦስተኛ ዓመት መሆኑን በይፉዊ የቲውተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመስከረም ወር 2015 በለንደን SKYTRAX 2022 የአለም ምርጥ አየር መንገዶች ሽልማት ላይ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ በመባል መሸለሙ ይታወሳል። በዚሁ SKYTRAX ምርጥ የአለማችን 100 አየር መንገዶች ዝርዝር ውስጥም አስራ አንድ ደረጃዎችን በማሻሻል 26ተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ መቻሉ ተገልጿል።