Get Mystery Box with random crypto!

ከኅዳሴ ግድብ የሚመረተው ኃይል ወደ ዋናው ግሪድ እንዲገባ የሚካሄደው የመስመር ጥገና እና ፍተሻ ሥ | ሰሌዳ | Seleda

ከኅዳሴ ግድብ የሚመረተው ኃይል ወደ ዋናው ግሪድ እንዲገባ የሚካሄደው የመስመር ጥገና እና ፍተሻ ሥራ በቀጣይ ሣምንት ይጀመራል ተባለ።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚገኙ ከ30 በላይ ወረዳዎችን አቆራርጦ አዲስ አበባ እንደሚገባም ነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። በዚህ ርቀት ውስጥ በሚሰሩ ሥራዎች የክልሎቹ የጸጥታ ኃይሎች እና መላው ነዋሪ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጠይቋል።

በሌላ በኩል የኢትዮ ኬንያ የኤሌክትሪክ የኃይል ሽያጭን ለማከናወን ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናቶች የኃይል ሽያጩ ይጀመራል ተብሏል። በመጀመሪያው ሽያጭም 200 ሜጋ ዋት ኃይል ይቀርባል ነው የተባለው። የኃይል ግዢ ስምምነቱ ባለፈው ነሐሴ ወር መፈረሙ የሚታወስ ነው።

via - fbc