Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ 10 ወራት ዉስጥ 3 ሚሊዮን ደምበኞች ማግኘቱን አስታወቀ በመስከረም ወር | ሰሌዳ | Seleda

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ 10 ወራት ዉስጥ 3 ሚሊዮን ደምበኞች ማግኘቱን አስታወቀ

በመስከረም ወር መጨረሻ በአዲስአበባ አገልግሎት መስጠት የጀመረዉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን ሶስት ሚሊዮን ደምበኞች ማፍራቱን አስታውቋል።

በዛሬዉ እለትም ኩባንያዉ "ተረክ በጉርሻ" ሲል በሰየመዉ የደምበኞቹ እጣ ሽልማት መርሐግብር እድለኛ የሆኑ ተጠቃሚዎቹን ሸልሟል።

በ ሶስተኛ እና አራተኛ ዙር አሸናፊ የሆኑ ባለእድለኛ ደምበኞቹን አንድ ዘመናዊ የቤት መኪና ፣ አንድ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ፣ አንድ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተርሳይክል እና የተለያዩ የእጅ ሞባይል እና የታብሌት ሽልማቶችን ለባለእድለኛ ደምበኞቹ አበርክቷል።