Get Mystery Box with random crypto!

ከቱሪዝም ዘርፍ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ ባለፉት 9  ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ 3 ነጥብ | ሰሌዳ | Seleda

ከቱሪዝም ዘርፍ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

ባለፉት 9  ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ 3 ነጥብ 06 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስትሩ የውጭ ምንዛሪ ግኝትና የስራ ዕድሎችን በማስፋፋት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ የሆኑትን የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች (ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሀላላ ኬላ፣ ኮይሻ)፣ የጅማ አባጂፋር ቤተ-መንግስትና የስንቀሌ የቆርኬዎች መጠለያን በተሟላ መልኩ ወደ ስራ ለማስገባት በቅንጅት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡