Get Mystery Box with random crypto!

ዲቪ 2023 የደረሰን ሰዎች ሊቃጠልብን ነው» ባለ እድለኞች የ2023 የዲቪ ሎተሪ ባለዕድል ከሆ | ሰሌዳ | Seleda

ዲቪ 2023 የደረሰን ሰዎች ሊቃጠልብን ነው» ባለ እድለኞች

የ2023 የዲቪ ሎተሪ ባለዕድል ከሆኑት መካከል እስካሁን ኤምባሲው ለ123 ሰዎች ሂደቱን ጨርሶ ቪዛ እንደሰጠ፣ የ130 ሰዎች የቪዛ ጥያቄያቸው እየታየ መሆኑን እንዲሁም ሌሎች 130 ባለዕድሎች ደግሞ ሂደቱን መጀመራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ከ2761 ዕድለኞች ውስጥ ለ383 ሰዎች ብቻ ነው ሂደቱ የተጀመረላቸው ወይንም ያለቀላቸው። ኤምባሲው በወር ውስጥ እያስተናገደ ባለው የሰው ቁጥር መሰረት 2200 የሚሆኑት ሰዎች ዕድላቸው ወደ መቃጠል እየሄደ ነው” ይላል አቶ አያና የዲቪ 2023 እድለኛ ስጋቱን ሲገልፅ።

አቶ ሙሉቀን ጣሰው በበኩሉ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኛ መሆኑን ባወቀ ጊዜ እርሱም ሆነ ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸው እነደነበር ያስታውሳል።

የባንክ ማናጀር የነበረው ሙሉቀን የዲቪ እንደደረሰው ካወቀ በኋላ “ወደ አሜሪካ በቅርቡ እሄዳለሁ በሚል ተስፋ ሥራዬን ለቅቄ በግል ሥራ ላይ አትኩሬ ነበር” በማለት አሁን ግን ይህ ዕድል ወደ ሊቃጠል ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ መሆኑን ተናግሯል።

“አሁን አሁን ሳስበው ምናለበት የዲቪው ሎተሪው ባይወጣልኝ ብዬ እያሰብኩ ነው። ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ መቼ ነው የምትሄደው እያሉ ይጠይቁኛል። ይህ ዕድሌ ከተቃጠለ እዚህ ከተማ ውስጥ መኖር አልችልም” ይላል ሙሉቀን።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት በኮቪድ እና በሌሎች ችግሮች ምክንያት በርካታ ውዝፍ ሥራዎች ስለነበሩበት በሚፈለገው ሁኔታ የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞችን ለማስተናገድ እንዳልቻለ ገልጿል።

ለዲቪ ዕድለኞች የቪዛ መስጠት ሂደት “በአጭር ጊዜ ውስጥ በአስቸኳይ የሚከናወን ሥራ ስላልሆነ” በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ሁሉንም የዲቪ ዕድል አሸናፊዎች ማስተናገድ እንደማይቻልም ገልጿል።