Get Mystery Box with random crypto!

ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ታወቀ የኢትዮጵያ ‹‹የሰነደ ሙዓ | ሰሌዳ | Seleda

ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ታወቀ

የኢትዮጵያ ‹‹የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ›› ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ የመነሻ ካፒታል ያስፈልጋል መባሉን ሪፖርተር ጽፏል፡፡ ከገበያው መንግሥት 25 በመቶ የግል ኢንቨስተሮች ደግሞ 75 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል።

በ2016 ዓ.ም. ወደ ሥራ የሚገባው የሙዓለ ንዋይ ገበያው ትርፍ ለማስመዝገብ ከሦስት እስከ አራት ዓመታት እንደሚፈጅበት፣ በጥናት መታወቁን የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ለግል ኢንቨስተሮች አክሲዮን የመሸጥ ሥራ ማክሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ተጀምሯል፡፡