Get Mystery Box with random crypto!

9 ኛው የጉማ አዋርድ ዝግጅት በእስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው። በሀገራችን ኢትዮጵያ በኪነ | ሰሌዳ | Seleda

9 ኛው የጉማ አዋርድ ዝግጅት በእስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በኪነጥበብ ዘርፍ ላይ ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ጥበበኞች በመሸለም የሚታወቀው ጉማ አዋርድ ሰኔ 02/10/2015 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል የሰማያዊ ምንጣፍ ጉማ የፊልም ሽልማት እየተካሄደ ነው።

በዘንድሮ ጉማ አዋርድ ሽልማት የአርያ ሰብ ከያኒ በሚል ዘርፍ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ እየሠራች የምትገኘው እና በትወናው ዘርፍ በርከት ያሉ ስራዎችን ያበረከተችው አርቲስት መሠረት መብራቴ ልዩ ተሸላሚ እንደምትሆን እንዲሁም የህይወት ዘመን ተሸላሚ አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው አርቲስት ኪሮስ ሃይለስላሴ የሄርሜላ ተሸላሚ የአቢሲኒያ የስነ ጥበብ መስራች የሆኑት ወ/ሮ ገነት ከበደ ተሸላሚዎች መሆናቸው መገለፁ የሚታወስ ነው ።

በዘንድሮ የጉማ አዋርድ በ24 ዘርፎች በየዘርፋ 5 እጩዎችን አቅርቧል። የአንዳንድ አርቲስቶች ፎቶ ደግሞ መልክቱ ሃያል ነው።