Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-25 06:29:00
ስለ ገንዘቡ ምንጭ…

ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

﴿ليأتينَّ على الناس زمان ، لا يُبالي المرءُ بما أخذ المال : أمِنْ حلالٍ أم من حرام﴾

“አንድ ሰው ገንዘቡን ከሐላል ነው ወይስ ከሐራም የሚያመጣው የሚለው ደንታ የማይኖርበት ጊዜ በርግጠኝነት በሰዎች ላይ ይመጣል።”

ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 2083
386 views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 01:06:17
ቤተሰቦቹ ነጋ ጠባ «እስከዛሬ ያደረክልን አንድም ነገር የለም፤ የምንኖረው የሾቀ ህይወት ነው» እያሉ በንዴት አንጀቱን የሚያሾቁት አባት ነበር። ከተወሰነ ዓመት በኋላ በህመም አልጋ ላይ ወደቀ። ከህልፈቱ በፊት አንድ ኑዛዜ አስተላለፈ። ከቤቱ ውስጥ ተቆፍሮ የተቀበረ ትልቅ ኃብት እንዳለ የሚጠቁም ፍንጭ ሰጠ። ከሞተ በኋላ የቤተሰቡ አባላት ቤቱን አፍርሰው መሬቱን ቆፈሩት። ትልቅ ሳጥን አገኙ። ሲከፍቱት በውስጡ አንድ ደብዳቤ ተቀምጧል። ደብዳቤው ምን ቢል ጥሩ ነው ?

«እንደኔ ጀግና ከሆናችሁ ቤቱን እንደ አዲስ ገንቡት»

ምጥን አስተምህሮ


በዚህ ዘመን ለኢትዮጵያዊያን ደሳሳ ጎጆ ቢሆን እንኳ ከቤት በላይ ትልቅ ኃብት የትም አይገኝም። አይቀሬው የሞት ጥሪ መጥቶ ከምትኖርበት ቤት ያለፈቃድህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስክትወጣ ድረስ ገመናን ሁሉ በሚሸፍነው ቤትህ ውስጥ ሆነህ ይህንንስ ማን አየው አልሐምዱሊላህ እያሉ መኖር በራሱ የኃብቶች ሁሉ ትልቅ ኃብት ነው።
955 viewsedited  22:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 11:07:47
የወደድካትን ካላገባህ ያገባሃትን ውደድ
እሷ (ሚስትህ) ያለፈው ውድቀትህ ተጠያቂ አይደለችም
በቃ ያገባሃትን ውደድ ያንተ ያልሆነችን እየተከተልክ ያንተ የሆነችን ካጣሃት በኋላ ነው የሚገባህ
1.3K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 21:51:24
ይህን ፈቶ ያነሳልን እንዲህ ይላል.. በውሃ ገንዳ ውስጥ አንዲት ግመል ስትቦጫረቅ አስተዋልኩኝ ፣ ከዚያም ተነስታ ልጇን በቀጥታ ስታጠባ፣ እንቅስቃሴዋ በጣም ገረመኝ!!

ለምን እንደዚያ እንዳደረገች የግመሎቹ ባለቤት በደዊን ጠየኩኝ።
የግመሎቹ ባለቤት እንዲህ አለ፡- ግመሎ በውሃ ገንዳ ውስጥ ሲትቀመጥ ለልጆ ወተቱን ያቀዘቅዘዋል ፣ ከዚያም ከዘቀዘ ቡሃላ ግልገሎን ታጠባለች። ወተቱ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ስለነበር ቀዝቀዝ ይላል...

አላህም እንዲህ ይላል...

أفلا ينظرون إلى الإبل كيف خلقت
አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
አል ጋሺያ 17

ከአረበኛ ወደ አማረኛ በግርድፉ የተቀየረ
1.4K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 17:57:20
የውቂያኖሱ ጃውሳ
==============
ባህሩ መሃል ጉብ ብሎ የሚታይ ቋጥኝ እንዳይመስልህ። ከቦይንግ ድሪም ላይነር ሱፐር ጃምቦ ጀት ጋር የሚስተካከል አቋምና ክብደት ያለው የምድራችን ግዙፍ ፍጡር ሰማያዊው ዓሣ ነባሪ ሲሆን አየር ለመሳብ ከውሃው እየወጣ ነው የሚታየው።

በወጋችን መሃል ዓሣ ነባሪ በትንሹ በየ አምስት ደቂቃው አየር ለማግኘት ከውሃው የመውጣት ግዴታ አለበት። ረዥም የሚባል ጊዜ ውሃው ውስጥ የሚቆየው ለሃያ ደቂቃዎች ብቻ ነው።

ለመሆኑስ እንቅልፍ አይተኛምን? የሚል ጥያቄ ይነሳል። እንዴታ! ደህና አድርጎ ይለጥጣልን‘ጂ! የሚል ይሆናል ምላሹ። ግና ዶልፊንና ዓሣ ነባሪን የመሰሉ ፍጡራን የሚተኙት አእምሯቸውን ለሁለት ከፍለው ነው። የግራው የአእምሯቸው ክፍል ሲተኛ የቀኙ ንቁ( active) ስለሚሆን እንደያስፈላጊነቱ ከባህሩ እየወጣ አየር ይስባል። በተራው ደግሞ የቀኙ ሲተኛ የግራው ሥራውን ያቀላጥፋል

NB:—ለመሆኑ ከየብስ ፍጡራን ግዙፍ የሚባለው ዝሆን የዚህን ዓሣ ነባሪ ምላስ የሚያክል ክብደት ብቻ ያለው መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን?! የሚመገበውን በተመለከተስ ምን ለማለት ይቻላል? ዓሦችን አሳዶ ለመያዝ ቅልጥፍና ያንሰዋል እንጂ ቢያገኝ ተመራጭ ምግቦቹ በሆኑ ነበር። ክሪል የተባሉ ጥቃቅን ቃርሚያዎችን ከውሃው ጋር እየጋፈ ያስገባቸውና ወንፊት በመሰለ ማጣሪያ አጣርቶ ክሪሎቹን ወደከርሱ ከከተታቸው በኋላ ውሃውን ይተፋዋል። በቀን ሁለትና ሦስት ቶን የሚሆኑትን ይመገባል። አንድ ቶን 10 ኩንታል መሆኑን ያውቁ ኖሯል?!
1.4K views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 23:12:15
~ ለትዳር ሁሉን ሴት መውደድ በሽታ ነውና ይህ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ፡፡

~ የክፉ ቀን ጓደኛህን አትርሣ፡፡

~ የድህነት ሚስትህ ያን ድህነት መስላ አትታይህ፡፡

~ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን፡፡

~ ባልጠሩህ ስፍራ አቤት አትበል፡፡

~ ባትሄድም ጉድለት በማይከሰትበት ቦታ ጊዜህን አታባክን።

~ ካልሾሙህ መሪ አትሁን፡፡

~ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን፡፡⇝↡
⇨ለምን ብትል አንተ ሰው እንጂ ውሻ አይደለህምና፡፡
1.8K views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 19:04:13 ጥንቃቄ…


በአቋራጭ ለማድግ ብላችሁ ለምታስቡ…


እቤትዎ ቁጭ ብለው በወር ከመቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊየን ብር መስራት የሚችሉበት ምርጥ መንገድ እኛ ጋር አለ… ተብሎ የተጻፈ ፖስት አየሁና በተቀመጠው ስልክ ደወልኩ

ስልኩን ያነሳው ጎረምሳ ጥቂት የማይመስል ወሬ ካወራኝ ቡሃላ …ስራውን ከመጀመርህ በፊት በኦንላይን ስልጠና መውሰድ አለብህ አሁን በምነግርህ አካውንት ለመመዝገቢያ 3ሺህ ብር አስገባና ደረሰኝ ላክ ከዚያ …ብሎ ሊቀጥል ሲል ይቅርታ ግን ትክክለኛ መገኛ አድራሻችሁ የት ነው? ቢሮ መጥቼ ክፍያ ልፈጽም ስለው …ጆሮየ ላይ ስልኩን ዘግቶ አሰናበተኝ… ድጋሜ ስሞክር አይሰራም እንደነቃሁበት አውቋል ብሎክ ሊስት ከቶኛል ማለት ነው

ለማንኛውም ይሄ አይነቱ የሶሻል ሚድያ ሳክስ ሿሿ ነው …ብዙ ሰው ይነቃል ብየ አስባለሁ ያልነቃችሁ ካላችሁ አተርፍ ባይ አጉዳይ እንዳትሆኑ ጥንቃቄ ያሻል ለማለት ያክል ነው

~
2.4K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 00:07:52
በይቱል-ዐንከቡት

የሸረሪት ድር(በይቱል-ዐንከቡት) ሲባል ቁርአንን ማንበብ ወደሚችል ሰው አዕምሮ ቀድሞ የሚመጣው ደካማ ቤትነቱ ነው።ይህም አሏህ በቁርአኑ ቤቱን በደካማነቱ ባህሪይ ገልፆ በማንሳቱ ምክኒያት ነው።

وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ

"ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡"

(አል-ዐንከቡት፥41)

ታዲያ በጣም ያስገረመኝ በሂጅራው ክስተት ነቢያችን ﷺ እና ባልደረባቸው በዋሻው በነበሩበት ሰዓት ከቁረይሾች አሰሳ ከታደጋቸው አስባባት አንዱ በዋሻው መግቢያ ላይ የነበረው የሸረሪት ድር ነበር።የቁረይሽ አሳሾች ሰይዳችንﷺ ከሲዲቅ ጋር ወደ ተቀመጡበት ዋሻ መግቢያው ጋር ሲደርሱ:-
"(ሙሐመድ) እዚህ ቢኖር የሸረሪት ድር በደጃፉ አያደራም ነበር።" ብለው ነበር የተመለሱት።

አሏህ ይሁን ካለ አንተን ደካማ በተሰኘ ሰበብ ይጠብቅሃል።እርሱ ይሁን ካለ የሸረሪት ድር የእልፍ አዕላፍ ሰራዊትን መንገድ ይሰውራል።ከክፋት አይኖች ሁሉ ይከልልሃል።
እርሱ አላህ ነዋ!
2.1K views21:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 05:38:32
~• •~

አንድ ጥበበኛ እንዲህ አለ…

~ አእምሮህን ለማሳረፍ እነዚህን ነገሮች አስወግድ…

① - ባመለጠህ ነገር አትዘን ።
② - የእነሱን ዓይነት በሌለህ ነገር ሰዎችን አትውቀስ ።
③ - በግማሽ ጉልበትህ ለህልምህ አትታገል ።
በኋላ እንዳትጸጸት !!

~
1.9K viewsedited  02:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 05:23:35
ታቢዒዩ ኢብኑ ሲሪን በህይወታቸው የመጀመሪያ ዘመናት በሃብታቸው የታወቁ ባለፀጋ ነበሩ።ታዲያ ከዚህ የክብረት ዘመናት በኃላ የድህነት አመታትን ኖረዋል።ህልፈታቸውም በእስር በነበሩበት ጊዜ ከመሆኑ ጋር በሞቱበት ወቅትም የሰው ብድር ነበረባቸው።
ከሃብት ማማ በኃላ የኖሩበትን የድህነት ሁኔታ የታዘበ አንድ ሰው:-
"ሁኔታሁ ግን እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ?" ሲል ጠየቃቸው።

ኢብኑ ሲሪንም:-
"ይህ አርባ አመታት ሙሉ ስጠባበቀው የነበረ የወንጀሌ ቅጣት ነው።ከአርባ አመት በፊት ለአንድ ሰው :-"አንተ ድሃ!" ብዬ አነውሬው ነበር።" ሲሉ መለሱለት።

አታነውር፤ትፈተንበታለህ!
1.8K views02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ