Get Mystery Box with random crypto!

የውቂያኖሱ ጃውሳ ============== ባህሩ መሃል ጉብ ብሎ የሚታይ ቋጥኝ እንዳይመስልህ። ከቦ | ወርቃማ ንግግሮች

የውቂያኖሱ ጃውሳ
==============
ባህሩ መሃል ጉብ ብሎ የሚታይ ቋጥኝ እንዳይመስልህ። ከቦይንግ ድሪም ላይነር ሱፐር ጃምቦ ጀት ጋር የሚስተካከል አቋምና ክብደት ያለው የምድራችን ግዙፍ ፍጡር ሰማያዊው ዓሣ ነባሪ ሲሆን አየር ለመሳብ ከውሃው እየወጣ ነው የሚታየው።

በወጋችን መሃል ዓሣ ነባሪ በትንሹ በየ አምስት ደቂቃው አየር ለማግኘት ከውሃው የመውጣት ግዴታ አለበት። ረዥም የሚባል ጊዜ ውሃው ውስጥ የሚቆየው ለሃያ ደቂቃዎች ብቻ ነው።

ለመሆኑስ እንቅልፍ አይተኛምን? የሚል ጥያቄ ይነሳል። እንዴታ! ደህና አድርጎ ይለጥጣልን‘ጂ! የሚል ይሆናል ምላሹ። ግና ዶልፊንና ዓሣ ነባሪን የመሰሉ ፍጡራን የሚተኙት አእምሯቸውን ለሁለት ከፍለው ነው። የግራው የአእምሯቸው ክፍል ሲተኛ የቀኙ ንቁ( active) ስለሚሆን እንደያስፈላጊነቱ ከባህሩ እየወጣ አየር ይስባል። በተራው ደግሞ የቀኙ ሲተኛ የግራው ሥራውን ያቀላጥፋል

NB:—ለመሆኑ ከየብስ ፍጡራን ግዙፍ የሚባለው ዝሆን የዚህን ዓሣ ነባሪ ምላስ የሚያክል ክብደት ብቻ ያለው መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን?! የሚመገበውን በተመለከተስ ምን ለማለት ይቻላል? ዓሦችን አሳዶ ለመያዝ ቅልጥፍና ያንሰዋል እንጂ ቢያገኝ ተመራጭ ምግቦቹ በሆኑ ነበር። ክሪል የተባሉ ጥቃቅን ቃርሚያዎችን ከውሃው ጋር እየጋፈ ያስገባቸውና ወንፊት በመሰለ ማጣሪያ አጣርቶ ክሪሎቹን ወደከርሱ ከከተታቸው በኋላ ውሃውን ይተፋዋል። በቀን ሁለትና ሦስት ቶን የሚሆኑትን ይመገባል። አንድ ቶን 10 ኩንታል መሆኑን ያውቁ ኖሯል?!