2023-01-25 07:25:55
~ የመስሩርና የመቅሩር ታሪክ
~ ክፍል አስራ ሶስት
የመቅሩር ህልፈት
መስሩር በሞት ጣዕር ላይ በነበረበት ጊዜ መቅሩር በበኩሉ በአንድ የእንጨት ክምር ዙሪያውን ባለበት ምሰሶ ላይ ታስሮ የሚፈፀምበትን ይጠባበቅ ነበር፡፡ ቦታው ለእርሱ ተብሎ የተዘጋጀና የሞት ቅጣቱን የሚያገኝበት ሥፍራ ነው፡፡ እንዲሞት የተወሰነበት ተቃጥሎ ነው በመጀመሪያ የተጋጋመው እሳት እየተንቀለቀለ ዙሪያውን ሲከብበው ሲያይ በጣም ደንግጦ ነበር።
በኋላ ላይ ግን አንድ እንግዳ የሆነ ፍጥረት ከፊት ለፊቱ እንዳለ ሊመለከት ከፍተኛ መረጋጋት አደረበት ያ እንግዳም መልአክ ሲሆን እንዲህ አለው “አይዞህ አትፋራ ና ወደዚህ ከዚህ በኋላ ቅንጣት ስቃይ አይደርስብህም እንዲሁም
ተቃጥለህ አትሞትም።”
መቅሩር በለሆሳስ፡ “አንተ ማን ነህ? እለ
"እኔ ለአንተ የምስራች ልነግርህ የመጣሁ መልዕክተኛ ነኝ "ምንድን ነው የምትነግረኝ የምስራች?
አንተ በእርግጥ የሞት መልአክ ነህን?*
“አዎ
መቅሩር እንዲህ አለ "አሁን እስክሞት ከተቃጠልኩ አላህ ያደረኩትን ተውበት ተቀብሎኛል ማለት ነው?
መልአኩም ሲመልስ አንተ እስክትሞት ድረስ በእሳት አትቃጠልም - እሳቱ አንተ ያለህበት ከመድረሱ በፊት ነፍስህ እንድትወጣ ይደረጋል።
እኔ'ኮ በአላህ መንገድ ተቃጥዬ ብሞት ነበር ፈቃዴ
“ተስፋ አትቁረጥ! በመጪው ዓለም ጥሩ አቀባበል ይጠብቅሃል ስቃይ የሚባል ነገርም ያበቃል፡፡”
በዚህ ቅጽበት መቅሩር ሁሉም ነገር ግልጽ ሆነለት። ስሜቱን በቅጡ ሲያጤነው የጀነትን መልካም ሽታ አፍንጫው ሲያበስረው አስተዋለ።
ነገር ግን መልአከ ሞት ራሱን ለመቅሩር በገለፀበት ቅጽበት ነፍሱ አካሉን ተለይታ ህያው እንደሆነች የመልአኩን ማራኪና ውብ ፊት እያሰበች ነጐደች።
መቅሩርን ከነነፍሱ ለማጋየት ተዘጋጅቶ የነበረው የማቃጠያው ሠራተኛ አለቃውን በጩኸት በመጣራት ክቡር አለቃዬ ሆይ! ተከሳሹ ሰው ሞቷል ገና እሳቱ እርሱ ወዳለበት ሳይደርስ ነፍሱ ወጥታ ተዘርሯል” አለ፡፡
አለቃውም በመገረም “ስማ ይህ ሰው የሚያጋጥመውን አደጋ ገና ካሁኑ የፈራው ይመስላል። በድንጋጤ ራሱን ስቶ ይሆናል እንጂ እኔ በእውነት ሞቷል ብዬ አላምንም። ይልቁንስ ቀዝቃዛ ውሃ ፊቱ ላይ እርጭበትና ሲነቃ ጠብቀህ አቃጥለው። ከዚያ በኋላ አመዱንና የተራረፈውን አካሉን በወህኒ ቤቱ መቃብር ስፍራ ቅበረው አለው።
በተመሳሳይ ሰዓት መልአከ ሞት የመስሩርን ነፍስ ማውጣቱን አጠናቆ ስለነበር ሰውነቱ መወራጨቱን አቁሞ ፀጥ ብሎ ተጋድሟል። በዚህ ጊዜ ከደንገጡሮቹ አንዷ እሪታዋን አስነካችው። ሌሎቹም ተቀብለው ማልቀስ ሲጀምሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እሷንና እዚያ የተሰበሰቡትን ሁሉ ክፍሉን ለቅቀው እንዲወጡ አዘዛቸው። ከእርሱም ጋር የደኅንነት ኃላፊውና የዘበኞቹ አለቃ ብቻ ቀሩ።
ሶስቱ ሰዎች ብቻቸውን መሆናቸውን ያረጋገጠው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲህ አለ ፣ ሰዎች ታላቁ መሪያችን እንደሞተ ይናገራሉ ይህ አባባላቸው በፍጹም ትክክል አይደለም። እባካችሁ እርሱ አንድ የሆነ ቦታ መሄዱንና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይመለሳል ብላችሁ ንገሯቸው፡፡ አሁን አስከሬኑን ከወህኒ ቤቱ መቃብር ቦታ ውሰዱና ቅበሩት የመሪያችን በልዩ ሁኔታ በእብነበረድ የታነፀው መቃብር ቦታ ግን ክፍት እንደሆነ ይቆይ። ይህም ሰዎች በውስጡ ምንም ዓይነት አስክሬን አለመኖሩን ሲገነዘቡ እኛ ያልናቸውን ነገር እንዲያምኑን ያደርጋቸዋል።
ምሽቱ ለዓይን ያዝ ሲያደርግ የደኀንነቱ ኃላፊና የዘበኞቹ አለቃ የመስሩርን አስከሬን በጥንቃቄ ተሸክመው መቅሩር ከተቀበረበት አጠገብ ቆፍረው አጋደሙት የመቅሩር አስከሬን ተቃጥሎ የተረፈውና አመዱ) ከጥቂት ጊዜ በፊት በዚያ ቦታ ላይ አርፎ ነበር ይህ ሁሉ ድርጊት ሲከናወን ከሶስቱ ስዎች ውጭ ማንም ስለማያውቅ ምስጢርነቱ ፍጹም አስተማማኝ ነበር ማለት ይቻላል።
ምፀታዊ በሚመስል ሁኔታ መስሩርና መቅሩር በአንድ የመቃብር ቦታ የተቀበሩ ሲሆን በሁለቱም ላይ የመቃብሮቹ በሮች ክርችም ተደርገው በአፈር ተዘግተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታላቁ መሪ የአገዛዝ ሁኔታ በተለመደው አኳኋን እንደሚቀጥል አዋጅ አስነገረ።…
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ
1.7K views04:25