Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-13 04:26:13 ደቢር ለና

አንዳንዴ ሰው አሏህን አንድን ጉዳይ እንዲያሳካለት አምርሮ ይለምናል።ህይወቱም ሙሉ ለሙሉ በዚያ ዱዓው መሳካት ላይ የተንጠለጠለች እንደሆነች አድርጎ ያስባል።
አሏህም ዱዓውን ይቀበለዋል።ብዙ ረጅም ጊዜ ሳይልፍም ያ የተሳከላት ዱዓ ለርሱ ጥቅምን እንዳላመጣለት ይደርስበታል።በዚያ የተነሳም ለከባድ አደጋ መዳረሱን ያስተውላል።ዘመን ወደ ኃላ ቢመለስም ያንን ዱዓ ፈፅሞ እንደማያደርግ እርግጠኛ ይሆናል።

በሰዪዲና ኑህ ዱዓ ውስጥ የምናገኘው ጥልቅ ትርጉምም ይህንን ነው።


قَالَ رَبِّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَسْأَلَكَ مَا لَيْسَ لِي بِهِ عِلْمٌ ۖ

«ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ፡፡"

ሰይዲና ኑህ ይህን ዱዓ ያደረጉት አሏህ በነገራት ፍፃሜ እውቀቱ ስለሌላቸው ነገር እንዳይጠይቁት ከነገራቸው ወዲህ ነው።

فَلَا تَسْأَلْنِ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۖ إِنِّي أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ الْجَاهِلِينَ

"በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ፡፡"

ተመልከት።እንዲህ የተባሉት አሏህ ከፍጡራን መሃል በእውቀትም ሆነ ተቅዋ ላስበለጣቸው ከኡሉል-ዐዝም አንዱ ለሆኑት ነቢይ ኑህ ናቸው።ለርሳቸው እንዲህ ከተባለ እኛ ለዚህ መሰል ዱዓ እጅጉን የተገባን ነን።
ነገራትን በሙሉ ወደ አሏህ ከማስጠጋት የተሻለ መንገድ ማግኘት ለኛ አስቸጋሪ ነው።
ለዚህም ከሰለፎች መሃል የአንዱ ዱዓ እንዲህ ነበር:-
اللهم دبِّر لي؛ فإني لا أُحسن التدبير، واختر لي؛ فإني لا أُحسن الاختيار

"አሏህ ሆይ! ነገራቶቼን አስተናብርልኝ።እኔ ማስተናበርን አላሳምርም።(ከነገራት)መልካሙን መምረጥንም አልችልምና፤ ምረጥልኝ። ።
775 views01:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 03:45:52 ስደት፣ መከራና ችግር ብርቅ ባልሆነባት ዱንያ ላይ የስደት ሕይወት በነቢያት ኑሮ ላይ ጭምር ተንፀባርቋል፡፡ ነቢዩ ሙሳም ነቢዩ ሙሐመድም ተሰደዋል፡፡ የአላህ እዝነት አይለያቸው፡፡ የሁለቱም ነቢያት ስደት በመጨረሻም በስኬት ነበር የተጠናቀቀው፡፡
..
ድንገት በተፈጠረ ፀብ ምክንያት ከግብፅ ተሰደው መድየን ምድር የደረሱት ነቢዩ ሙሳ ዐ.ሰ. እዚያ ሲደርሱ ለአገሩ ባዳ፣ ለሰዉም እንግዳ ባይተዋር ነበሩ፡፡ ‹ምንም ነገር› በሚባል መልኩ ወላሀብት፣ ወላ ሚስት፣ ወላ ወዳጅ ዘመድ ምንም ነገር አልነበራቸውም፡፡
ሆኖም ግን በደረሱበት ሁሉ የበጎ ሥራ ስሜት አብሯቸው ነበርና መንጋዎቻቸውን ዉሃ ለማጠጣት የተቸገሩ ሴቶችን ባዩ ጊዜ ዉሃ በማጠጣት አገዟቸው፡፡ በድርጊታቸው ዉለታም ሆነ ክፍያ ፈልገው አልነበረም፡፡

ይህችን በጎ ሥራ ሠሩና ወደ አንዲት ዛፍ ጎራ በማለት ጥላዋ ሥር አረፉ፡፡ በሁኔታቸው የዋለሉና ግራ የተጋቡ ይመስላሉ፡፡ ጥላዋ ሥር ሆነው ወደ ነፍሣቸው አምላክ እጃቸውን አነሱ ‹ ጌታዬ ሆይ እኔ አንተ የምታወርድልኝን መልካም ነገር ፈላጊ ድሃ ነኝ፡፡› አሉ፡፡
በእዝነትህ ጎብኘኝ፣ መላዬም መፍትሄዬም አንተው ነህና … የሚሉ ይመስላሉ፡፡
.
በርሱ ከልብ ለተማመኑት ሁሉ መከታ የሆነው ጌታ ምላሽ አልነፈጋቸውም፡፡ ያውም ባልታሰበ ፍጥነት እነዚያን ሴቶች ሰበብ በማድረግ ምላሽ ሠጣቸው፡፡ በዚያው ቀን ዉስጥ ሚስት፣ ሥራም ቤትም አገኙ፡፡
በየትኛውም እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ብንሆን በፈጣሪያችን ላይ መልካም ሀሳብ ይኑረን፡፡ ለማለት ነው መልዕክቱ፡፡
.
ሀሳቡ የሸይኽ አልዐሪፊ ነው።

~⇨ Abx

በመልካም ዱአችሁ አስቡን መልካም ነገር ሁሉ አያርቅባችሁ ከክፉ ነገር ይጠብቃችሁ ወሩ ረመዷን ነውና በዱኣ በኢባዳ በርቱል።…
353 views00:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 23:37:25
እንኳን ለተከበረው ለውርሃ ረመዷን ሸህሩን ሙባረክ በሰላም አደርሰን አደረሳችሁ።

ወሩን ከይር በመስራት የተቸገሩትን በመዳበስ በመጠየቅ እንዲሁም ወደ አላህ በመቅረብ ከይር የምሰራበት የምገበይበት ወር ነው።

አላህ ወሩን ወፍቆናል ከተጠቀሙበትም ያድርገን መልካም የከይር ወር ያድርግል በአፍያ በአማን አላህ ያስጨርሰን…
454 viewsedited  20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 23:36:19
ልክ እንደ ሁሉ ሰው ሰዋዊ ስሜት ነበራቸው።
ፊታቸው እስኪያበራ ይደሰ፤
ጉንጫቸው እስኪቀላ ይቆጡ፤
ፂማቸው በምባ እስኪርስ ያለቅሱ፤
ክራንቻ ጥርሳቸው እስኪታይ ይስቁም ነበር።
ነገር ግን በዚህ ሁሉ ሁነቶች ሚዛናዊ ነበሩ።ደስታ የማያኮራቸው፤ሃዘን የማያስረሳቸው፤ቁጣ የነብሳቸውን ልጓም የማይነጥቃቸው ነበሩ።
በዚህም ከሰዎች ሁሉ እጅግ ታጋሹ፣ፍትሃዊውና ነፍሰ ፅዱው ነበሩ።
ሰለዋቱሏሂ ወሰላሙሁ ዐለይሂ
456 views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 09:35:55 በዕለተ ቂያማ ከአላህ ሱ.ወ እና ከወላጆቼ ማን እንዲተሳሰብህ ትፈልጋለህ ብባል ከወላጆቼ በላይ  የሚያዝንልኝን አላህ እመርጣለሁኝ !
አል ቁርኣን
'በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡
እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
231 views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 14:00:26
ኢማን ሩሁን እያጣ ሲሄድ፤ከውስጥ ይልቅ የውጫዊ ገፅታ ጉልህ ትኩረትን ያገኛል።ይህም ይሄድ ይሄድና...ሰርቆ ስላገኘው ገንዘብ ቃላቱን አስወቦ "አልሐምዱሊላህ አሏህ የዱንያ ክብረትን ችሮኛል።" የሚል ሩህ የለሽ የሸክሊያ ኢማን የተጎናፀፈ ስብእናን ይፈጥራል።በሐራም ለመጣ "ክብረት" ምስጋናው ተውባህ እንጂ ሌላ መንገድ አለውን?
715 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 06:40:13 አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች
ታላቅ የምስራች ከአሊፍ ኦንላይን የቁርኣን መድረሳ

በቤትዎ በቢሮዎ እንዲሁም ባሉበት ቦታ ሁነው በተመችዎት ጊዜ ሚቀሩበት ሲሆን ብቃት ባላቸውና ቁርአንን በሀፈዙ ኡስታዞች ብቻ የሚቀሩ ይሆናል . በተጨማሪም ቁርአንን መሀፈዝ ለሚፈልጉ ሰዎችም ቦታችን ክፍት መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን

-  ቁርአን ለጀማሪዎች
-   ቁርኣንን በተጅዊድ
-  ቁርአን ሒፍዝ
-  የተጅዊድ ትምህርት


ቁርአንን ለመቅራት ጊዜ,ቦታ,ስራ,ልጆች,ቤተሰብ,እድሜ ሳይገድበን መቅራት በምንችልበት ዘመን ሳንቀራ ህይወታችን እንዳያልፍ

ለመመዝገብ እና ቂረኣት ለመጀመር ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ                       
           

         @onlineAliifquran
         @onlineAliifquran
         @onlineAliifquran
           
          
1.0K views03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 06:30:43 ፈተናዎች ወደተሻለ ቦታ ሊያደርሱን የሚችሉ መወጣጫዎች ናቸው። እናም በተፈተንን ጊዜ በህይወት ተስፋ የሌለን እንደሆነ አንሰብ።

ህፃን ልጅ ጥርሱ እንዳይበላሽ ከረሜላ መብላት ብትከለክለው፣ ውድ የሆነበትን ነገር እንደቀማሃው ተሰምቶት፣ ልቡ ተሰብሮ ያለቅሳል። እኛም አላህ ፊት እንደዚህ ነን… ለወደፊት የሚከሰተውን ስለማናውቅ፣ የሚጠቅመንንና የማይጠቅመንን መለየት ይከብደናል። አንዳንዴ፣ ያስፈልገናል ብለን ያሰብነውን አላህ ከጎናችን ሲያነሳው፣ እንደዚያ ህፃን ልጅ ተበደልን ብለን ልባችን አይሰበር፣ ብሶት አናሰማ። አላህ ከመጥፎ ነገር ሊጠብቀን ወይንም ጥሩ ነገር ሊሰጠን ፈልጎ ቢሆን እንጂ፣ ለባሪያወቹ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ አዛኝ ነው።
956 views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 18:53:19 ዱንያ እንዲህ ናት እንግዲህ። ባለፈው ጠንካራዉን ቡድን ፍርስርሱን አውጥቶ ያሸነፈው ወገን ዛሬ ደግሞ መጨረሻ ላይ ባለ ቡድን ይሸነፋል።
ትናንት ትልቁን አሸነፍኩ ብለህ አትኩራ ዛሬ በትንሹ ትሸነፋለህ።
በተሰጣችሁ ነገር ከልክ በላይ አትደሰቱ፣ ባመለጣችሁ ነገርም ብዙ አትዘኑ። አይደለም ነገ የሚቀጥሉት ደቂቃዎች ምን እንደያዙ አናውቅም።
872 views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 03:21:31 አንደበቴ ቃላት አጥቶለት ፤ በደረቴ የታሰረ የልብ ምኞቴን የምትሰማ አንተ አሏህ ነህ!

ኢላሂ…
452 views00:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ