2023-06-18 18:50:01
የጅብ ልጅ ሞት ! ተረት = ረት
==========
ጅብ ልጅ ይሞትበትና ለአንኩዮ አህይት ልጄ ሞቷልና አላቅሱኝ ሲል መርዶ ነጋሪ ላከ ።
ተረጂዎቹም እንግዲህ ሰምተን ብንቀር ይጣላናል ብንሄድም ይበላናል እንዴት ብናደርግ ይሻለናል ብለው ምክር ጀመሩ ። ነገር ግን ቀርተን ከሚጣላን ሄደን ቢበላን ይሻላል ብለው ተነስተው ልብሳቸውን አሸራርጠው ሄዱ ።
ከለቅሶው ቦታ እንደደረሱ አንድኛዋ ብድግ አለችና
ምን አጥንት ቢሆን ይሰበራል ጥረረስዎ
ምን ጨለማ ቢሆን እሾክ አይውጋዎ
ምን ጥቁር ቢበሉ ነጭ ነው ክስዎ
ያንን ጎራ ዞሮ ይሰማል ድምጥዎ
አሁን የርሶዎ ልጅ ምን አገኘብዎ
እያለች ሙሾ ታወርድ ጀመር
እሱም ቀበል አለና …
አንቺስ ደግ ብለሻል
መልካም አልቅሰሻል
ይህ ሁሉ አዘንተኛ ምን ይብላ ብለሻል ።
ሲል መለሰላት
እንዳልማራቸው ባወቁ ግዜ እንግዲህ አለቀቀንም ምን ማድረግ ይሻለናል ብለው እነእንኩዮ አህይት ምክር ጀመሩ ።
አንዲት እናቷ የሞተችባት ውርጭላ ከነርሱ ጋር ነበረችና ይቺን እንስጥና እንገላገል ብለው ሲነጋገሩ ግልገሏ አህያ ሰምታ ምነው እኔ ውርጭላ ማን ይዞኝ በሩጫ ብላ ብላ ተነስታ ትታቸው በሩጫ እልም አለች ።
ከዚህ ቡሃላ ጭንቀት ያዛቸውና መቼስ ምን ይደረግ ብለው ለምቦጫችንን ሰጥተው እንሂድ ብለው ተማከሩ ወዲያ በል እንግዲህ የላይ የላይ ለንቦጫችንን ውሰድ አሉት እሱም እንዳመላከቱት ለምቦጭ ለምቦጫቸውን ገነጣጠለና ለቀቃቸው ።
በሶስተኛው ቀን ደግሞ እስቲ ዛሬ ሳልስቱ ነው ና መቃብሩ ላይ ደርሰን አያ ጅቦ ጠይቀን እንምጣ ብለው ቢሄዱ አያ ጅቦ ቀደሞ ከመቃብሩ ላይ ሲያለቅስ ደረሱ ።
አያ ጅቦም ድዳቸውን ገልፍጠው ባየ ግዜ ለካ ለኔ ሀዘን ለናንተ ሰርግና ምላሽ ሆኖላችሃልና የኔ ልጅ ትናንት ሞቶ ዛሬ እናንተ እየሳቃችሁ የመጣችሁት በምን ምክንያት ነው ብሎ ተቆጣና ለወገኖቹ እረ በሉ እያንዳንዷን እየዘረጠጣችሁ ጣሉልኝ አላቸው ።
ከዚህ ቡሃላ የጅብ ወገን የአህያን ልጅ እየገነጣጠለ ጣለ ይባላል ።
☞ ባለጋራን ቆቅ ሆነው ካልጠበቁት ምንም ቢለማመጡት ማጥቃቱን አይተውም ።
☞ አንድነት ሀይል ነው ።
አያ ጅቦም ሳታማህኝ ብላ የተባለው ለዚህ ነበር ።
፥ ብዙ መልእክቶችን እንዳስተላለፈ ተስፋ አለኝ!
2.2K views15:50