Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-16 05:59:19 አንዱ ካንዱ የሚሸሽበት ቀን


ፀሐይ በየደቂቃው እየቀረበች ግለቷም እያየለ ሲሄድ ምድር ደግሞ በበኩሏ እየተስፋፋችና እየተንሰራፋች መጣች። ፍጥረት የተባለ ሁሉ ከዚህ ጉድ ለማምለጥ መውጫ ቀዳዳ ባገኝ ብሎ ይራወጣል የሰው ልጅ ደግሞ አንዱ ካንዱ ሀቅ ለማምለጥ (ለመሸሽ ይሞክራል መስሩር ከመቅሩር ተለይቶ ወደ ግራ አቅጣጫ ሊያፈተልክ ጥረቱን ተያይዞታል የሰው ልጅ የዱር አራዊት ጅኖችና አእዋፋት እርስበርሳቸው ተደበላልቀዋል።


የሰማይ አካላት መርገፍ የተራሮቹ መንኮታኮት ሌላውም ጩኸትና ድብልቅልቅ ከፍተኛ ውጥንቅጥና ውድመት በማስከተሉ ምክንያት ፍጡር የተባለ ሁሉ ወዴት እንደሚሸሽ ባያውቅም እንዲሁ ባፈተተው እግሬ አውጭኝ በማለት ላይ ነው፡፡ መስሩርም እንደሌላው ሰው ሁሉ በርግጎ ልቡ አስኪጠፋ ሮጠ ይህን ያደረገውም አንድ ዓይነት ማምለጫ በመሻት ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ነገር ዋጋቢስ በሆነ ግርግር ከመታመስ በስተቀር ሽሽቱ ምንም ዓይነት ለውጥ አላመጣም። ይህን ያስተዋለው መስሩር በተስፋ መቁረጥ ሀሞቱ ፈሰሰ አሁን ሁኔታውን ቆም ብሎ ሲያስተውለው ያ ሁሉ ሩጫና ድካም ዓላማ የለሽ ሆነበት ምክንያቱም በዚያ ቀን መቆምም ሆነ መሮጥ የሚያስከትሉት የተለየ ነገር አልነበረምና ነው።


ሁለቱም ያው ናቸው ምን ማምለጫ አለና ወዴትስ ይሸሻል? በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ መስሩር በድንገት የወታደሮቹ አለቃና የደኅንነቱን ኃላፊ ከጐኑ ሲሮጡ አስተዋለ እንደ እውነቱ ከሆነ በዚህ ሰዓት ከፍተኛ ደስታ ነው በውስጡ የተሰማው በመሆኑም ጊዜ ሳያጠፋ በጩኸት ጠራቸው የወታደሮቹ አለቃ ወደ እርሱ ዘወር ሲል ፊቱ በስቃይ ተጠባብሶ አስተዋለው:: እንዲያውም እርሱንም በደንብ ያወቀው አልመሰለውም። መስሩር ከዚያ በኋላም የደኀንነቱን ኃላፊ ሊረዳኝ ይችላል - በማለት በጩኸት ጠራው እርሱ ግን እየት አድርጐት ሀይ ነፍሴ ወይ ነፍሴ እያለ በመጮህ ሩጫውን ተያያዘው ከዚያም መስሩርን እየተራገመና እየተሳደበ ከአዓይኑ ተሰወረ መስሩር በመንፈሱ ውስጥ ብቅ ብሎ የነበረው የደስታ ስሜት በአንድ ጊዜ ከውስጡ ተንኖ ሲጠፋ በምትኩ የተለመደው ፍርሃትና ጭንቀት መልሶ ነገሰበት



ተስፋ ማድረግ ካለማድረግ ይሻላል በማለት እንጅ ኃይልና ስልጣኑ እንደከዱት መስሩር ከተገነዘበ ቆይቷል። እንዲያውም አሁ ራሱን እየቆጠረ ያለው በትልቅ ወጥመድ እንደተያዘች አይጥ ረዳት የለሽ አድርጐ ነው በመሆኑም ያለ አንዳች ዓለማ መሮጡን ቀጥሏል። አንድ ጊዜ ወደ ግራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ቀኝ በማለት እያለከለከ ይከንፋል በዚሁ ሩጫው ላይ እያለ እናቱና አባቱ ባጠገቡ ሲያልፉም እንዳላየ በመሆን ምንም ሳይላቸው ቀጠለ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም የዘበኞቹ አለቃ በአጠገቡ አለፉ። እነርሱ ግን በጣም የደነገጡና ቅስማቸው ድቅቅ ያለ መሆኑ ያስታውቃል።



አሁን መስሩር በሚገባ የተገነዘበው ነገር ማንም ከዚህ ጉድ እንደማያስጥለው ሲሆን እርሱም በበኩሉ ከወንድሙ፣ ከእናቱ ከአባቱ እንዲሁም ከልጆቹ ለምን እንደሚሸሽ ግልጽ ሆኖለታል። ከዚህ በኋላ በፍርሃት ተሸንፎ ከመርበድበድ ውጭ ሌላ የተሻለ ነገር እንደማያገኝ ውስጡ ነግሮታል። አሁን እንግዲህ ከራሱ የሚሸሽ እስኪመስል ድረስ ያለምንም ተስፋ መሮጥ እጣፈንታው ሆኖአል
የዕለተ ቂያማ አስፈሪነት መስሩር ከድንጋጤ ጋር ድርና ማግ ሆኖ እንደተሰራ ሁሉ መላ እርሱነቱን ፍፁም ቀይሮት መላ ቅጡ የጠፋው አዲስ ጅምር እብድ አስመስሎታል።


ይህ ቀን መስሩር ብቻ ሳይሆን ከመቃብር አብሮት የተቀሰቀሰውን መቅሩርንም ግራ በማጋባት ያለማቋረጥ ጌታውን እንዲማፀንና ይህንን ውጥንቅጡ የወጣ የመከራ ድርድር ከፊቱ ዞር እንዲያደርግለት እንዲለምን አድርጐታል።
ሌላው አስደናቂው ክስተት በዚህ አስደንጋጭ ቀን የጅኖች መላና ኃይል ሁሉ ከላያቸው ላይ ተነስቶ ፍፁም ምስኪንና ረዳት የለሽ ሆነው መታየታቸው ነው። በተከሰተው ከባድ ሁኔታ ተደናብረው ከሚሸሹት የሰው ዘሮችና የዱር አራዊት ጋር ተቀላቅለው ባፈተተው መንጎዳቸው ለዚህ ሁኔታቸው እንደ አንድ ትልቅ ማስረጃ ሊጠቀስ ይችላል። በሌላ በኩል የዱር አራዊቱ በሰው ልጅና በጅኖች ላይ ጥገኛ በመሆን በመጠኑም ቢሆን ደህንነት የተሰማቸው መስሏቸው ነበር። ይሁን እንጂ የሁኔታውን መክፋት ተከትሎ በተለይም የሰው ልጆች ለማምለጥ ሲራኰቱ፡ ሲያስተውሉ ፍፁም ድንጋጤ ነበር የዋጣቸው።

ምድር ይበልጥ እየሰፋችና እየተዘረጋች ነው የምትሄደው፡፡ በአኳያውም ፍጡርን በሙሉ በየጊዜው እየተባባሰ የሚሄድ ተስፋ መቁረጥና ድንጋጤ እየዋጠው ሲሄድ ይታያል።


ኢንሻ አላህ ይቀጥላል…
161 viewsedited  02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 05:46:20 መጨረሻው ሲቃረብ


አሁን እየሆነና እየተካሄደ ያለው ነገር በጣም አስፈሪ ከመሆኑ የተነሣ ለሰው ዘር ለጅኖችና ለዱር አራዊት ሊቋቁሙት የሚከብድ እየሆነባቸው ነው ከአባታችን አደም ጀምሮ የነበረውን ፍጡር ሁሉ ምድር እንድም ሳታስቀር እየተፋችው ነው::


ይህ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰው ልጅና ጅኖችን እንዲሁም እንስሳትና አራዊት የያዘ ስብስብ የፍርዱ ቀን ወይም (ዕለተ ቂያማ) መድረሱን በግልጽ ተገንዝቧል፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት ይኖሩበት የነበረችው ምድር ከዚህ በኋላ ብዙም ጊዜ የምትቆይ አለመሆኗን እየተረዱ መጥተዋል። በሕይወት በኖሩባት የቀድሞ ዘመናት ቤታቸው ከእንግዲህ ከነትዝታዎቿና ኮተቷ ጋር በዓይናቸው ስር ድምጥማጧ ሊጠፋ መሆኑን እያዩ ነው።


የባህሮች መቃጠል፣ የተራሮች ተነቅሉ መንኮታኮት፡ የጨረቃ ተገምሶ መውደም የከዋክብት መርገፍ የፀሐይ ወደ ምድር መቅረብ ያለፈውና ብዙ ዘመናት የኖረው የተፈጥሮ ሕግ ተሽሮ ድብልቅልቁ መውጣቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን አሮጌው ዓለም ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል እየፈራረሰ መሆኑን ያሳያል።


ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፍጥረታት አንድ ላይ : ተሰብስበው የአሮጌውን አጽናፈ ዓለም መፈራረስ የመጨረሻ ሁኔታ ይታዘባሉ የአጽናፈ ዓለሙ ፍርስራሽ እየተርገፈገፈና እየተፍረከረከ መውደቁ ከአላህ ፊት መስገዱና መተናነሱ መሆኑን ማንም ያለምንም ልዩነት እንዲገነዘብ ተደርጓል። እንግዲህ ሁሉም ፍጠራን ይህ አጽናፈ ዓለም በፈጣሪው የሚሰግድ መሆኑን በአርምሞ እያስተዋሉ የሚቀጥለውን ትዕይንት ይጠባበቃሉ።


ወሳኙ ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ ፍጠራኑ ውጫዊው አስደንጋጭ ትዕይንት ከውስጣዊው ይሆናል ብለው ከገመቱት) ስሜታቸው የበለጠ የሚያርድና ተስፋ የሚያስቆርጥ እየሆነባቸው መጥቷል ፀሐይ ወደ ምድር ተጠግታ ያለምንም ርህራሄ አናት እንደሽሮ የሚያንተከትክ ሙቀቷን እየለቀቀች ባለችበት ሰዓት መስሩር ወደ መቅሩር ጠጋ ብሉ እንዲህ ሲል ጠየቀው “ፀሐይዋ ደግሞ ምን ነክቷት ነው?


መቅሩር በዚህ ጊዜ ፀሐይን እያስተዋላት የነበረ ሲሆን ይበልጥ ምድርን በተጠጋች ቁጥር ስፋቷና ታላቅነቷ እየጨመረ እንደሚመጡ ልብ ብሏል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ መቅሩር ስሜቱ በጣም በመናወጡ ለመስሩር ጥያቄ ተገቢውን መልስ ለመስጠት አልቻለም ነበር።
የፀሐይዋን ወደ ምድር መጠጋት ተከትሎ ከፍተኛ የሀሩር ውርጅብኝ በመዝነቡ ፍጡር የተባለ ሁሉም በላብ ተጠመቀ ወይ ተዘፈቀ ማለቱ ይቀላል ይህ የፍጡራኑ ላቦት ወደ ሰማይ ከሚትጉለጐለው የአቧራና አሸዋ ብናኝ ጋር እየተቀየጠ በሚፈጥር ወላፈን ምክንያት መስሩር በፈላ ውኃ ውስጥ የሚራመድ መሰለው የሚወጣው ላብ እስከ ጉልበቱ የደረሰ በመሆኑ እግሮቹ ለመራድ በጣም ከበዱት በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ወደ መቅሩር ሲመለከት በጣም ተደነቀ ምክንያቱም መቅሩር እያላበው ቢሆንም መጠኑ !
ያን ያህል እንደርሱ ከባድ አልነበረምና ነው።


ፀሐይዋ አሁንም ወደ ምድር በጣም እየተጠጋች ሲሆን የመስሩ እግር የዚያኑ ያክል እየከበደው መጣ ላቡ በጣም እየበዛ በመሄዱ የተነሣ እስከ ደረቱ : ከፍ : ብሏል በዚህ ሁኔታ ላይ እያለም የመቅሩርን ሁኔታ ከማስተዋል አልቦዘነም አዎ መቅሩርም እያላበው ነው። የላቡ መጠን ግን እስክ ቁርጭምጭሚቱ ድረስ ብቻ ነው የደረሰው መስሩር አሁን እርግጠኛ እየሆነ የመጣው በዚህ የሰውነቱ ላብ ተዘፍቆ በመስጠም እንደሚሞት ነው በሁኔታው በጣም ተስፋ ቆረጠ።


ለእርሱ ሞቶ ቢገላገል ከዚህ ሁሉ ስቃይና መከራ ምንኛ በተሻለው ነበር። አሁን ግን የተረዳው አንድ አስደንጋጭ ህቅ ሞት ከእንግዲህ በቀላሉ የሚገኝ ነገር እንዳልሆነ ነው። ላቡ የጐርፍ ያህል ወርዶ እስከ አንገቱ ያስጥመው ጀመር እንደዚያም ሆኖ ግን ወደፊት ከመራመድ አልታገታም
የፀሐይዋ ግለት ወደ ምድር ይበልጥ እየተጠጋች ከመምጣቷ ጋር ጨምሯል ጠቅላላውን ፍጥረት ታላቅ ጭንቀት ስለዋጠው የሚያደርገው ሲያጣ ባወጣ ያውጣው በማለት ሁሉም ሩጫውን ተያያዘው…

ይ ቀ ጥ ላ ል…
349 views02:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 12:43:06 የዱር እንስስት መሰባሰብ


በበረሃ ላይ የተተከለ ድንኳን ችካሎቹ በአጋጣሚ ቢነቀሉ ነፋስ የትም ወስዶ በምድረ በዳ እንደሚጥላቸው ሁሉ ተራሮችም ከመሬት ሲነሱ አቧራ ብናኝ ሆነው በመጥፋታቸው ምድር የተንጣለለች ሜዳ ሆናለች ሰውም በመላእከት እየተነዳ ይርመሰመስባት ጀምሯል


ቀደም ብሎ እንደተገለፀው ተራሮቹ በሚያስደንቅና ይሆናል ተብሎ በማይገመት - ሁኔታ ተፈርፍረውና ቦንነው ድራሻቸው ጠፍቷል ፣ ሰውም በከፍተኛ ደረጃ በፍርሃት ተውጦ ይቅበዘበዛል ሁሉም ሰው በዚህ ታይቶ በማይታወቅ አስደንጋጭ ቀን አጀማመር በፍርሃት ቢዋጥም ገና የወደፊቱን ሁኔታ ሲያስበው - ሊመጣ የሚችለውን የከፋ አደጋ በመገመት በሰቃ ይተነፍሳል። መቅሩር በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ጌታውን መለመኑን አልተወም አላህ ሆይ እባክህ እዘንልኝ አንተ እጅግ አዛኝ ነህና አለ
መስሩር በበኩሉ ድንጋጤው አይሎል በሁለም አቅጣጫ አደጋ እያደነው መሆኑ ተሰምቶታል። ምን ይኽ ብቻ።


ሁኔታው ከዚህ የከፋ ቢሆንም ሞት የማይገኝበትና ምቾት የሌለው መሆኑ ነው ትልቁ አሳር መሬት እየተከፈተችና እየተሰነጠቀች በውስጧ ያሉትን ሙታን በምትተፋበት ወቅት የዱር አራዊትና እንስሳት እንዲሁም ጅኖችም ከሁሉም አቅጣጫ እየወጡ ከሰው ጋራ ይተራመሱ ገብተዋል
የሰውን ልጆች ከቀኝ በኩል በቅርብ የተቀላቀሏቸውን ጅኖች ተፈጥሯዊ መልካቸውን ሲያዩዋቸው በጣም አስቀያሚ መሆናቸው ሌላ ችግር ሆኖባቸዋል ሆኖም ከአጠቃላዩ ቀኑ ይዞት ከመጣው አስፈሪና አስደንጋጭ ነገር ጋር ሲነፃፀር የጅኖቹ መልከ ጥፉነት እዚህ ግባ የሚባል ችግር አይደለም::

ከዚህ ይልቅ የባህሮች መቃጠልና የተራሮች ተነቅሎ መንኮታኮት ነው ታላቅ መባትና ፍርሃት በሰው ልጆች ልብ ላይ የለቀቀባቸው ጅኖች በከዋክብቶች መካከል እንዲሁም ወደ ምድርና ወደ ሰማይ እንደፈለጉ እየበረሩና እየሮጡ ሲጫወቱ አስደናቂ እንዳልነበሩ ዛሬ ግን ሁሉም ቅስማቸው ተሰብሮና በሀሳብ ተውጠው እንገታቸውን
ደፍተዋል ወደ ታላቅ የሆነ የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት መንጋ በሰው ልጆች ሰልፍ በግራ በኩል መሰባሰብ ጀመረ ቁጥራቸው ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው የሚሄደው ከመሬት ውስጥ እያንዳንዱ መን እየወጣ በተጠጋ ቁጥር አንገቱን ደፍቶ በፍርሃት ሲራመድ ይታያል ብዙ ዓይነት የአራዊት ዝርያዎች አንበሳ፣ ነብር፡ የተራራ ፍየሎች ውሻ፡ አእዋፋት ዝሆኖችና አውራሪሶች ወዘተ ሁሉም አንድ ላይ ተቀላቅለው ይነጉዳሉ


የአንበሶች መንጋ መስሩርን ሲቀርቡት በድንጋጤ ይርበተበት ጀመር፡፡ በምድረ ዓለም እያለ ብዙ አንበሶችን በአደን ገድሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ከእነዚህ አናብስት አንዱ ቂሙን ሊበቀለኝ ይዘነጥለኝ ይሆናል ከሚል ነው ስጋቱ የመነጨው ፣ ይሁን እንጂ የአንበሶቹ መንጋ አጠገቡ እንደደረሱ ብዙም ትኩረት ሳይሰጡት ሩጫቸውን ቀጠሉ መስሩር አሁን ልብ ያለው ነገር ከእነዚያ አንበሶች ጋር የዱር ፍየሎች ያሉ መሆኑን ነው አንበሶቹ በፍየሎቹ መኖር - ግድ አልነበራቸውም፡፡

እንደዚሁም ፍየሎቹ ከአንበሶች ጋር መሆናቸው ምንም የሚያስፈራቸው አይመስልም ይህ ሁኔታ የሚያሳየው የዚህ ቀን ድንጋጤ የዱር እንስሳትን ባህሪ ፍፁም በመቀየር ደመነፍሳቸው ስለሚመገቡት ነገር እንዲያስበ እንዳላደረጋቸው ነው እንግዲህ ሁኔታውን ሲያጤነት የጅኖችና የዱር አራዊት በዚህ ስፍራ መተራመስ የቀኑን አስፈሪነት ይበልጥ እንዲባባስ አድርጐታል ማለት ይቀላል።
መስሩር እና መቅሩር አሁንም ተቀራርበው ነው የሚጓዙት ምንም እንኳን መስሩር በጭንቀት እየተንጠረጠረ ቢሆንም ቅሉ በዚህ ጊዜ መስሩር ወደ መቅሩር ቀረብ ብሎ አንዳንድ ግራ የሚገቡ ጥያቄዎችን ያቀርብለት ጀመር ከሞትን ምን ያህል ጊዜ ሆነን? ማለቴ ምን ያህል ጊዜ ነው ከመሞታችን በፊት የኖርነው? ማለቴ ምን ያህል ጊዜ ሆነን ከሞትንና ከተነሣን?


መቅሩር ለዚህ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ እንዲህ አለ " ሁሉንም ነገር የሚያውቀው አላህ ነው እኔ በበኩሌ ትንሽ ቀናት እንዲያውም ጥቂት ስዓታት የቆየሁ ሆኖ ነው የሚሰማኝ እንደማስበው ከትንሽ ቀናት በፊት በሕይወት ነበርን ከጥቂት ሰዓታት በፊት ደግሞ የሞትን ይመስለኛል በእውነቱ ምኑም አልገባኝም

ይቀጥላል…
286 views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 03:14:48 ~

ሌሊቱ አንድ ቢሆንም ሁላችንም የየራሳችን ጨለማ አለን።
ተደሰትንም አዘንንም ሕይወት መቀጠሏ አይቀርም።

ዱንያ…
574 views00:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 23:10:19 بسم الله الرحمن الرحيم

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

_ውድና የተከበራችሁ ኢትዮጲያዊን በአማራ ክልል በኦሮሚያ ዞም በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጨፋ ሮቢት ፣ ዲዶ ፣ ደልጎ ፣ጭሪ አከባቢ *ቤታቸውን ንብረታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ከጎናቸው እንቁም* በሚል መሪ ቃል ግሩፕ ከፍተን ለተጎዱ ወገኖቻችን የገዘብ ስብሰባ ጀምረናል ማህበረሰቦቹ ገበሬዎች አርብቶ አደር እንደመሆናቸው በቤታቸው ያስቀመጧትን ለአመት ቀለብ ትባቃናለች ያሏትን ንብረት ሳይቀር ነው ያጡት በሁን ሳኣት ችግር ላይ ናቸው እናም ይሄን በመገንዘብ ሁላችሁ እንድትረባረቡ ጥሪ እናቀርባለን።_

https://chat.whatsapp.com/HkZAvkd55St0LLJQdXZMTu
679 views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 05:44:23 የመስሩርና የመቅሩር ታሪክ

ክፍል አስራ ዘጠኝ

የሚፈራርሱት ተራሮች


አንድ ላይ እጅብ ብሎ የሚነጉደው ሕዝብ ወደ ሰንሰለታማዎቹ ተራሮች እየተጠጋ ነው መስሩር ከጥቂት ጊዜ በፊት ባየው የባህሩ መቃጠልና የውሃው ማዕበል የእሳት ነበልባልና ጪስ መትፋት ግራ በመጋባት በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄዷል መቅሩርን በተመለከተ አሁን በሁለም ነገር እርግጠኛ እየሆነ መጥቷል። ሞቶ መነሳቱም ለእርሱ እውነት ነው አዎ ከሞት በኋላ ሌላ ሕይወት ይቀጥላልና
ሆኖም አንድ መስሩርን የመሰለ ግለሰብ እየተካሄደ ስላለው እውነታና አጠቃላይ እየተናጋ ስላለው የአጽናፈ ዓለሙ ሥርዓት እንዴት አድርጐ ሊገባው ይችላል በዚህ ስሜት ውስጥ እያለ መስሩር ወደ መቅሩር ጠጋ አለ ወደ እርሱ ቀረብ በማለት የደኅንነት ስሜት እንዲያድርበት የፈለገ ይመስላል ከዚያም አሁን ምን እየተካሄደ ነው ያለው? ዓላማውስ ምንድን ነው? ሲል መቅሩርን ጠየቀው፡፡


መቅሩርም ይህማ ዕለተ ትንሳኤ (የቂያማ ቀን ነው አለው መስሩር ይቅርታ በግልጽ በመጠየቅ መቅሩርን ያነጋግረው ጀመር “አየህ! አንተ ያኔ እውነቱን ነበር የተናገርከው እኔም በሳለፍኩብህ የሞት ቅጣት ብያኔ እንዳልተቀየምኸኝ ተስፋ አለኝ አለው ՈዚՍ ጊዜ መቅሩር ምንም ከተሰማው አነስተኛ የሆነ የክብር አስገራሚነት ነበር ስሜቱን የማረከው የሞት ቅጣት ከመወስንና ይህንኑም ሊያደርስበት ይችላል? ምንም ቃል አልተነፈሰም መንፈሱ ( የበለጠ የሁኔታው ይኸ ሰው ምን እያለ ነው? ከማስፈፀም በላይ ምን በደል አለ መስሩር ግን የመቅሩርን ዝምታ እንደ ድብቅ የጠላትነት ስሜት ነበር የቆጠረው::

ከዚያ በኋላ እየተቆናጠረ ከአጠገቡ ዘወር አለ ጥልቅ በሆነው ስሜቱ ውስጥ እየተገነዘበው እንደመጣው ግን ታላቅ አደጋ ወደፊት እንደሚጠብቀው ግልጽ እየሆነለት ነው:: ለብዙ ጊዜያት ከሚከታተሉት ኃይላት ለማምለጥ ሞክሮ ነበር አንዳንድ ጊዜ በድንገት ወደ ቀኝ ወደ ግራ ቢንጋደድም እንዲሁም ጥቅጥቅ ባለው:: የሰው አጀብ ውስጥ ገብቶ ለመጥፋት ቢሞክርም ፈጽሞ አልቻለም በሌላ ጊዜ ደግሞ በፈጣን ሩጫ ለማምለጥ ይሞክራል


በመጨረሻ ግን ያረጋገጠው ነገር ቢኖር ማንኛውም እንቅስቃሴውን በንቃት የሚከታተሉት ጠባቂዎች ውልፍት የማያደርጉት መሆኑን ነው በሄደበትም ሆነ በቆመበት ቦታ ሁሉ ከኋላውና ከፊቱ እንደጥላው የሚከተሉት ኃይሎች ፍፁም የሚላቀቁት አይመስልም እየተከታተሉ በእርግጥ እነዚህ ኃይላት በተለዬ ሁኔታ የማይለቁት መሆኑን ያወቀው መስሩር ፍፁም ተስፋ መቁረጥና ውድቀት ይሰማው ጀምሯል። እንደዚያም ቢሆን ግን ጨርሶ ተስፋ ላለማጣት ወስኗል።


ድንገት አንድ ሐሳብ ብልጭ አለለት አዲስ የመጣለት ሐሳብም እርዳታ እንዲደርስለት የማድረግ ዘዴ ነው። ሐሳቡ ፍፁም ቂልነት የተሞላበት ቢሆንም ጭንቀት የወለደው ነበር የሠራዊቱ ኃላፊ የሌሊት ዘበኞቹ አለቃና የደኅንነቱ ኃላፊ ከጐኑ የሚገኙለት ከሆነ አሁን የሚታየው ነገር ሁሉ መቀያየሩ አይቀርም ብሎ አምኗል። በመጨረሻም በእነዚህ ኃይሎች መገኘት ሰበብ ፍፁም ሰላም የእርሱ እንደሚሆን እርግጠኛ ነው ከዚያ በኋላ ዙሪያ ገባውን በዓይኑ እያማተረ ይፈልጋቸው ጀመረ ከብዙ ሙከራ በኋላ ነበር ፍለጋው ከንቱ መሆኑን በማመን ተስፋው የተሟጠጠው በእዚህ ሁሉ ወፈ ሰማይ ሕዝብ መካከል አንድን ሰው ፈልጐ ማግኘት መርፌን በጭድ ክምር ውስጥ ፈልጐ ከማግኘት ያልተናነሰ እጅግ አድካሚ ጉዳይ ነው። ለነገሩስ ቢያገኛቸው ምን ሊረቡት እነሱም በሌላ ጠባቂ ተወጥረው ተይዘዋል። ወዴት ሊኬድ? ምን ማምለጫ አለና?


እነ መስሩር የሚገኙበት የሕዝብ ክምችት እየተመመ ወደሰንሰለታማዎቹ ተራሮች ሲቃረብ አንድ የሚያጓጓ ትዕይንት ተከሰተ ይኸውም ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የማይታይ እጅ እነዚያን ተራሮች ከነበሩበት ቦታ አንስቶ ወደ ላይ በማንሳፈፍ ያ ሕዝብ የሚያልፍበት መንገድ ሰፊና ዘና ያለ እንዲሆን ማድረጉ ነው፡፡

የሰው ልጅ ዓይኖች ሁሉ ይህን ትንግርታዊና የሚያስፈራ ትዕይንት ለማየት ወደ ሰማይ ቀና አሉ ተራሮች ልክ ደመናዎች ብዙም ልብ ሳይባሉ እንደሚያልፉት በሰዎቹ አናት ላይ በመንሳፈፍ አለፉ ከዚያ በኋላም ወደ ብናኝ አቧራነት መለወጥ ጀመሩ። ይህ ሁኔታ በተከታታይ የፍንዳታና የመፈረካከስ ሂደት በመታጀብ ከቀጠለ በኋላ ተራሮች ወደ አለመኖር ተሸጋገሩ ተራሮች ከተነሱ በኋላ ምድር አባጣ ጐርባጣ የማይገኝባት ወለል ያለች ሜዳ ሆነች።


ሁኔታው ግን ቀላል አልነበረም ይልቁንም ልብን የሚያርድና መንፈስን በፍርሃት የሚንጥ ክስተት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ከጫፍ እስከጫፍ በተንጣለለችው ምድር ላይ ከመቃብሮቻቸ ተቀስቅሰው የሚግተለተሉት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕዝቦች ተሰራባት……
967 views02:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 17:00:35 ##የመስሩርና የመቅሩር ታሪክ##

ክፍል አስራ ስምንት

የባሕሮች መቃጠል


መስሩር በድንገት መራመዱን አቆመ። በዚህ ጊዜ አጅበውት ከሚሄዱት መልአኮች አንዱ ለምን መራመድ አቆምክ? ሲል
ጠየቀው ጠየቀ። መስሩር በብስጭት እንደተሞላ የት ነው የምትወስዱኝ? በማለት ከፊት ለፊቱ ሲሄድ የነበረው መልአክ ለዚህ ጥያቄው ምንም ዓይነት መልስ አልሰጠውም:: ከኋላው እየተከተለው የነበረው ግን እንደሚከተለው በማለት መልስ ሰጠው ሰውዬ ሁላችንም ትዕዛዙን አክብረን እየሄድን ነው፡፡

ከአሁን በኋላ ምንም ዓይነት ወለም ዘለም ማለት የለም ገባህ? ወደፊት ቀጥል መስሩር እንደታዘዘው ወደፊት ለመጓዝ ተንቀሳቀሰ መቅሩር በበኩሉ ከጐኑ እየሄደ ቢሆንም ጉዞው ግን ዘና ያለ ይመስላል። መቅሩር በጉዞው ላይ ፈጣሪውን በማውሳት ስራ ላይ ምላሱን አስጠምዶ ነው እየተራመደ ያለው እንዲህ እያለ አላህን ይለምን ነበር ጌታዬ አላህ ሆይ! እባክህ እርዳኝ መቅሩር እንደ መስሩር ሁሉ ከፊቱና ከኋላው እንደጥላው ያጀቡት ኃይሎች እንዳሉ የተገነዘበ ቢሆንም ብዙም የተረበሸ አይመስልም።


መቅሩር ከሁለቱ አንዱን በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ እንዲህ በማለት ጠየቀ ምን እየተካሄደ ነው ያለው ክቡራን?
ጠባቂዎቹም ሆነ ብለውና ትህትና ሳይጓደላቸው “ይህ የፍርዱ ቀን የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው አሉት
ይህ አስፈሪ የሆነ ትዕይንት የመጀመሪያው ምዕራፍ ከሆነ የመጨረሻው ምን ሊሆን ነው? አለ መቅሩር
መላእክቱም ለዚህ አስተያየትና ጥያቄ መልስ ሳይሰጡ ቶሎ በል ፍጠን! በማለት ጉዟቸውን ቀጠሉ
ከአንዱ የሰዎች ስብስብ በኋላ ሌላ ከአንዱ ብሄር በኋላ ሌላው ብሄር እንዲሁም ከአንድ ሕዝብ በኋላ ሌላ ሕዝብ እየተግተለተለ ይተምማል።


ምድር ከመቃብሮቻቸው እየወጡ በሚተራመሱ ሰዎች ተጨናነቃለች ይህ የሚያሳየው ሁኔታው የአጽናፈ ዓለሙ ህልውና ማብቃቱንና የፍርዱ ቀን መቃረቡን የሚያሳይ ታላቅ ምልክት መሆኑን ነው፡፡

እየተተራመሰ ወደ አንድ አቅጣጫ ከሚነጉዱት ሕዝቦች ውስጥ አንድ ሰው እንዲህ በማለት ጮኸ ተመልከቱ ተመልከቱ ያንን ባሕር ብዙ ዓይኖች ሰውየው ወደጠቆመው ባህር ተወረወሩ በሚደንቅ አኳኋን ባህሩ እየተቃጠለ ነው ባህሩ ቤንዚን እንደሆነ ሁሉ እየተንቀለቀለ ይጦፋል። የባህሩ ውሃ እንደ እሳተ ገሞራ ነፋሪት ወደሰማይ እየተምዘዝገ ይወጣና መልሶ ይወድቃል በመቀጠልም እየተንጫረረና እየተረጨ ይጨሳል። ከዚያም የእሳት አሎሎ በመስራት እየተወነጨፈ ከተቀጣጠለ በኋላ አየሩን ወደ ሰማያዊነት በመቀየር ይትጐለጐላል።

መስሩርና መቅሩር በዚያ ሁልቆ መሳፍርት በሌለው ሕዝብ መሃል ቆመው እየሆነ ያለውን ነገር ፈዝዘው ያስተውላሉ በምድር ዓለም በነበሩበት ጊዜ የሚያውቁት ውሃ እሳትን ሲያጠፋ ነው:: ዛሬ ግን ሁኔታው የተገላቢጦሽ ነው የሆነው ውሃ እሳትን እያንቀለቀለ ሲያስጮኸው ተመለከቱ ከዚያ በኋላ ሁሉም ወደሚሄድበት አቅጣጫ መንቀሳቀስ ጀመረ
እንደመብረቅ ከየመቃብሮቻቸው ውስጥ እየፈነቀሉ የሚወጡት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው የሚሄደው፡፡


ሁኔታውን ሲያስተውሉት መቃብር የሚተፋውን የሰው ልጅ ቁጥር መገመት ከባድ ነው ወንዶች፣ ሴቶች ፣ ህፃናትና አረጋውያን እንዲሁም የተለያዩ ቀለማት የፊት ቅርጽ ፣ ቋንቋ ምኑ ቅጡ ሁሉም በክረምት ወቅት ከመሬት እንደሚወጣ አሸን ይርመሰመሳል በዚህ ሁሉ ሕዝብ መሐል ያሉት መስሩርና መቅሩር በጉዟቸው ላይ ሁልጊዜም የሚራራቁት በትንሽ ጫማ ብቻ ነው የዚያ ሁሉ ወፈ ሰማይ ሕዝብ መጨረሻ እንዳይታይ ከአድማሱ ጥግ ያሉት ሰንሰለታማ ተራሮች ሰልፉን ያዘበራርቁት ጀምረዋል።


ይቀጥላል…
191 views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 23:46:04 የመስሩር እና የመቅሩር ታሪክ

~ ክፍል አስራ ሰባት

የሙታን ከየመቃብሮቻቸው መነሳት


ምድር በልቧና በሆዷ ያስቀመጠቻቸውን ሁሉ ከየማዕዘናቱ የምድር ከርስ የወጡ ሙታን ሁሉ ዳግም ህያው ሆነው ተቀሰቀሱ ከዚህ በኋላ ነፍሶች ከአካሎቻቸው ጋር በፍጹም አይለያዩም። ለብዙ ዘመናት ተቋርጦና የተረሳሳ መስሎ የነበረው የአካልና የህሊና ግንኙነት ድሮ እንደነበረው ያለምንም እንከን እንዲቀጥል ተደርጓል። ይህ ማለት ሰውየው ሲሞት አብሮት የነበረው ህሊናው የማስታወስ ችሎታው፣ ትዝታው ሁሉም ነገሩ እነደገና ተመልሶለታል ማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ ሁሉ እርቃኑን በባዶ እግሩና
አቧራ እንደለበሰ ከተኛበት ቦታ ተነሣ።


በዚህ ሁኔታ መስሩር ከሞተበት የመቃብር ስፍራ ሲቀሰቀስ መቅሩርን ከጐኑ ቆሞ ተመለከተው፡፡ መስሩርም በማመናጨቅ መልክ አንተ ማን ነህ? እዚህስ ምን ታደርጋለህ? በማለት ጠየቀው። መቅሩርም የፈጣሪ ያለህ ሞተን አልነበረም እንዴ? አለ የመቅሩር ቃላት መስሩርን ድንገተኛ በሆነ ፍርሃት ናጠው፡፡


ከዚያም መስሩር ፍርሃቱን መደበቅ እያቃተው ፊትህን ሳስተውለው ከዚህ በፊት የማውቅህና አዲስ አልመስልህ አለኝ። አንድ ጊዜ በክህደት ወንጀል ከሰንህ ነበር ልበል? አለ።


መቅሩርም ሲመልስ ልክ ነው በአንድ ወቅት በክህደት ወንጅላችሁኝ ነበር። ያ የተመሰረተብኝ ክስ ምክንያት ይኸው አሁን የምናየውን ከሞት በኋላ ስለመቀስቀስ ማመኔ ነበር” አለው፡፡


መስሩር በድንገት ሁኔታው ተለወጠ ከዚያም ኩራት በተላበሰ መንፈስ አንተ ሞኝ እንከፍ! አንተ እንደምትለው ሳይሆን እስካሁን የሚያስጠላ ህልም ውስጥ ነበርን። አሁን ገና መንቃታችን ነው የታለ የሌሊት ዘበኞቹ አለቃ? የደኅንነት ኃላፊውስ የት ነው? ይልጀመር።


መስሩር ይህን ከተናገረ በኋላ አቅሉን ሰብሰብ አድርጐ ስለ መቅሩር ሁኔታ ማሰብ ጀመረ። መቅሩር አሁን እየተናገረው ያለው ነገር ምናልባትም እውነት ሊሆን ይችላል። እውነትም ሞተው የነበረ መሆኑ ሀቅ ይሆናል እርሱ እንደሚያስበው የሚያስጠላ። ህልም ላይሆን ይችላልኮ ደግሞም ባይሞቱ ኖሮ ራቁታቸውን አይቆሙም ነበር።


አሁን ሁኔታውን ሲያስበው ያ እንግዳ የሆነ ፍጡር ለሁለም የሰው ዘር የማይቀር ነው እያለ እንዲጐነጭ የሰጠውን የሞት ጽዋ ቅዥት ወይም የሚያስጠላ ህልም ነበር ለማለት እንዳማይቻል ተገነዘበ። ከሁሉም በላይ በመቃብር ውስጥ ያጋጠመው በቃላት የማይገለጽ ስቃይ ህልም እንዳልሆነ እርግጥ ነው፣ ሁኔታውን አሁን እያገጣጠመ በአእምሮው ሲመረምረው እንደተባለው ሞቶ እንደነበርና አሁን ደግሞ ከመቃብሩ መቀስቀሱን ማመን ጀምሯል።


ይህ ሃሳብ እውነት መሆኑ ከፍተኛ የፍርሃት ዝንቅ ውስጥ ከተተው መስሩር ስለመቅሩር ጉዳይ ሲያስብ በቅጽበት የመፀፀት ስሜት ወረረው አሁን ሲያስታውሰው ይህን መሣይ ምስኪን ሰው አደጋና ሴራ ደቅኖብኛል ብሎ ማመኑ ምንኛ የማይመስል ነገር ነበር! እንዴትስ የሞት ቅጣት እንዲወሰንበት ተደረገ? በመቅሩር ላይ የተወሰነው የሞት ቅጣት በችኰላ የተፈፀመ መሆኑን ቢያምንም በሌላ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩና የደኅንነት ኃላፊው ያቀረቡትን ሪፖርት በመፃረር የሰውየው ንፁህነት መቀበል ደግሞ በጊዜው ከባድ እንደነበር አስታወሰ


አሁን መስሩር በደመነፍስ ወደ አንድ አቅጣጫ እየተጓዘ መሆኑን ልብ አለ። ዙሪያውን ሲያማትር በሺዎች የሚቆጠሩ ሙታን እንደርሱ ራቁታቸውን እየተግተለተሉ ወደ መሰብሰቢያው ምድር እያመሩ ነው። መስሩር ራሱን እንዲህ እያለ ይጠይቅ ነበር “እንዲህ እየተጣደፍኩ ወዴት ነው የምጓዘው? ማንስ ነው የቀሰቀሰኝ? ልብሶቼ የታሉ ቤተ መንግስቴስ የት አለ? አገልጋዮቹና ወታዶሮቼስ? ለመሆኑ ከሞት እንድነሳ ትእዛዝ የሰጠው ማን ነው? እግሮቼ እንዲንቀሳቀሱ ያደረገው ማን ነው? ጠቅላላ ስልጣኔና ክብሬን ማን ወሰደብኝ?


መስሩር አሁን መላ ቅጡን ባልለየው ምስጢራዊ ሁኔታ እንደተወጠረ ባለበት ሁኔታ ሁለት እንግዳ የሆኑ ፍጥረታት አብረውት እየተጓዙ እንደሆነ አስተዋለ
ከሁለቱ አንደኛው ከፊት ለፊቱ ሆኖ ያለምንም ድምፅ እየመራ ወደ አንድ አቅጣጫ እየወሰደው ሲሆን ሌላው ደግሞ ከኋላው ሆኖ እየተጠባበቀው ይጓዛል። ሁኔታቸውን ሲያጤነው ልክ እንደ በከባድ ወንጀል ተከሶ የተፈረደበት ሰው በሚጠበቅበት አኳኋን ነው በጥብቅ አጅበውት የሚሄዱት። መስሩር አሁን ያረጋገጠው ሀቅ እንደፈለገና በመረጠው ሁኔታ መጓዝ እንደማይችል ብቻ ሳይሆን ማምጫ በሌለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር የወደቀ መሆኑንም ጭምር ነው……

ይቀጥላል
573 views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 23:35:34 የመስሩርና የመቅሩር ታሪክ

~ ክፍል አስራ ስድስት

አለቀ ደቀቀ እና . . .


አንድ ዓመት አለፈ መቶ ዓመታት ጭልጥ ብለው ነጐዱ ሺህ ዓመታትም እንደዘበት ተቆጠሩ። በየመቃብሮች ውስጥ ያሉ ሙታን ድቅቅ እምሽክ ብለው ወደሙ። በመጨረሻም አቧራና ትቢያ ብቻ በየጐድጓዶቻቸው ቀረ በአንድ ወቅት የሙታን የመቃብር ስፍራዎች ከተሞች እየሰፉና እየተለጠጡ ሲመጡ ችምችም ያሉ ቤቶች ተሰሩባቸው ፈራርሰው ቤቶች ማረፊያ የነበሩ እነዚያም ለመቃብርነት ተከለለ በተራቸው ቦታው ተመልሶ


ይህን የመሰለው የሰው ልጅ በአፀደ ነፍስ ወደዚች ዓለም ከመጣባት ሰዓት ጀምሮ የሚከታተለው አዙሪት መልአኩ ከቀንድ የተዘጋጀውን መለከት(ጡሩምባ) እስኪነፋ ድረስ ቀጠለ ጠሩምባው በተነፋ ጊዜ ግን ከታላቁ ፈጣሪያችን አላህና እርሱ ከፈለጋቸው በስተቀር በሰማያትና በምድር እንዲሁም በመካከላቸው ያለ ፍጡር ሁሉ ጭጭ ምጭጭ ብሎ አለቀ ነፍስ ያላት ፍጡር ሁሉ ሞት ያገኛታል። ሙታንም በያሉበት ቦታ ተከማቹ ሰማያትና ምድርም ብቻቸውን ቀሩ
ከነዋሪዎቻቸው ፀድተው ምንም ዓይነት ድምጽም ሆነ ማንሾካሾክ ሳይኖር ሁሉም ፀጥ ረጭ ብሏል።



አንድም ፍጡር የማይታይ ሲሆን በሰማያትና በምድር እንዲሁም በመካከላቸው ሁሉም ነገር ፀጥ ከማለቱ የተነሣ የሚሰማ ነገር ቢኖር የነፋሶች ሹክሹክትና ፉጨት ብቻ ነው፡
ሞት ሕይወት ያለውን ፍጡር ሁሉ አስገብሮ ጓዳ ጐድጓዳውን ሁሉ በማሰስ ድል መትቶታል ከአንዱና ሁሉን ቻይ ከሆነው ጌታችን አላህ በስተቀር ሁሉም ነገርና ፍጡር አለፈ ጠፋ። እርሱ ግን ዘመኑ መጨረሻ በሌለው ድካ ባልተበጀለት ልክ እስከዘለዓለሙ በዙፋኑ አርሹ ላይ እንደተደላደለ ይኖራል። በዚህ ሁኔታ ዘመናት ጭልጥ ብለው አለፉ።


ከዚያ በኋላ ኃያሉ አላህ አዝራኤል የተባለውን መልአክ በቀንዱ እንዲነፋ አዘዘው። እርሱም ቀንዱን (መለከቱን) ከነፋ በኋላ እንዲህ እለ የአላህን ትክክለኛ የሆነውን ኃያልነቱን አላወቁም። በፍርዱም ቀን ምድር በሞላ በጭብጡ አትሞላም። ሰማያት በጠቅላላው በቀኝ እጁ ይጠቀለላሉ፡፡ ጥራት ይገባው እርሱ ስዎች አጋር ከሚያደርጓቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው”


ሁለተኛው መለከት እንደተነፋ የፍርዱ ቀን መድረሱን ማብሰሪያ መሆኑ ታወቀ ከዚህ በኋላ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ረዥሙ ቀን ጀመረ ከዚህ ሁሉ በኋላ ሰማያት፣ ምድርና ተራሮች ፍርስርስ እንክትክት ብለው እንደ አቧራ በመቡነን ጠፉ የሰው ልጅ ብቻ ስለዚህ ከላይ ስለተጠቀሰው አማና(ዲን) ሊጠየቅ ከሙታን ዓለም ተቀሰቀሰ ይህ ዓለም በተለይም ሰማያትና ምድር ፍርስርሳቸው ሲወጣ የታየው ታላቁ ትዕይንት እጅግ ወደር የማይገኝለት አስደንጋጭና አብረክራኪው ነው።


ይህ ታላቅ ቀን የጀመረው አጽናፈ ዓለሙን ሲገዙትና ሲመሩት የነበሩትን የተፈጥሮ ሕግጋት በማፋለስና በማጥፋት ነው ዋና ዋና የሚባሉት ከእነዚህ የተፋለሱ ሕግጋቶች አንዱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ስርዓተ ፀሐይን ( ጨምሮ / የሁሉንም ተንቀሳቃሽ የሰማይ አካላት አስማምቶና አዋድዶ ያኖራቸው ደንብ ሲሆን በዚሁ ጦስ የሰማይ አካላት እየተገጨና እየተርገፈገፉ ፈራርሰው ቡናኝ እንዲሆኑ ተደረጉ።


እጽናፈ ዓለሙ መፈራረስና መበላሸት በጀመረበት ቅጽበት ሙታን ሁሉ ከያሉበት ተቀስቅሰው ልዩ በሆነች ዝግጁ ምድር በአላህ ፈቃድ ለመሰብሰብ ተንቀሳቀሱ ሙታን በየመቃብሮቻቸው ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዑደቶች ተካሂደውባቸው ፍፁም ተቀይረውና ተለዋውጠው : ከአንዱ ዓይነት ይዘት ወደሌላኛው ሊሸጋገሩ ኖረው እንደገና ተቀሰቀሱ ስጋ ደምና አጥንት በዘመናት ሂደት ከአፈርና ከአለት ጋር ተቀይጠው በመሬት ልብ ውስጥ ወደ ድንጋይ ከስልና ሌላም ማዕድንነት ተቀይረው የተረፈውም ወደ አቧራነት ተለውጧል ይህ ሁሉ ሂደትና ኡደት ቢፈጠርና ሁኔታዎች ለብዙ ዘመናት ቢቀያየሩም። የሰው ልጅ ከምንምነት ወደ ህያወነት እንዲመለስ እርግጥ ሆነ መጀመሪያውኑስ ካልነበረበት በእናቱ ማህፀን በኩል ወደዚች ዓለም እንዲመጣ ሆኖ የለምን?

ይቀጥላል……
608 viewsedited  20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 06:23:59
~

መውደቂያሽን አበጅተው መልካም እድል የሚሉሽ እልፍ ናቸው። መሰላልሽን ደግፈውልሽ እይታሽ የማይደርስባቸው ጥቂቶችም አሉ። ዱንያን በሁለቱ መሐል ቃኚያት።
ABX

ሰብሃል ከይር
1.2K views03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ