Get Mystery Box with random crypto!

አንዱ ካንዱ የሚሸሽበት ቀን ፀሐይ በየደቂቃው እየቀረበች ግለቷም እያየለ ሲሄድ ምድር ደግሞ በበ | ወርቃማ ንግግሮች

አንዱ ካንዱ የሚሸሽበት ቀን


ፀሐይ በየደቂቃው እየቀረበች ግለቷም እያየለ ሲሄድ ምድር ደግሞ በበኩሏ እየተስፋፋችና እየተንሰራፋች መጣች። ፍጥረት የተባለ ሁሉ ከዚህ ጉድ ለማምለጥ መውጫ ቀዳዳ ባገኝ ብሎ ይራወጣል የሰው ልጅ ደግሞ አንዱ ካንዱ ሀቅ ለማምለጥ (ለመሸሽ ይሞክራል መስሩር ከመቅሩር ተለይቶ ወደ ግራ አቅጣጫ ሊያፈተልክ ጥረቱን ተያይዞታል የሰው ልጅ የዱር አራዊት ጅኖችና አእዋፋት እርስበርሳቸው ተደበላልቀዋል።


የሰማይ አካላት መርገፍ የተራሮቹ መንኮታኮት ሌላውም ጩኸትና ድብልቅልቅ ከፍተኛ ውጥንቅጥና ውድመት በማስከተሉ ምክንያት ፍጡር የተባለ ሁሉ ወዴት እንደሚሸሽ ባያውቅም እንዲሁ ባፈተተው እግሬ አውጭኝ በማለት ላይ ነው፡፡ መስሩርም እንደሌላው ሰው ሁሉ በርግጎ ልቡ አስኪጠፋ ሮጠ ይህን ያደረገውም አንድ ዓይነት ማምለጫ በመሻት ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ነገር ዋጋቢስ በሆነ ግርግር ከመታመስ በስተቀር ሽሽቱ ምንም ዓይነት ለውጥ አላመጣም። ይህን ያስተዋለው መስሩር በተስፋ መቁረጥ ሀሞቱ ፈሰሰ አሁን ሁኔታውን ቆም ብሎ ሲያስተውለው ያ ሁሉ ሩጫና ድካም ዓላማ የለሽ ሆነበት ምክንያቱም በዚያ ቀን መቆምም ሆነ መሮጥ የሚያስከትሉት የተለየ ነገር አልነበረምና ነው።


ሁለቱም ያው ናቸው ምን ማምለጫ አለና ወዴትስ ይሸሻል? በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ መስሩር በድንገት የወታደሮቹ አለቃና የደኅንነቱን ኃላፊ ከጐኑ ሲሮጡ አስተዋለ እንደ እውነቱ ከሆነ በዚህ ሰዓት ከፍተኛ ደስታ ነው በውስጡ የተሰማው በመሆኑም ጊዜ ሳያጠፋ በጩኸት ጠራቸው የወታደሮቹ አለቃ ወደ እርሱ ዘወር ሲል ፊቱ በስቃይ ተጠባብሶ አስተዋለው:: እንዲያውም እርሱንም በደንብ ያወቀው አልመሰለውም። መስሩር ከዚያ በኋላም የደኀንነቱን ኃላፊ ሊረዳኝ ይችላል - በማለት በጩኸት ጠራው እርሱ ግን እየት አድርጐት ሀይ ነፍሴ ወይ ነፍሴ እያለ በመጮህ ሩጫውን ተያያዘው ከዚያም መስሩርን እየተራገመና እየተሳደበ ከአዓይኑ ተሰወረ መስሩር በመንፈሱ ውስጥ ብቅ ብሎ የነበረው የደስታ ስሜት በአንድ ጊዜ ከውስጡ ተንኖ ሲጠፋ በምትኩ የተለመደው ፍርሃትና ጭንቀት መልሶ ነገሰበት



ተስፋ ማድረግ ካለማድረግ ይሻላል በማለት እንጅ ኃይልና ስልጣኑ እንደከዱት መስሩር ከተገነዘበ ቆይቷል። እንዲያውም አሁ ራሱን እየቆጠረ ያለው በትልቅ ወጥመድ እንደተያዘች አይጥ ረዳት የለሽ አድርጐ ነው በመሆኑም ያለ አንዳች ዓለማ መሮጡን ቀጥሏል። አንድ ጊዜ ወደ ግራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ቀኝ በማለት እያለከለከ ይከንፋል በዚሁ ሩጫው ላይ እያለ እናቱና አባቱ ባጠገቡ ሲያልፉም እንዳላየ በመሆን ምንም ሳይላቸው ቀጠለ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም የዘበኞቹ አለቃ በአጠገቡ አለፉ። እነርሱ ግን በጣም የደነገጡና ቅስማቸው ድቅቅ ያለ መሆኑ ያስታውቃል።



አሁን መስሩር በሚገባ የተገነዘበው ነገር ማንም ከዚህ ጉድ እንደማያስጥለው ሲሆን እርሱም በበኩሉ ከወንድሙ፣ ከእናቱ ከአባቱ እንዲሁም ከልጆቹ ለምን እንደሚሸሽ ግልጽ ሆኖለታል። ከዚህ በኋላ በፍርሃት ተሸንፎ ከመርበድበድ ውጭ ሌላ የተሻለ ነገር እንደማያገኝ ውስጡ ነግሮታል። አሁን እንግዲህ ከራሱ የሚሸሽ እስኪመስል ድረስ ያለምንም ተስፋ መሮጥ እጣፈንታው ሆኖአል
የዕለተ ቂያማ አስፈሪነት መስሩር ከድንጋጤ ጋር ድርና ማግ ሆኖ እንደተሰራ ሁሉ መላ እርሱነቱን ፍፁም ቀይሮት መላ ቅጡ የጠፋው አዲስ ጅምር እብድ አስመስሎታል።


ይህ ቀን መስሩር ብቻ ሳይሆን ከመቃብር አብሮት የተቀሰቀሰውን መቅሩርንም ግራ በማጋባት ያለማቋረጥ ጌታውን እንዲማፀንና ይህንን ውጥንቅጡ የወጣ የመከራ ድርድር ከፊቱ ዞር እንዲያደርግለት እንዲለምን አድርጐታል።
ሌላው አስደናቂው ክስተት በዚህ አስደንጋጭ ቀን የጅኖች መላና ኃይል ሁሉ ከላያቸው ላይ ተነስቶ ፍፁም ምስኪንና ረዳት የለሽ ሆነው መታየታቸው ነው። በተከሰተው ከባድ ሁኔታ ተደናብረው ከሚሸሹት የሰው ዘሮችና የዱር አራዊት ጋር ተቀላቅለው ባፈተተው መንጎዳቸው ለዚህ ሁኔታቸው እንደ አንድ ትልቅ ማስረጃ ሊጠቀስ ይችላል። በሌላ በኩል የዱር አራዊቱ በሰው ልጅና በጅኖች ላይ ጥገኛ በመሆን በመጠኑም ቢሆን ደህንነት የተሰማቸው መስሏቸው ነበር። ይሁን እንጂ የሁኔታውን መክፋት ተከትሎ በተለይም የሰው ልጆች ለማምለጥ ሲራኰቱ፡ ሲያስተውሉ ፍፁም ድንጋጤ ነበር የዋጣቸው።

ምድር ይበልጥ እየሰፋችና እየተዘረጋች ነው የምትሄደው፡፡ በአኳያውም ፍጡርን በሙሉ በየጊዜው እየተባባሰ የሚሄድ ተስፋ መቁረጥና ድንጋጤ እየዋጠው ሲሄድ ይታያል።


ኢንሻ አላህ ይቀጥላል…