Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-17 05:46:38 በእናቱ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቀ። ዕድሜው ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናቱን ቀበረ።
በስምንት ዓመቱ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጉት አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው። እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት። ያ ፈታኝ ጊዜ "የሀዘን ዓመት" ተብሎ ተሰየመ።

ይባስ ብሎ ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።

ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው።

ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች። ታሪክ ክስተቱን በደማቅ ፃፈ።

ግንባሩን ከመሬት ሰይሞ ከፈጣሪው ጋር በለሆሳስ ሲያወጋ የመካ ሙሽሪኮች በትከሻዎቹ መሃል የግመል አንጀት ከደም ጋር ቀላቅለው ሲያፈሱበት ግንባሩን ከመሬት ለአፍታ አላነሳ።
 
በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር ይቅር ባይነት የዘወትር ስንቁ ነበር። ስቃይ በተሸከመው አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ለሊቱን በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል። 

ልቦቻችን ውሃ እንዳጣ የዓረቢያ ምድረ በዳ ስንጥቅ በዝቶባቸዋልና ፈለግህን በመከተል በፍቅር ይረሰርሱልህ ዘንድ ደጋግመህ ሰለዋት አውርድ።
ሰለዋቱ ረቢ ወተስሊማቱሁ ዓለይሂ የአላ አሊሂ ወሰህቢሂ ወሰለም
2.0K views02:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-16 01:05:33
እነሆ የፉአድ ሙና ከተወደደለት ምርጥ መፅሀፍ ኢፋዳ የተሰኘው መፅሀፍ በኢማራት ገብታለች።

ይህ መፅሀፍ የማንበብ ፍላጎት ከማነሳሳት አንፃርም እንደ ሙስሊም ደግሞ ለኢማን ልብ ያገራል።

አፃፃፉ የራሱን ዘይቤ እና የማንበብን ፍላጎት የሚከፍት ነው።

ኢስላማዊ ዘውግ የያዘ ብዙ ትምህርት ቀንጭበን የምናልፍበት ግሩም መፅሀፍ ነው።


መፀሀፉን ኡዝታዞች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች አንብበውት ወደውት እንድናነበው ይመክራሉ በተለይ በዚህ በድርቅ ለተመታ ትውልድ።

በዋትስ አፕ = 0501949692
በቴሌግራም = @Ibnu_Mohammed

ኦርደር ማድረግ ትችላላችሁ ካላችሁበት ድረስ ከቤታችሁ ይመጣል።
2.0K viewsedited  22:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 18:15:31 አንተ አብደላህ ሆይ ከሰዎች መሀል አላህ ዘንድ በላጩ ማን እንደሆነ አታውቅምና ሰውን አትናቅ፣ አትተችም ፤ ነውሩንም ቢሆን እግር በእግር አትከታተል። ምን አልባት ዛሬ ላይ ከሰጋጆች ጎን ተሰልፈህ ይሆናል። ከቁርአንም ጋር ያለህ ግንኙነት የሚያምር፣ የሚያስደስት ይሆን ይሆናል። ምላስህም ብትሆን አላህን ከማውሳት ቦዝና አታውቅ ይሆናል። ወላሂ አብደላህ የነገን ግን አታውቅም!፣ ማናችንም አናውቅም!።

ጌታችን مقلب القلو ነው። ልብን እንዳሻ የሚገለባብጥ። ዛሬ ልባችን አላህን በማውሳት ትረካ ይሆናል ፤ የነገን ግን አናውቅም። ታዲያ ለምን ነው ሰዎችን የምንንቀው። ለምንስ ነው እነሱን እያማን ኸይር ስራችንን ለእነሱ አሳልፈን የምንሰጠው።

ሀቢቢ! ዛሬ ኸይር ቦታ ቆመህ ይሆናል። ዛሬ በአላህ መንገድ ላይ ሆነህ ይሆናል። ይሄን የቆምክበትን ኸይር ነገር ለሰዎች አሳውቃቸው። ያገኘኸውን ደስታ ሰዎችም ያገኙት ዘንድ ጋብዛቸው። አንድ የምታውቃት የረሱል (ሰ•ዐ•ወ) አንቀፅ ካለች ለሰዎች አድርስላቸው። بلغوا عني ولو ايه ብለውንም አይደል።

አላህ በጭንቁ ቀን (በዕለተ የውሙል ቂያማህ) ጭንቀታችንን እንዲያነሳልን ከሻን በዱንያ ላይ በቻልነው አቅም የሙዕሚን ወንድሞቻችንን ጭንቀት እናንሳ። ነውራችንን እንዲደብቅልን ከሻንም በዱንያን ላይ ነውራቸውን እንደብቅላቸው። የወንድሙን ነውር የደበቀ አላህ በዱንያም በአሄራ ነውሩን ይደብቅለታል ብለዋል እና ነብያችን ሙመሀመድ (ሰ•ዐ•ወ)።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር
2.1K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 21:28:22 አጣሁት የምትለው ልጅም ሆነ ንብረት ባለቤቱ አላህ ነው፤ ቢኖረኝ ብለህ የምትመኘው ሪዝቅ ካዝናው አላህ ዘንድ ነው፤ በድሎህና ጎድቶህ የሄደ ሰው የአላህ ባርያ ነው፣ ተሸክመህ የምትዞረው ሀሳብ ከአላህ ነው፣ ወደፊትህን ብትፈራው በአላህ እጅ ነው፣ መጨረሻህ ቢያሳስብህ አዋቂው አላህ ነው፣ ቢሰጠን የሱ ነው፣ ቢከለክለንም የራሱን ነው፣ ቢያቆየን መብቱ ነው፣ ቢወስደን ንብረቱ ነን።
ያገኘነው፣ ያጣነው፣ የምንመኘው፣ የምንናፍቀው ሁሉ የሱ ነው፡፡ ከሱ ሆነን ወደርሱም ሆነን አላህ ይጎዳናል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው፡፡ ምድር ላይ አስገኝቶን ያለ ልጅ ያለ አጋር ያለ ወገን ብቻችንንም ይተወናል ብሎ ማሰብ ኢማን ማጣት ነው፡፡

ድንግሏ መርየም ወለደች፣ መሃኗ ሳራ ልጅ አገኘች፣ ዘከርያ ማምሻ ዕድሜው ላይ አላህ ብቻዉን አልተተወም፣ ዒሳ አንቀልባ ዉስጥ ሆነው ተናገሩ፣ መቶ ዓመት በላይ የተኙ ወጣቶች ከእንቅልፍ ነቁ፣ አላህም ለነቢ ሙሳ ባህርን ከፈለ፣ እሣት ነቢዩ ኢብራሂምን አላቃጠለችም፣ ነቢ አዩብ በዓመታት በሽታ ወድቀው አልቀሩም፣ ዓሳ ነባሪ ነቢ ዩኑስን ዉጦ አላስቀረም፣ ነቢ ሙሐመድ ከምንም ተነስተው ዓለምን አበሩ፡፡

በአላህ ላይ ሰፋ አድርገህ አስብ፣ በአምላክህ ላይ ትልቅ የቂን ይኑርህ፣ ባመጣህ ጌታ ላይ መጥፎ አትጠርጥር ፣ ዉስጥህን በጥሩ ሀሳቦች ገንባ፣ ኢማንህንም ከፍ አደርግ፣ እሱ ከሻው የማይሆነው የለም፡፡ አልሙ ተስፋ አትቁረጡ፣ ተጓዙ በጠዋት አትድከሙ፡፡
ከምንም ያስገኘን አላህ በችግሮች መሃል ፈጽሞ አይተወንም።

@MuhammedSeidAbx
2.4K viewsedited  18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 21:14:34 አላህ ባሮቹን በደረጃ አበላልጧል።ከፊሉን ነብይ ከፊሉን ሲዲቅ ከፊሉን ደግሞ ሷሊሕ አደረገ።ከፊል ባሮቹን ደግሞ በችሮታው የቀብር ቅጣት አንዳይኖርባቸው ደነገገ።

ማንኛውም ሙእሚን ግን ኢማኑ በቀብር ውስጥ ሳይፈተን ወደ ጀነት ሊገባ አይቻለውም።ስለሆነም ድንጋጌዎቹ የማይጋጩበት ጌታ ከቀብር ፊትና ነፃ ያደረጋቸውን ባሮቹን የቀብርን ፈተና እዚሁ ዱንያ ላይ እንዲፈተኑት አደረገ።

ይህ ጉዳይ በጣም የደነቀው ሰሓባ ታድያ ወደ ረሱላችን ﷺ ዘንድ መጣና ጠየቃቸው፦

«ሙእሚኖች ቀብር ውስጥ ሲፈተኑ ሸሂድ የማይፈተንበት ምክንያት ምንድን ነው? » ሲል ሚስጥሩን ለማወቅ በመጓጓት ጠየቃቸው ።

የአላህ መልእክተኛም ﷺመለሱለት፦
«ከጭንቅላቱ በላይ ሲያዋካ የነበረው የሰይፎች ፉጭት ድምፅ ከፈተና በቅቶታል» አሉት።

(ነሳኢይ 2052)

ሸሂዶች አላህ ዘንድ የላቀ ደረጃ ያላቸው ባሮቹ ናቸው። በርሱው መንገድ ላይ ለርሱ ቃል ልእልና ውድ ነፍሳቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡ ወዳጆቹ ናቸው። ስለሆነም ደረጃቸውን አልቆታል። ሽልማታቸውንም እጥፍ ድርብ አድርጎታል።

በዚህ ሐዲስ እንደተረጋገጠው ሸሂድ የቀብር ፈተና የለበትም።በቀብር ውስጥ ያለው ፈተና ሊቀርለት የቻለውም በካሀዲያን ፊት የመሳሪያ ጋጋታና ጩኸት ሳይበግረው ፀንቶ መፋለሙ የኢማኑ ማረጋገጫ ስለሆነ ነው።

የጂሃድ ፍልሚያ በፊልም እንደምናየው ቀላል አይደለም።የሰይፎች ቃቃታ፣የሚያጥወለውለው የጥይት ጋጋታ ፣ የሚያስገመግመው የታንክና የሞርታር ትርምስ ፣ ያረረ ሳንቡሳ አስመስሎ የሚጠብሰው የድሮን ሚሳኤል ፍንዳታ የሚደመጥበት የጭንቅና የፍልሚያ አውድማ ነው።

በዚህ ሜዳ ላይ ሊፀና የሚችለው በርግጥም እርሱ ኢማኑ የፀናና የማያወላውል ሙጃሂድ ብቻ ነው።

የዚህን አውድማ ከባድነትና አስጨናቂነት ለመረዳት አላህ ከቀብር ፈተና ጋር እኩል አድርጎ የቀብር ፈተናን መተኪያ ማድረጉ በቂ ነው። ስለሆነም አላህ በዚህ ሜዳ ፀንቶ ሲፋለም የተገደለን ባሪያ የቀብር ፈተናን ያለፈ ስለሆነ የቀብር ውስጥ ፈተናን ከርሱ ላይ አስወግዷል።

ሸሂድ የማንንም ምስክርነትና ዱዐን ስለማይፈልግ ተራ ሰው አይደለም ነብይ ራሱ በርሱ ላይ ሶላተል ጀናዛ እንዲሰግድበት አልፈቀደም። ሸሂድ ስራው ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት እንዳለው አላህ ዋስትና ሰጥቶታል።የኛ ቢጤ ተቀማጮች ግን ስራችን ተቀባይነቱ አልተረጋገጠልንም።

አላህ እንዲህ ይላል፦

« እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ሥራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸውም፡፡በእርግጥ ይመራቸዋል፡፡ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡ ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡»
(ሙሐመድ 4–6)

አላህ ሁኔታውን ያበጀለት ሰው በርግጥም የርሱን ፈተና ያሳልፈዋል!

ቴሌግራም፦ t.me/ismaiilnuru
2.1K viewsedited  18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-12 20:38:45 ያ ሸይኽ "እኔ ትዳር አለኝ፣ ሀብታምም ነኝ፣ አንዲት ሴት አለች። ከሐራም ለመጠበቅ በሚል ኒያ ባገባት ምን ይሆናል?" አላቸው።

ሸይኹም መለሱለት " ምንም አይሆንም፣ ነገርግን ገንዘቡን ለአንድ ደሀ ወጣት ስጥና ይጋቡ። በዚህ መልካም ሥራህ የሁለቱንም አጅር ትጋራለህ።" አሉት።

አምሽታችሁ ነው?
2.1K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-12 00:27:27
ህዝቡ በውሸትና በሃሰተኛ ምስክርነት ታዋቂ የሆነባት አንዲት መንደር ነበረች።

በዚህ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው በድብቅ ሊያገባ ከሸንጎው መሐል ገባ። ሸይኹ ምስክሮች ባሉበት ዘወጅቱከ ሲሉት ቀቢልቱ እያለ ጋብቻውን አፀደቀ።

ከወራት በኋላ ባል ሚስቱን ከቤት አስወጥቶ ሜዳ ላይ ጣላት። ስለክብሯ ሳይጨነቅ አመናጭቆ አባረራት። በገነች። እያነባች እጇን ወደ ሠማይ እንደዘረጋች ስሞታዋን ልታሰማ፣ ስለፍትህ ልትጮኽ ቃዲው ዘንድ ደረሰች።
"ምስክሮች በተጣዱበት በሐላል አግብቶኝ ሲያበቃ በበደል አረንቋ ማኖሩ ሳያንስ አዋርዶ አባረረኝ" በማለት ስሞታዋን አሰማች።

ቃዲው ባልየው ከነሁለቱ ምስክሮች እንዲገኙ ጠይቆ የተፈጠረውን ቢጠይቅ ልጅቷን እንደማያውቋት ምለውና ተገዝተው ተናገሩ። እንደውም ከዚህ ቀን በፊት አይተናትም አናውቅ በማለት ካዱ። በውሸት ላይ ተባበሩባት።

ዳኛው ሁለቱን ምስክሮች በጥልቅ ተመለከተና ወደ ሴትዮዋ ዞሮ "በባልሽ መኖርያ ግቢ ውስጥ ውሾች አሉን?" ሲል ጠየቀ።
"አዎ" አለች ዕንባዋን እየጠረገች።
"የውሾቹን ምስክርነት ትቀበያለሽን?" አላት ዳግም እየጠየቃት።
ግራ በመጋባት መንፈስ ውስጥ ተውጣ "አዎ" አለች።
"ውሰዷት ውሾቹ ከጮኹባት ውሸታም ናት፤ በዝምታ ወደ ቤቱ እንድትገባ ከፈቀዱላት የቤቱ ባለቤት ናት" አለ ዳኛው።
ምስክሮቹ እርስ በእርስ ተፋጠጡ።
"እነዚህም በውሻው ምስክርነት መሰረት ውሸታሞች ናቸውና ግረፏቸው" ሲል አዘዘ።

ውሾች ከህዝቦቿ በላይ ታማኝ የሆነባት መንደር ምንኛ ከፋች!!

ኮፒ ነው
2.2K views21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-11 23:45:06
~

በላጭ ሰው...
እውነትን በማወቅ ብቻ የሚብቃቃ ሳይሆን
ሌሎች ሰወችን እውነትን እንዲያቁ የሚያግዝ ነው!
2.0K views20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-09 23:09:36
ሙእሚን ሳያስብ አሊያም ተዘናግቶ ወንጀል ላይ ወድቅ ይችላል፤ ግና ፈጽሞ አይዋሽም፡፡ ያልሆነዉን ነኝ አይልም፣ በልቡ የሌለን በአፉ አይናገርም፡፡ ዉሸት እጅግ አስቀያሚ ባህሪ ነው፡፡ የሙናፊቅ ምልክትም ነው፡፡
የምትናገሩት ነገር ዉሸት መሆኑን እያወቃችሁ ለሰው አንዲትም ቃል አታውጡ፡፡ ልባችሁን አስቀምጣችሁ በምላስ አታውሩ። በዉሸት ቃላችሁ ላይ ህልማቸዉን የሚገነቡ ሰዎች ብዙ ናቸዉና፡፡ ቃል መከፈል ያለበት ዕዳ ነዉና፡፡ ላትፈጽሙላቸው ነገር ሰዎችን የተስፋ እንጀራ አታብሏቸው፡፡ የምናብ ኑሮም አታኑሯቸው፡፡
የሰዉን ቀልብ መስበር አጥንቱን ከመስበር በላይ ከባድ ነው፡፡ የሰው ልጅ ቀልብ አንድ ናት፤ ያች አንድ ልብ ከተሰበረች መጠገኑ ከባድ ነው፡፡ አጥንት ግን ብዙ መሆኑን ልብ በሉ፡፡
በመሀላ ቃል ገብተህ እንደዋዛ ቃልህን ስታፈርስ ጥፋትህን የሦስት ቀን ፆም ብቻ የሚያብሰው ይመስልሃልን!?፡፡ መስሎሃል። ቃል በማፍረስህ፣ እምነት በማጉደልህ፣ በማታለልና የሰው ዕድሜ በማባከን ጭምር ጥያቄ አለብህ፡፡ ጠብቅ ወላሂ፡፡

ዕድሜ ለሰው ልጅ የተሠጠው እንዲኖርበት እንጂ ሌሎች ሙድ እንዲይዙበትና እንዲጫወቱበት አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ነፍስ ክቡር ናት። ልብላሽ አልብላሽ እያለች ድመት እንደምትጫወትበት አይጥ አይደለችም።
ዒባዳዎች ከራስህ አንፃር ያጠፋኸዉን ጥፋት ያብሱልህ ይሆናል፤ ከሌላ አንፃር ያጠፋኸው ግን የበደልከዉን ሰው ዐፈውታ በመለመን ብቻ ነው የምትፈታው፡፡

በሰው ስሜትና ጊዜ የሚጫወቱ ሁሉ የእጃቸዉን የሚያገኙበት፣ በመጥፎ ሥራዎቻቸው የሚጎበኙበት ቀን እሩቅ አይደለም፡፡ ሰው ያስቀመጠዉን አንድ ቀን ማግኘቱ አይቀርምና፡፡ የባሮች ጌታ ሁሉን ነገር ያያልና።

ቲስበሑ
2.4K views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 04:58:01
ተማሪውያቸው መምሀሩን ሩሚን እንዲህ ሲል ጠየቀ፡፡ ፈጣሪን ማመስገን እፈልጋለሁ እና እንዴት ማመስገን እንደሚገባኝ ያስተምሩኝ…

ሩሚ ጠየቁት… የወፎች ዝማሬ ሰምተህ ታውቃለህ?

ተማሪው… በሚገባ መመህር ሆይ ዘወትር ማለዳ እሰማለሁ።

ሩሚም… ዎፎች ስለድምጻቸው ማማር የሚጨነቁ ይመስልሀል?

ተማሪያቸው… በፍጹም መምህር ሆይ ሲል መለሰ

ሩሚም… አየህ ፈጣሪን እንዴት ማመስገን እንዳለብኝ የተማርኩት ከወፎች ዝማሬ ነው፡፡ ወፎች የማለዳ ዝማሬን በተፈጥሮ የተቀበሉት እና ይህንኑ የሚፈጽሙ ፍጡሮች ናቸው፡፡ስለድምጻቸው ማማርም ሆነ ማስጠላት አይጨነቁም፡፡እኔም ፈጣሪዮን ለማመስገን የተቀበልኩት ድምጽ ከበቂ በላይ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ምስጋናዬን ሳቀርብ ሰዎች ምን ይሉኛል ወይም ሰዎች ይተቹኛል ብየ አላስብም ፡፡ እናም ፈጣሪ የሰጠህን ሰው መልሶ እንዲያስተምርክ አትሻ››በማለት አሰናበቱት ፡፡
341 views01:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ