Get Mystery Box with random crypto!

ህዝቡ በውሸትና በሃሰተኛ ምስክርነት ታዋቂ የሆነባት አንዲት መንደር ነበረች። በዚህ መንደር ውስ | ወርቃማ ንግግሮች

ህዝቡ በውሸትና በሃሰተኛ ምስክርነት ታዋቂ የሆነባት አንዲት መንደር ነበረች።

በዚህ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው በድብቅ ሊያገባ ከሸንጎው መሐል ገባ። ሸይኹ ምስክሮች ባሉበት ዘወጅቱከ ሲሉት ቀቢልቱ እያለ ጋብቻውን አፀደቀ።

ከወራት በኋላ ባል ሚስቱን ከቤት አስወጥቶ ሜዳ ላይ ጣላት። ስለክብሯ ሳይጨነቅ አመናጭቆ አባረራት። በገነች። እያነባች እጇን ወደ ሠማይ እንደዘረጋች ስሞታዋን ልታሰማ፣ ስለፍትህ ልትጮኽ ቃዲው ዘንድ ደረሰች።
"ምስክሮች በተጣዱበት በሐላል አግብቶኝ ሲያበቃ በበደል አረንቋ ማኖሩ ሳያንስ አዋርዶ አባረረኝ" በማለት ስሞታዋን አሰማች።

ቃዲው ባልየው ከነሁለቱ ምስክሮች እንዲገኙ ጠይቆ የተፈጠረውን ቢጠይቅ ልጅቷን እንደማያውቋት ምለውና ተገዝተው ተናገሩ። እንደውም ከዚህ ቀን በፊት አይተናትም አናውቅ በማለት ካዱ። በውሸት ላይ ተባበሩባት።

ዳኛው ሁለቱን ምስክሮች በጥልቅ ተመለከተና ወደ ሴትዮዋ ዞሮ "በባልሽ መኖርያ ግቢ ውስጥ ውሾች አሉን?" ሲል ጠየቀ።
"አዎ" አለች ዕንባዋን እየጠረገች።
"የውሾቹን ምስክርነት ትቀበያለሽን?" አላት ዳግም እየጠየቃት።
ግራ በመጋባት መንፈስ ውስጥ ተውጣ "አዎ" አለች።
"ውሰዷት ውሾቹ ከጮኹባት ውሸታም ናት፤ በዝምታ ወደ ቤቱ እንድትገባ ከፈቀዱላት የቤቱ ባለቤት ናት" አለ ዳኛው።
ምስክሮቹ እርስ በእርስ ተፋጠጡ።
"እነዚህም በውሻው ምስክርነት መሰረት ውሸታሞች ናቸውና ግረፏቸው" ሲል አዘዘ።

ውሾች ከህዝቦቿ በላይ ታማኝ የሆነባት መንደር ምንኛ ከፋች!!

ኮፒ ነው