Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-16 17:33:28 ሕይወትን እንዳለች ተቀበል

  የዚህ ህይወት ደስታ አጭር ነው ። ብዙ ጊዜ በሀዘን ይቀየራል ። ህይወት ሀላፊነት ነው ። ለውጥ አይቀሬ የሆነበትና ችግሮች የሚደራረቡበት ጉዞ ። ከችግሮች ነፃ የሆነ ባል ፣ ሚስት ፣ ልጅ ወይም ጓደኛ የለም ። አሏህ ይህንን አለም በሁለት ተቃራኒ ነገሮች እንድሞላ አድርጎ ነው የፈጠረው ። ጥሩና መጥፎ ፣ ሐቀኛና ሙሰኛ ፣ ደስተኛና ሀዘንተኛ ወዘተ ። ጥሩነት ፣ ሐቀኛነትና ደስተኛነት ለጀነት ሲሆኑ  መጥፎነት ፣ ሙሰኝነትና ሀዘንተኛነት ደግሞ ለእሳት ናቸው ።

#ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰላም « ይህች አለም በውስጧ ከያዘችው ነገር  ጋር የተረገመች  ናት ፤ አሏህን አስታዋሽ  ፣ አዋቂና እውቀት ፈላጊ ሲቀር» ብለዋል ።

      የሌለ ህይወት ከማንም ይልቅ የህይወትህን እውነታ ተቀብለህ በዛው መሰረት ለመኖር ሞክር ። ይህ ከጭንቀትና ከከንቱ ድካም ነፃ ያደርግሀል ። ህይወትን እንዳለች ተቀበላት ።  ሁሉንም ነገር እንዳመጣጡ መልስ ። በዚህ ዓለም ላይ እንከን የለሽ ነገር ወይም ፍፁም የሆነ ሁኔታ አታገኝም ። ምክንያቱም እንከን አልባነትና ፍፁምነት የዚህ አለም ባህሪያት አይደሉም ። ስለዚህ ማካካስ ያስፈልገናል ። ቀላል የሆነውን መያዝ  ፣ ከባድ የሆነውን መተው ። በተደጋጋሚ የሌሎችን ስህተትና ጉድለት  ይቅር ማለት ይኖርብናል  ።
1.3K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 23:16:26 በህይወት የመጨረሻዋ ወቅት…

አቡ አል ረይሃን አል በይሩኒ እጃቸው ከእስኪርቢቶ የማይለይ ታላቅ ፀሀፊ ነበሩ ። ለሰባ ስምንት አመታት ያክል የኖሩ ሲሆን ሙሉ ህይወታቸውን በማንበብ ፤ በመፃፍና በማስተማር ነው ያሳለፉት ።

አቡል ሀሰን ዐሊ ኢብን ዒሳ ሲናገሩ 《 አቡ አልረይሃን ታመው ልጠይቃቸው ወደ ቤታቸው ሄድኩ ። ሳያቸው በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን ተገነዘብኩ ። ከዚያ ቀን በፊት በተገናኘን ጊዜ በኢስላማዊ የውርስ ህግ ዙሪያ አንዳንድ ነገሮችን ተወያይተን ነበር ። በዚያ ሁኔታ ላይ እያሉ ያኔ እኔ የተናገርኩትን ነገር ስህተት መሆኑን እንደተረዱ ነገሩኝ ። በጣም አሳዘኑኝና { እንደዚህ ታመው ባሉበት ሁኔታ ስለ እንድህ አይነቱ ነገር መወያየት ተገቢ ነው ወይ? } ስል ጠየቅኳቸው ። እሳቸውም { ይህችን አለም እየለቀቅኩ መሆኔን አውቃለሁ ፤ ነገር ግን ይህን ጉዳይ ሳላውቅ ከመቅረት ይልቅ ማወቁ የሚሻለኝ አይመስልህም ? } ሲሉ መለሱልኝ ። ከዚያም ጉዳዩን ደገምኩላቸውና ያብራሩልኝ ጀመር ። ወይይታችንን እንደጨረስን ወጣሁ ። ትንሽ እንደተራመድኩ በአካባቢው የጩኸት ድምፅ ተሰማ ። አቡ አልረይሃን አረፉ ። የሳቸው አይነት ጥቂት ነፍሶች ብቻ ናቸው እንድህ እስከ መጨረሻ ድረስ ጠንካራ ሆነው የሚቆዩት ።》

ዑመር ረድየሏሁ አንሁ ወአርዷህ በስለት ተወግተው ሊሞቱ ደም እየፈሰሳቸው እንዳለ ሶላታቸውን ማጠናቀቃቸውን ለጓደኞቻቸው ጠይቀዋል ።

ኢብራሂም ኢብን አልጀራህ ሲናገሩ 《 አቡ ዩሱፍ ታመው ራሳቸውን በመሳትና በመንቃት መካከል እየዋለሉ ነበር ። ከዚያም አእምራቸው መለስ ሲልላቸው ስለ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጠየቁኝ ። ጥያቄውን በአድናቆት መቀበሌን ሲያዩ { ምንም ችግር የለም ፤ ይህን ጉዳይ እናጠናዋለን ፤ እውቀቱ ተወርሶ አንድ ሰው እንኳን ቢሆን ከጥፋት መጠበቅ ይቻላል በሚል ተስፋ} አሉኝ።》

ደጋግ ሙስሊሞች እንድህ ነበሩ ። በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ጣዕረ ሞት መለስ ባለላቸው ቁጥር ስለ ኢስላማዊ እውቀት ነበር የሚያወሩት ። እንደ አስተማሪ ወይም እንደ ተማሪ ። እውቀት ለእነሱ ወሳኝ ነገር ነበር ። በህይወታቸው የመጨረሻ ጊዜያት ቤተሰባቸውን ወይም ሀብታቸውን ሳይሆን የህይወታቸው ብርቱ ልፋት የነበረውን እውቀትን ብቻ ነበር የሚያስታውሱት ። አሏህ ይማራቸው ።

1.5K viewsedited  20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:54:04 ሁረል ዐይን

~ ሉዕባ ሆይ!

ዓብደላህ ኢብኑ መስኡድ (ረ ዐ) እንዲህ ብለዋል…

በጀነት ውስጥ ሉዕባ የምትባል የጀነት ሴቶች ሁሉ በቁንጅናዋ የሚገረሙባት እንስት አለች ፤ ትካሻዋን በእጃቸው መታ እያደረጉ እንዲህ ይሏታል «ሉዕባ ሆይ! ምነኛ እድለኛ ነሽ ፈላጊዎችሽ ቢያዩሽ ኖሮ አንቺን ለማግኘት ምነኛ በለፉ ነበር። በዓይኖቿ መሀልም ‹‹እኔ የሚፈልግ ጌታዮን በኢባዳ ያስደስት ›› የሚል ጥቅስ ተፅፏል።

እርቃን የሆኑ ሴቶችን ከመመልክት ዓይንህን የሰበርክ ከጭቃ የተሰራችውን እንስት ችላ ብለህ ከሉል የተሰራችውን ያስበለጥክ ፤ አብሽር የሉእባ ዓይነት ውድ እንስትን ታገኛለህ…።

የሑረል ዐይኗን ጉንጮች
እንደመስታወት ይጠቅማል ፤
ልብሶ አያረጅም
ወጣትነቷ አይለወጥም ፤
ጡባ ሊዘውጂሃ…›››››


1.4K viewsedited  17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 18:25:57 እንደኔ በቢክ እስክርቢቶ፣ በማምኮ ደብተር፣ ስፖርት በካራውን ደብተር፣ ሒሳብ በስኬር ደብተር፣ ፌስታል እንደ ቦርሳ፣ ትምህርት በሬዲዮ እያዳመጣችሁ፣ ድንጋይ እንደ ወንበር፣ እስክርቢቶ እንዳይሰረቅባችሁ ወረቀት ላይ ስማችሁ ጽፋችሁ ከቀፎው ያስገባችሁ፣ ቁርስ ሻሂ በዳቦ በልታችሁ፣ የምሳ እቃ የሚባል ሳታውቁ...ወዘተ የተማራችሁ እንደምን ናችሁ?
1.4K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 09:55:15 እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ።
በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦

«እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ  እንዳይመስላትና  ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ።

እኔም ማስገባቱ  ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ

«ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው»

ጀነት በእናት እግር ስር ናት < ነቢዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ >
ጁምዐ
ሱረቱል ከህፍ
ሰሉ አለ ነቢይ
ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
2.0K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 02:06:43
እንዲህም ይወደዳል
.
.
ቃለ መጠይቅ ስለነበረብኝ ወደ ቢቢሲ የዜና ጣቢያ በኮንትራት ታክሲ ሄድኩኝ።የጣቢያው ደጃፍ ስደርስም ለሹፌሩ ለአርባ ደቂቃ ያክል እንዲጠብቀኝ ጠየቅኩት።
ሹፌሩም ቤት ሄዶ የዊንስተን ቸርችልን ንግግር መስማት እንዳለበት በመግለፅ፤መጠበቅ አለመቻሉን በይቅርታ ገለፀልኝ።
ንግግሬን ለመስማት የነበረው የጋለ ስሜት እጅጉን አስደስተኝ።ማንነቴን ሳልገልፅለትም ከኪሴ አስር ፓውንድ በማውጣት ሰጠሁት።
የሰጠሁትን ገንዘብ ባየም ጊዜ ደስታና ግርምት ተቀላቅሎት እንዲህ አለኝ:-
"አንድ ሰዓትም ቢሆን እጠብቆታለሁ ጌታዬ! ቸርችል ከፈለገ ገደል ይግባ።"
1.8K views23:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 19:41:52
ዱንያ ላይ እያላችሁ የቀብርን ህይወት በከፊልም ቢሆን ከሚያስታውሱ ቦታዎች መካከል MRI የሚባለው ክፍል ነው። የዲስክ ህመምተኞች የጀርባ አጥንታቸውን ለመታየት ምንም ሳይንቀሳቀሱ ከ20ደቂቃ በላይ እዚህች ጠባብ ክፍል ውስጥ በጀርባቸው ይተኛሉ። እዚ ቦታ ስትገቡ አሏህ በናንተ ላይ የዋለውን የዓፍያ ፀጋ ታመሰግናላችሁ .. የደረሰበት ያውቀዋል ..
አሏህን አመስግኑ
2.1K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:16:32
~

ዕድሜህ በሄደ ቁጥር በዚህች ዓለም ሕይወት ላይ ያዘንክባቸው ነገሮች ሁሉ ያን ያህል ዋጋ ሊሠጣቸው እንደማይገባ ትረዳለህ። ዱንያ እንዲሁ ናት። ታሸንፋለህ ትሸነፋለህ፣ ታዝናለህ ትስቃለህ፣ ታገኛለህ ታጣለህ፣ ሙሲባ ይመጣል ይሄዳል፣ ሰው ይሄዳል ይተካል፣ ዱንያ ላይ ለዘላለሙ አብሮህ የሚዘልቅ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የለም። የነገሮች መወለድና መሞት ያለ ነዉና ብዙ አትገረም።
ቀናችሁን ከምትጀምሩባቸው ነገሮች ሁሉ ምርጦቹ ዚክር፣ ሶላትና ዱዓ ናቸው።
2.3K viewsedited  04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 03:34:33
ያለፈ ህይወቴን ስመለከት፤ፈፅሞ ያልፋሉ ብዬ ያላሰብኳቸው ብዙ ቀናትን እንዳለፍኩ አየሁ።የዘመናት ቀያያሪ የሆነው አሏህ ጥራት ይገባው።

~ አልሐምዱሊላህ
1.9K views00:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 23:43:19 እናንተ ጋር ባልሆን ምን ታደርጉ ነበር ?
ⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐ

በትንሽዬ መንደር ውስጥ ከአንዲት ላም ወተት እየጠጡ ሚኖሩ ሰዎች ናቸው አሉ ። ከዕለታት ባንዱ ቀን ላሟ ውሀ ለመጠጣት በትልቅ ጋን ውስጥ አንገቷን አስገባች ። ከዚያም መውጣት አቃታት ።

ሰዎቹ ግራ ገብቷቸው መፍትሄ ፍለጋ የመንደሩ መሪ ዘንድ ሄደው ...
" እባክህ ከጉድ አውጣን ። ላማችን እና ጋናችንን አድንልን " አሉት ።

እሱም ላሟ ያለችበትን ሁኔታ ካየ በኋላ በጣም አስቦና ተጨንቆ መፍትሄ ያለውን ሀሳብ ...
" የላሚቷን አንገት ቁረጡ " ሲል ነገራቸው ።

በተባሉት መሠረት አንገቷን ቆረጡ ። ከዚያም እርሱ ዘንድ ተመልሰው መጡና ...
" የላማችን አንገት አሁንም ከጋኑ አልወጣም !" አሉት ።

ለአፍታ አሰበና :- ጋኑን ስበሩት አላቸው ። ሰበሩት ።

ከዚያም መሪያቸው ዞር ብሎ ማልቀስ ጀመረ ። የመንደሩ ሰዎች ሊያፅናኑት ወደርሱ መጡ ።
" አይዞህ ላሚቷም ትሙት ፣ ጋኑም ይሰበር አንተ ብቻ ደህና ሁንልን !" ሲሉት ...

እርሱም ወደነርሱ እየተመለከተ ....
" እኔኮ በላሟ ሞትም ሆነ በጋኑ መሰበር አላዘንኩም ። ግን እናንተ መሀል ባልሆን ምን ታደርጉ ነበር ? ብዬ ነው ያዘንኩት !" አላቸው ።
3.1K views20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ