እናንተ ጋር ባልሆን ምን ታደርጉ ነበር ? ⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐⓐ በትንሽዬ መንደር ውስጥ ከአንዲት ላም ወተት እየጠጡ ሚኖሩ ሰዎች ናቸው አሉ ። ከዕለታት ባንዱ ቀን ላሟ ውሀ ለመጠጣት በትልቅ ጋን ውስጥ አንገቷን አስገባች ። ከዚያም መውጣት አቃታት ። ሰዎቹ ግራ ገብቷቸው መፍትሄ ፍለጋ የመንደሩ መሪ ዘንድ ሄደው ... " እባክህ ከጉድ አውጣን ። ላማችን እና ጋናችንን አድንልን " አሉት ። እሱም ላሟ ያለችበትን ሁኔታ ካየ በኋላ በጣም አስቦና ተጨንቆ መፍትሄ ያለውን ሀሳብ ... " የላሚቷን አንገት ቁረጡ " ሲል ነገራቸው ። በተባሉት መሠረት አንገቷን ቆረጡ ። ከዚያም እርሱ ዘንድ ተመልሰው መጡና ... " የላማችን አንገት አሁንም ከጋኑ አልወጣም !" አሉት ። ለአፍታ አሰበና :- ጋኑን ስበሩት አላቸው ። ሰበሩት ። ከዚያም መሪያቸው ዞር ብሎ ማልቀስ ጀመረ ። የመንደሩ ሰዎች ሊያፅናኑት ወደርሱ መጡ ። " አይዞህ ላሚቷም ትሙት ፣ ጋኑም ይሰበር አንተ ብቻ ደህና ሁንልን !" ሲሉት ... እርሱም ወደነርሱ እየተመለከተ .... " እኔኮ በላሟ ሞትም ሆነ በጋኑ መሰበር አላዘንኩም ። ግን እናንተ መሀል ባልሆን ምን ታደርጉ ነበር ? ብዬ ነው ያዘንኩት !" አላቸው ። 3.1K views20:43