Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2022-07-09 12:10:54 ~ ኢድና የልጅነት ትውስታ..

የሆነ አስፈሪ ነፍሳት እንዳየ ሰው በሩጫ እየሮጥኩኝ ወደ እቤት ገባሁኝ እያለከለኩኝ እህቴ እህቴ አልኮት በሚያቆራርጥ ድምፅ ወይየ ከቢርየ አለችኝ ታላቅ እህቴ አባቴሳ የት ሄዶ ነው አልኮት እርሻ ሄዶል። እጭ እናቴስ የት ሄዳ ነው ገብያ ሄዳለች ውይ ሲያናድድ ለምንድን ነው ወንድሜ አለች እህቴ... እሁ ተይው በቃ በር ላይ ሆኜ ልጠብቃት እናቴን... እሺ ደስ እንዳለህ ወንድሜ።

እናቴ የበአል ገብያ ነበርና ሸምታ ስትመጣ ከሩቁ አየኋትና እየሮጥኩኝ ሄጄ ተቀበልኮት። እናቴ እናቴ አልኮት አይናይኗን እያየሁ እቤት ልጄ ምነው አለቺ ደክሞኛል እቤት ታወራኛለህ። ሸንኮራም ሙዝም ብርቱካንም ገዝቼልሃለሁ። ሙልሙል ዳቦ አለ ለአንተ ገዝቻለሁ ግን እህቶችህ ሳያዩ ትበላለህ አይደለም እሱን አይደለም የምልሽ እማዮ አልኮት... እና ምንድን ነው ልጄ እቤት ታወራኛለህ በቃ እረ አስቸኮይ ነው እማ።

ልክ እያወራን እበሩ ላይ ስንደርስ አባቴ እንጨት ተሸክሞ መጣ ድብልል አድርጎ ነው በትካሻው የተሸከመው አላግዘው ነገር ሆነብኝ... ልክ ሸክሙን እንዳወረደ ወደ እሱ ዞሬ አባየ አባየ አልኩት አቤት ልጄ ምን ነበር አለኝ። እይውማ እነከሌ እነከሌ ጓደኞቼ ለበዓል ልብስ ተገስቶላቸዋል። በዓሉም ቅዳሜ ነው እያሉ ነው ልንገርህ ብየ ነው አልሰማህ ከሆነ። እህህህ አለ አባቴ ልብስ ግዙልኝ የሚለውን የሽሙጥ መናገሬ መሆኑ ገብቶታል። እሺ ና በቃ ወደቤት እንግባና ይገዛል አለኝ በደስታ ፈነደቅኩኝ ለኢድ አዲሱን ልብሴ ለብሼ እማ እማ ቤት እንደምሄድ ማሰብ ጀመርኩኝ ጓደኞቼም ጋር የኔ ያምራል ያንተ ያስጠላል ለመባባል አሰብኩኝ እይውማ እይውማ አባቴ ጓደኛየ ከላይም ከታችም ሙሉ ቱታ እርሳስ ከለር ነው። የኔም ከሱ ለየት ያለ መሆን አለበት አልኩት እሺ አለኝ... ከዛም ጓደኞቼን አስቀናቸዋለሁኝ ። ከዛም አጓቴቼንም አሳያቸዋለሁኝ ሳንቲምም እቀበላለሁ....

ልጄ ልጄ እስቲ ና ለካው ልክ ካልሆነህ ሄደህ ትቀይራለህ አለቺ ምኑን አልኮት ረስቼው ሳልነግርህ ልብስ ገዝቼልሃለሁ ልክ ከአፏ ሳትጨርሰው ሄጄ ጥም ጥም አልኮባት በደስታ ሳም አደረግኮትና ልብሱን ተቀበልኮት በቃ ተሳካ ብዮ በደስታ ቅልጥ አደረኩት....

ልክ ልብሱን እንደለካሁት ልኬ ነበርና ደስ አለኝ እናቴ ጨማውንም ይሄንም ለካው አለቺኝ በድጋሜ ሄጅ ጥምጥም አልኮባት ከዛም እሶኑ ተደግፌ ጫማየን ተጨማሁኝ። ልክ ነው አልያዘህም አለቺኝ አዎን አልኮት እስቲ ቁጭ ብድግ በል ልብሱንም ልየው አለቺኝ ቁጭ ብድግ አልኩና አሳየኋት... ልክ ነው ልጄ አለቺኝ። ልብሱ ሳላወልቀው በሩጫ ጥያቸው ላፍፍፍ ልጄ ልጄ ለኢድ ነው የምትለብሰው አውልቅ እያለቺኝ ላፍፍፍ ተጓደኛየ ቤት ሄጄ እኔም ተገዛልኝ እየው የኔ ያምራል አልኩትና ወደቀጣዩ ጓደኛየ ሄጄ እሱንም አሳይቼ ሌላውንም አቀለጭልጬ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ እቤት ልክ ስደርስ ሸንኮራና ሙዙ ትዝዝዝ አለኝ እናቴ ስጭኝ ፋንታየን ምንድን አለቺኝ ሸንኮራና ሙዝ ፋንታየን ስላት ሂድና መደቡ ላይ አለልህ ውሰድ አለቺኝ ልብሱን ግን አውቅልቅ አለቺኝ እሺ ብየ አወለኩኝ በቢጫ ፌስታል ታስሮ ተሰቀለ አይጥ እንዳይበላው አድርገሽ ስቀይው.... እሺ እማ አልኮት አታስብ ልጄ።...

ኢድኩም ሰኢድ ይሁንላችሁ...
በዓሉን ስናከብር ወላጅ የሌላቸውን የቲሞችን እንዳብስ ከቻልን ልብስ እንግዛላቸው ሁለት ሶስት አራትም በጀምኣ ሆነን አንድ የቲም ልብስ እናልብስ። አቅመ ደካሞችን እንርዳ የሞተባቸውን እንዘይር። በመልካምና በዚያራ በሚወደድ ተግባር ኢድን እናሳልፈው መልእቴ ነው።

አመት አመት ይደጋገምን በድጋሜ ኢድኩም ሰኢድ ይሁንላችሁ...

Ibnu Mohammed
2.3K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:50:31 ~
“ለዚህች አለም ፍላጎት አይኑርህ፡፡ አላህ ይወድሀል፡፡ በሠዎች እጅ ባለም ነገር ላይ ፍላጎት አይኑርህ - ሠዎች ይወዱሀል።"

~ "ነጭ በጥቁር ላይ የበላይ አይደለም። የትኛውም ዘር በየትኛው ላይ የበላይ አይደለም፡፡ መበላለጥ ያለው (መመዘኛው) በተቅዋ ነው።

ሃቢቡና መሐመድ (ሠ.ዐ.ወ) ..

ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
ሰሉ ዓለል ሃቢቢ...


https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
2.3K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:18:54
.
~ ከጌታህ የለመንከው ሆኖ አንድም ጉዳይ የከበደ ሆኖ አያውቅም በራስህ ልታሳካው ያሰብከው አንድም ጉዳይ ቀላል ሆኖ አያውቅም።

~ ~
ኢብን ዐጧኢላህ
https://t.me/Golden_Speech
2.0K viewsedited  16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:37:09 ~ የመጨረሻው እስትንፋስ በጭጋጋማ

ክፍል = አስራ ስምንት


በዓለማዊ መጠቃቀሚያና በስሜት ባህር የተዘፈቁ ሰዎች አንድ እለት አላህ መጥፎ አያያዝ የያዛቸው ጊዜ ወዮላቸው፡፡ ያኔ የመጪው ዓለም መጋረጃ.... ይገላለጥና ሁሉንም ነገር በዓይነ ሥጋቸው ሲመለከቱ ምን ይውጣቸው ይሆን?

~ ይህን አንኳር ሃቅ ኃያሉ አላህ በብዙ የቁርዓን አንቀፆች የገለጸው ሲሆን ቀጣዮቹ አንቀፆችም የሚያብራሩት ይህንኑ ነው።

- ‹‹ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡» (አል-አንቢያ፡ 35)


«ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሐሪው ነው፡፡ » (አልሙልክ ፡ 2)

~ ኢማም አል-ገዛሊ እንዲህ ይላሉ..
• በዚህ ዓለም ላይ እውቀትን (ኢልምን) ለመማር የሚገኘውን ደስታ ያላጣጣመ ሰው የመጪውን ዓለም ያማረ ሕይወት ማስተንተን አይችልም፡፡ አንድ ሰው በዚህች ዓለም ላይ ሰርቶ ያላሳለፋትን መልካም ነገር በመጪው ዓለም ኣያገኛትም፡፡ ማንም ቢሆን ከዚህች ዓለም የተከለውን ፍሬ ነው በመጪው ዓለም የበሰለ ሆኖ የሚያገኘው፡፡ ሁሉም ሰው እንደ አኗኗሩ ይሞታል፡፡ እንደ አሟሟቱም ይቀሰቀሳል፡፡ በመጪው ዓለም ደስታ የምናገኘው አላህን በመፍራት በሰራነው መልካም ሥራ ልክ ነው፡፡››

ስለሆነም በእያንዳንዷ እስትንፋሳችን ራሳችንን አንድም ለታላቅ ቅጣት ወይም ማለቂያ ለሌለው ደስታና ሽልማት እያዘጋጀን ነው፡፡ ኃያሉ አላህ እንዲህ በማለት ይገስፀናል፡

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች ከሆነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞችና ኃይለኞች የሆኑ መላእክት አሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ፡፡›› (አትተሕሪም፡ 6)

ኃያሉ አላህ በተጨማሪም እንዲህ ይላል፡

««ገሃነምም በተነደደች ጊዜ ፣ ገነትም በተቀረበች ጊዜ ፤ ነፍስ ሁሉ (ሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፡፡»
(እት-ተክዊር 12-14)

فأين تذهبون
“ታዲያ ወዴት ትሄዳላችሁ?»
(አት-ተክዊር፡ 26)

ትርፍና ኪሳራ ማግኘትና ማጣት ያሉት በዚህች ዓለም ላይ ብቻ ነው፡፡ በመጪው ዓለም ግን ያለው ምርመራ ብቻ ነው፡፡ አማኝ ሰው መጨረሻው ያምር ዘንድ ነፍሱን ከአጓጉል ዝንባሌዋ ማጽዳትና በመልካም ምግባርና በሰናይ ባሕሪ እንድታሸበርቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ይህም አላህን መፍራትን (ተቅዋን) ያላብሳል፡፡

~ ~
ይቀጥላል
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
2.2K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:07:51
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

ዉድ ቤተሰቦቼ ይቺን ኸይር ስራ አብረን እና ተጋግዘን እንስራት ። አንድ ጥሩ ነገር ስንሰራ አላህ ዘንድ እጥፍ ሆኖ ቢጠብቀን እንጂ ከእኛ ቅንጣት ታክል አይቀነስብንም ።

ከፊት የሚመጣዉ በአላችንን በማስመልከት የቲሞችን እና አቅመ ደካሞችን :-
#በልብስ እና #በአስቤዛ እንገዛቸዉ እያለ ጥሪዉን ጠንካራዉ መረዳጃ ጀመዐ እና የትምህርት ጀመዐ የሆነዉ የኢማም አህመድ ጀመዐ ጥሪዉን አቅርቦልናል ።

ሆኖም እናንተም ቤተሰቦቼ በዚህ ኸይር ስራ ላይ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪዉን ላደርሳችሁ ወደድኩኝ ።

አሁን ላይ ቢያንስ ከ 70 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ልብስ ያስፈልጋቸዋል ።
#ለህፃን
#ለአዋቂ ለሁሉም የሚሆን

አላችሁበት ድረስ መጥተን መቀበል እንችላለን እናንተ ብቻ ንያችሁን አስቀምጡልን ብለዉናል ።

የባንክ አካዉንት ካስፈለገ :-
አዋሽ ባንክ 014305551059000

አድራሻ :-
#ደሴ_ሸል_ካቤ_ህንፃ_ሁለተኛ_ፎቅ

ያላችሁበት ድረስ መጥተን ንያዎትን መቀበል እንችላለን ።
+251906847685
@anwu6
1.7K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:36:11 ~ ምዕራፍ ሦስት
ክፍል = አስራ ሰባት
~ የመጨረሻው እስትንፋስ በጭጋግ
ያልተጋረደ መስታዎት


የሰው ፍጻሜ ልክ በጭጋግ እንዳልተጋረደ ወይም እንዳልወየበ መስታወት መልካም እድልንም (ሰዓዳ) ሆነ መጥፎ እድልን ሸቃዋ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ክስተት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው የመጨረሻው ውጤቱ የሚወሰነው ሰውየው ባሳለፈው የሕይወት ዘይቤ ላይ ነውና፡፡ ሰው የዘራውን እንጂ ሌላን ሊያጭድ ከቶ አይቻለውም፡፡


~ በቁርዓን እንደተገለጸው ፈርዖን እድሜውን የፈጀው አላህን በማመጹ ነበር፡፡ እናም የሕይወት መስመሩ ሙሉ በመሉ ስህተት እንደነበር የተገነዘበው በቀይ ባህር ውስጥ የመጨረሻውን እስትንፋሱን ሲያወጣ ነበር፡፡ ያሳለፋቸው በአመፅና በእኩይ ድርጊት የተሞሉ የግዛት ዘመናቱ የሃዘኑና የሰቆቃው ምንጭ ሊሆኑት ካልሆነ ምን ሊበጁት!

~ እናም ሁሉም ነገር ከቁጥጥሩ ውጭ ነበር፡፡ መቸውም ሰው ነውና መፀፀት ስለማይቀር በመጨረሻ ላይ የማይጠቅም ፀፀቱን እንዲህ በማለት ገለፀ።.

{ ፡፡ «የእስራኤልም ልጆች ባህሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- ‹‹አመንኩ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ካመነበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ አለ፡፡››
(ዩኑስ ፡ 90)

~ ሆኖም ግን ይህ የፈርዖን አባባል ከንቱና ጥበብ የጎደለው ነበር፡፡ ሳያዩ (በገይብ) የሚያምኑ ብፁአን ናቸው፡፡የሚል አባባል አለ፡፡ ፈርዖን ግን ብዙ ተግሳጽ ተሰጥቶት፣ ብዙ ተለምኖና ተመክሮ አሻፈረኝ በማለት የኖረ ሰው ነው፡፡

~ በመጨረሻ ላይ የቀይ ባህር ውሃ በአፍና በአፍንጫው ሲገባበት ነበር በቁርጥ መያዙን የተገነዘበው፡፡ እናም ከላይ በቀረበው መልክ የሞት ሞቱን ዘላበደ፡፡ ሆኖም ግን ኃያሉ አላህ እንደሚከተለው በማለት ነበር አሁን መወራጨቱ እንደማያዋጣው የገነጸለት።

‹‹ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ፣ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን? (ተባለ)፡፡ ዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባህሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)፡፡ ...”
(ዩኑስ ፡ 91-92)

~ ስለሆነም በስሜታዊ ዝንባሌ ዥዋዥዌ ሲጫወቱ እድሜን ከጨረሱ በኋላ የሕይወት ጀንበር አቆልቁላ ልትጠልቅ ስትል አማኝ ነኝ ብሎ መወራጨት ዋጋ የሌለው ነገር ነው፡፡ በዓለማዊ መጠቃቀሚያና በስሜት ባህር የተዘፈቁ ሰዎች አንድ እለት አላህ መጥፎ አያያዝ የያዛቸው ጊዜ ወዮላቸው፡፡ ያኔ የመጪው ዓለም መጋረጃ....

~ ~
ይቀጥላል በአላህ ፍቃድ
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
1.9K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:33:29 ~ ነቢዩላህ ኢብራሒም እና
ልጃቸው እስማኢል....

"እንደዚሁም ኢብራሒምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መስኮት አሳየነው።" (አል አንዓም፡75)

ከላይ የተወሳውን የቁርአን አንቀጽ አስመልክቶ በተላለፈ ዘገባ ኢብራሒም (ዐ ሰ) በእያንዳንዷ ሌሊት ወደ ሰማይ ይወጡ ነበር። ወደ ሰማይ ዘልቀው በወጡባት አንድ ሌሊት ኃጢያት የሚሰራው ሰው ተመለከቱ እና እንዲህ አሉ፦

"ጌታዬ ሆይ! ይህ ሰው ከረዘቅከው ይበላል። በሰጠኸው እግሮች ይራመዳል። ይህ ሆኖ ሳለ ትዕዛዝህን ግን አይፈፅምም፣ አጥፋው!"

ያን ሰው አላህ ሱ ወ አጠፋው። ኢብራሒም (ዐ ሰ) ሌላ ወንጀል ፈፃሚ ሲያዩ አሁንም ዱዓ አደረጉበት። ከአላህ ጥሪ መጣላቸው።

" ኢብራሒም ሆይ! ባሮቼ እንዲጠፉ ከምታደርገው ዱዓ ታቀብ!" በሂደት እንዲስተካከሉ ቀስ አድርገህ ያዛቸው! እኔ በየዕለቱ ወንጀል ሲፈፅሙ እመለከታለሁ። ነገር ግን አላጠፋቸውም!"

ኢብራሒም (ዐ ሰ) ወደ መሬት ሲመለሱ በቁርአን የተወሳችውን ህልም ያያሉ። ልጃቸው በሙሉ ፍቃደኝነት "አባቴ! የታዘዝከውን ፈፅም" ሲላቸው የአላህ ወዳጅ ልጃቸውን ለማረድ ተዘጋጁ። ቢላዋውን በእጃቸው ይዘው ወደ አላህ እንዲህ በማለት ተጣሩ፦

"አምላኬ ሆይ! ይህ ብቸኛ ልጄ ነው። የዓይኔ ማረፊያ፣ የልቤ ፍቅር ነው።"

አላህ (ሱ ወ) እንዲህ ሲላቸው ሰሙ፦

"ባሪያዬን እንዳጠፋ የተማፀንክባትን ሌሊት ታስታውሳለህ? አንተ ለልጅህ እንደምታዝነው፣ እኔም ለባሪያዬ እጅግ በጣም አዛኝ፣ እጅግ በጣም ሩኅሩኅ መሆኔን አታውቅምን? አንተ ባሪያዬን እንዳጠፋ ተማፀንከኝ። (ስለዚህ) አሁን ልጅህን እንድትሰዋ እፈልጋለሁ!" ሱብሀነሏህ ውድ አንባቢያን አላህ (ሱ ወ) ልክ ልጃችን አንዳች ነገር ሲሆንብን እንደምንጨነቀው እንደምናዝነው ሁሉ አላህ (ሱ ወ) ደግሞ ለባሪያዎቹ የበለጥ ምን ያክል ሩህሩህ እንደሆነ ልናውቅ ይገባል።

ኢስማዒል (ዐ ሰ) የመታረጃ ጊዜያቸው ሲቃረብ አባታቸውን እንዲህ በማለት መከሩ፦_

1 = እጆቼን እና እግሮቼን አጥብቀህ እሰራቸው።ስቃይ ሲበዛብኝ እንዳላስቸግርህ እና የጌታዬን መብት እንዳላጓድል (ይረዳኛል)።_

2 = ደሜ እንዳይረጭብህ ልብሶችህን በደንብ ሰብስብ።_

3 = ቢላዋውን በደንብ ሳለው። ነፍሴ በቶሎ እንድትወጣ፣ አንተም ቶሎ እንድትገላገል።_

4 = ቢላዋውን ይዘህ ወደ ፌቴ አትመልከት፣ የአባትነት አንጀት የታዘዝከውን ከመፈፀም እንዳያዘገይህ።_

5 = ልብሴን ይዘህ ወደ እናቴ ሒድ! ለመፅናናት ይረዳት ይሆናል! "ልጅሽ ሸፊዕ ሆኖ ወደ አላህ ሔዷል" በላት።"


ኢብራሒም (ዐ ሰ) እነዚህን ቃላት ከልጃቸው አንደበት ሲሰሙ ዓይኖቻቸው በእንባ ተሞሉ። አብዝተው አለቀሱ። እንዲህም አሉ፦

"የአላህን ትዕዛዝ እንድፈፅም ምን ያክል አገዝከኝ!" ቀጥለው እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንስተው ዱዓ አደረጉ፦

"ጌታዬ! ባለሁበት ሁኔታ ትዕግስትን አላብሰኝ! እንግዲህ ምንም አልቀረኝም። አርጅቻለሁና እዘንልኝ!"

ኢስማዒልም (ዐ ሰ) አሉ፦ "ጌታዬ! ትዕግስትን እና ፅናትን አላብሰኝ!። አባቴ ሆይ! የጀነት በሮች ተከፍተዋል።"

መላኢካዎች በነገሩ ግራ ተጋብተውና ተደናግሯቸው ሱጁድ በመውረድ አላህን ይማፀናሉ፦ "ጌታችን ሆይ! ነቢይህ ያንተን ፍቃድ ሊሞላ ለመሰዋዕት ተጋድሟል፣…እዘንላቸው።" ይላሉ።

ኢስማዒል ቀጠሉና ለአባታቸው ፍፁም ታዛዥነታቸውን ለመግለፅ፣ ፅናታቸውን ለማሳየት እንዲህ አሉ፦

"አባቴ! ከፍቅር ማሳያዎች አንዱ አለመዘግየት ነው! በላ የታዘዝከውን ቶሎ ፈፅም!"

ኢብራሒም (ዐ ሰ) ኢስማዒልን (ዐ ሰ) አጋድመው "ውድ ልጄ! እንግዲህ የውመል ቂያማ ላይ እንገናኝ! በትንሳኤው ቀን ዳግም አይሃለሁ!" አሉትና ቢላዋውን አጥብቀው ይዘው ወደ ኢስማዒል (ዐ ሰ) አንገት ሰነዘሩ። በዚያችው ቅፅበት አላህ (ሱ ወ) ጅብሪልን አዘዘው፦

"ፍጠን። ቢላዋውን ገልብጠው!" ጅብሪል ቢላዋው የኢስማዒልን (ዐ ሰ) አንገት ከመንካቱ ገለበጠው። ኢብራሒም (ዐ ሰ) እንደገና ቢላዋውን አጥብቀው ይዘው ለመሰንዘር ሞከሩ። ግን መቁረጥ አልቻሉም። ቢላዋው እጃቸው ላይ እንዳለ ተገለበጠ።

~ አላህ (ሱ ወ) እንዲህ አለ፦

~ "ኢብራሒም (ዐ ሰ) ራዕዩን ተቀብሏል። ከልብ ማመኑን አረጋግጧል" ቀጠለና በአላህ (ሱ ወ) ትዕዛዝ መሰረት ጅብሪል ተክቢራ እያደረገ የጀነት በግ ይዞ ከተፍ አለ።

~ «አላሁ አክበር አላሁ አክበር»

ኢብራሒም (ዐ ሰ) ተክቢራውን ሲሰሙ እንዲህ በማለት ተቀበሉት፦

~ «ላኢላሀ ኢልለሏህ ወላሁ አክበር»

~ ኢስማዒልም (ዐ ሰ) እንዲህ በማለት ተክቢራውን ሞሉት፦

~ «አላሁ አክበር ወሊላሒል ሐምድ»

በዚህ መልኩ የተክቢር አትተሽሪቅ ክፍሎች ተሟሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ ዒድ አል አድሓ (የመስዋዕቱ በዓል) በመጣ ቁጥር በዓሉ ከዋለበት ቀን ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ አራተኛው ቀን የዐስር ወቅት ድረስ ተክቢር አትተሽሪቅ ይባላል።

አባት እና ልጅ በደስታ ተሞልተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። እናታችን ሐጀር ኢስማዒልን (ዐ ሰ) እቅፏ ውስጥ አስገባችው። ወደ ደረቷ በኃይል አስጠጋችው።

~ ~
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
2.5K viewsedited  13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 14:23:24 ~ ያሰብኩት ከዳኝ፣
~ ተስፋ ያደረግኩት ከዳኝ፣
~ ሸሪኬ ከዳኝ፣
~ ወዳጄ ከዳኝ፣
~ አብሮ አደጌ ከዳኝ፣
~ ሥራዬ ከዳኝ፣
~ ሀብቴ ከዳኝ፣
~ የትዳር አጋሬ ከዳኝ።
እያላችሁ አታልቅሱ፣
ዋናው ዓፍያ ነው፣ ትልቁ ነገር ጤና ነው።
ጤና ብቻ አይክዳችሁ ወዳጆቼ ።
የሄደው ይመለሳል፣ የራቀው ይመጣል፣ የጠፋው ይተካል።
" አላህን ዓፍያ ለምኑት" ብለዋል ረሱላችን ሰ.ዐ.ወ
2.2K views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 19:32:22 ~ አላህን ማስታወስ

ክፍል = አስራ ስድስት

ሞራሉ ይላሽቃል፡፡ ሕሊናውም ይደንዛል፡፡ እንደ እንስሳት ወይም ከዚያ በታች የተዋረደ ይሆናል..

«እንደ እነዚያም አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው (ሰዎች) አትሁነ፡፡ እነዚያ እነርሱ አመጸኞቹ ናቸው፡፡›› (አል-ሐሽር፡19)

~ በእርግጥም አላህን በማስታወስ ያልታነጸ መንፈስና ልብ የሰይጣን መጫወቻ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ሁልጊዜም ሲሆን አላህን ማስታወስና ሞትን መፍራት ልብን (ቀልብን) ሕያው ያደርጋል፡፡

~ ይህ እንዳይሆን የሚፈልገውና የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት ኢብሊስ (ሰይጣን) ሁልጊዜም እኛን ለማጨናነቅና አላህን የምናስታውስበት ጊዜ እንዳናገኝ ለማድረግ ይረባረባል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ጉዳዮች መንፈሳችን እንዲያዝ ያደርጋል።

~ አላህ ይህን ሁሉ ነገር ስለሚያውቅ ከሰይጣን ተንኮል እንድንጠበቅ እንዲህ የሚሉ የቁርአን አንቀፆችን አውርዷል..

7•{ w ««የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን? ተገዙኝም ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው (በማለትም)፡፡ ከእናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል የምታውቁም አልነበራችሁምን?››
(ያሲን ፡ 60-62)

~ ኃያሉ አላህ በብዙ የቁርዓን አንቀፆች በግልጽ የሚያስጠቀቅቀን ድርጊቶቻችን፣ ፍላጎቶቻችንና አጠቃላይ ፀባያችንን እንድንቆጣጠርና እንድናርም ነው። ይህን የማናደርግ ከሆነ ሕይወታችን በሀዘን ማሳረጓ የማይቀር ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡..

««እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅን ተጠንቀቁት፤ እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡ ››
(አሊኢምራን ፡ 102)

~ እዚህ ላይ አጽንኦት ሊያገኝ የሚገባው ሃሳብ ሁላችንም ቁርዓን ባበጀልን የሕይወት ዘይዮ እንመራ የሚል ነው፡፡ ይህች ዓለም አታላይ ነች፡፡ ሰው ነፋስን እንደመከተል በሚቆጠር ሩጫ ሲባዝንና ከኋላ ከኋላዋ ሲሮጥ ፈጽሞ ሊጨብጣት አልቻለም፡፡ በመጨረሻ በሞት መዳፎች ሲጨመደድና በፍርዱ ቀን ከአላህ ፊት መቅረቡን ሲገነዘብ ነው የሚባንነው፡፡

«እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ምሽቷን ወይም ረፋዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡»
(አን-ናዚአት፡ 46)

««እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና፡፡ በምታዩዋት ቀን አጥቢ ሁሉ ከአጠባችው ልጅ ትፈዛለች፡፡ የእርግዝና ባለቤት የሆነችም ሁሉ እርጉዟን ትጨነግፋለች፡፡ ሰዎቹንም (በድንጋጤ ብርታት) የሰከሩ ሆነው ታያለህ፡፡ እነርሱም (ከመጠጥ) የሰከሩ አይደሉም፡፡ ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ከመሆኑ እንጂ››
(አል-ሐጅ : 1-2)

~ ~
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
2.5K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 16:20:35 ስለ ኡድህያ መታወቅ ያለባቸው 30 ነጥቦች

በዒድ ቀን ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ ደግሞ ኡድሒያን ማረድ ነው፡፡ ስለሆነም ስለ ኡድሒያ ጥቂት እንተዋወስ፡-

1. ‹ኡድሒያ› ማለት በዒድ አል-አድሓ ቀንወደ አላህ (ሱ.ወ.) ለመቃረብና ትዕዛዙን ለመፈጸም ተብሎ የሚታረድ እንሰሳ ነው፡፡ በዱሓ ወቅት ማለትም ረፋድ ላይ ስለሚታረድ ስያሜውን ‹ዱሓ› ከሚለው አገኘ ያሉም አሉ፡፡

2. ኡድሒያ ሸሪዓዊ ድንጋጌ ያለው ጉዳይ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ‹ለጌታህ ስገድ፤ (በስሙ) ሰዋም፡፡› (አልከውሠር፡2) ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ.) እንዳሉት መስዋእት የተባለው ‹በዒድ አልአድሓ ቀን የሚፈጸም እርድ ነው፡፡›

3. በአነስ (ረ.ዐ.) ዘገባ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሁለት ቀንዳም የሆኑ በጎችን በማረድ አንዱ ለርሳቸውና ለቤተሰባቸው ሌላኛው ለተከታዮቻቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

4. ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ.) እንዳሉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) በመዲና ሳሉ አሥር አመት ሙሉ ኡድሒያ አርደዋል፡፡

5. ብያኔው ላይ የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን አብዛኞቹ ዑለሞች ‹ሱና ሙአከዳ/ አጽንኦትና ክብደት የተሰጠው ሱና› ያሉ ሲሆን እነ ኢማም አቡ ሐኒፋና ኢብኑ ተይሚያ ደግሞ ‹ግዴታ ነው› ብለዋል፡፡

6. ኡድሒያ ለማረድ ኒያ ያለው ሰው አሥሩ የዚልሒጃ ቀናት ከገቡ በኋላ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን መቆረጥ የለበትም፡፡

7. ኡድሒያ ለማረድ ያሰበ ሰው እንሰሳውን ሲገዛም ሆነ ሲያርድ ኒያውን ማስገኘት ይኖርበታል፡፡

8. ኡድሒያ የሚታረደው ከዒድ ከሶላት በኋላ ነው፡፡ ከዒድ በኋላ ባሉት ሶስቱ ቀናት ውስጥም ማረድ ይቻላል፡፡ በላጩ ግን መልካምን ነገር ቶሎ ለመፈፀም መሽቀዳደም ነው፡፡

9. የዒድ አልድሓ ቀን ሳይበሉ መውጣት እንዲሁም ከሶላት ከተመለሱ በኋላ ካረዱት እንሰሳ መመገብ ሱና ነው፡፡

10. ለኡድሒያ የሚታረደው እንሰሳ ምርጥና ውድ፣ ሲያዩት የሚያምርና የሰባ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ሶሓቦች ለኡድሒያ የሚያርዱትን እንሰሳት በመቀለብ እስከ መታረጃው ቀን ድረስ ያሰቡ ነበር፡፡

11. ኡድሒያ ከእስልምና ምልክቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ የእስልምናን ምልክቶችን መገለጫዎች ማክበር አላህን የመፍራት ምልክት ነው፡፡

12. ለኡድሒያ የታረደውን እንሰሳ ሶስት ቦታ በመክፈል አንድ ሶስተኛውን መብላት፣ አንደ ሶስተኛውን ሀዲያ/ስጦታ መላክ እንዲሁም አንድ ሶስተኛውን ለድሆች መመጽወት ያስፈልጋል፡፡

13. ለኡድሒያ የሚታረዱ እንሰሳት በዋናነት በግ፣ ፍየል፣ ከብት እና ግመል ናቸው፡፡ ዶሮ ሆነ ሌሎች የሚበሊ እንሰሶች ለኡድሒያ አይበቁም፡፡

14. ለኡድሒያ የሚታረደው እንሰሳ በግ ከሆነ ስድስት ወር፣ ፍየል አንድ አመት፣ ከብት ሁለት አመት፣ ግመል አምስት አመት የሞላው መሆን ይኖርበታል፡፡

15. ግመልና ከብትን ለሰባት ሆኖ ማረድ ይቻላል፡፡

16. ለኡድሒያ የሚታረድ እንሰሳ ምንም ዓይነት እንከንን ነውር የሌለበት መሆን ይኖርበታል፡፡ ነውርና እንከን ሲባል ዐይኑ የጠፋ፣ የታመመ፣ የሚያነክስ፣ የከሳ፣ ያረጀ፣ ላቱ፣ ጆሮው ወይም ከአካል ከፍሉ አንዳች ነገር የተቆረጠና የመሳሰለውን ነው፡፡

17. ለኡድሒያ የሚታረድ እንሰሳ ቆዳው መሸጥ የለበትም፡፡ በአግልግሎት ክፍያ መልክም ለአራጅ መስጠት አይቻልም፡፡

18. የኡድሒያ ባለቤት ኡድሒያውን በራሱ እጅ ቢያርድ፣ በራሱ እጅም ቢያከፋፍል መልካም ነው፡፡ የአምልኮ ተግባር ነውና፡፡

19. በሚያርድበት ጊዜም ‹ቢስሚላህ አላሁ አክበር› በማለት ቀጥሎም ‹አልላሁም ሃዛ ዐንኒ ወዐን አህሊ በይቲ፡፡ አልላሁምመ ተቀብበል ሚንኒ/አላህ ሆይ! ይህ ከኔ እና ከቤተሰቤ ነው፡፡ አላህ ሆይ ተቀበለኝ› ማለት ይኖርበታል፡፡

20. ቤተሰቡ የበዛ ቢሆንም እንኳን ለሙሉ ቤተሰብ አንድ ኡድሒያ በቂ ነው፡፡

21. የሚታረደው እንሰሳ የራስ ንብረት መሆን አለበት፡፡ ያለባለቤቱ ፈቃድ፣ ሰርቆም ሆነ ነጥቆ ማረድ ተቀባይነት የለውም፡፡ በንጹህ እንጂ በውሸት ገንዘብ ወደ አላህ (ሱ.ወ.) አይቀረብምና፡፡

22. ለኡድሒያ ታስቦ አንድ ሰው አንድን በግ ወይም ፍየል መጋራት አይችልም፡፡ ከሰባት በላይ በሆነ ሰውም አንድን ከብት ማረድ አይበቃም፡፡

23. ኡድሒያን ከሰላት በፊት ማረድ አይቻልም፡፡ ከጊዜው በፊትም ሆነ ከጊዜው በኋላ ማረድ እንደማንኛውም ሥጋ እንጂ ኡድሒያ አትሆንም፡፡

24. አራጅ የእርድ ሥነሥርኣትን መጠበቅ አለበት፡፡ የሚታረደውን እንሰሳ ወደ ቂብላ ማዞር፣ የአላህን ሥም ማውሳት፣ አንደኛውን እንሰሳ ሌላኛው ፊት አለማረድ፣ የሚያርዱበትን ቢላዋ በሚገባ መሳልና ቶሎ ማሰረፍ ጥቂቶች ናቸው፡፡

25. ኡድሒያ ማረድ ለማይችል ሰው እሱን ነግሮና አስፈቅዶ ለሱ አስቦ ማረድ ይቻላል፡፡

26. ድሃ ሰው የተላከለትን የኡድሒያ ሥጋ መሸጥም ሆነ ሌላ የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል፡፡

27. ኡድሒያን ሰው ወክሎ ማሳረድ ይቻላል፡፡ የሚታረደለት ሰውም ጸጉሩን ጥፍሩን ከመንካት መቆጠብ ይኖርበታል፡፡

28. ዑለማኦች ኡድሒያን ማረድ ያልቻሉ ሰዎች ሀሳብ ሊገባቸው እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱም ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ሁለት በጎችን በሚያርዱበት ወቅት አንዱን አቅም ለሌላቸው ህዝቦቻቸው አርደዋልና፡፡

29. ኡድሒያ የአላህን ትዕዛዝ ለመፈጸም ወደሱ መቃረቢያ ተግባር ከመሆኑም በላይ የመተዛዘንና የመተሳሰብ ተምሳሌት ነው፡፡ በዕለቱ ድሆች ጠግበው ይውላሉ፡፡ ሥጋ አያምራቸውም፡፡

30. የኡድሒያ ቀን አላህን ማውሳት የሚጎላበት ነው፡፡ ፀጋውንም ደጋግመን እናመሰግንበታለን፡፡ ቅኑንና ተወዳጁን ነቢይ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ.) እና ልጃቸውን ኢስማዒልን እናስታውስበታለን፡፡

ወላሁ አዕለም፡፡

ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ

ይህን መልዕክት ሼር በማድረግም ላልደረሳቸው እናዳርስ

~ ~
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
2.7K viewsedited  13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ