Get Mystery Box with random crypto!

~ አላህን ማስታወስ ክፍል = አስራ ስድስት ሞራሉ ይላሽቃል፡፡ ሕሊናውም ይደንዛል፡፡ እንደ እን | ወርቃማ ንግግሮች

~ አላህን ማስታወስ

ክፍል = አስራ ስድስት

ሞራሉ ይላሽቃል፡፡ ሕሊናውም ይደንዛል፡፡ እንደ እንስሳት ወይም ከዚያ በታች የተዋረደ ይሆናል..

«እንደ እነዚያም አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው (ሰዎች) አትሁነ፡፡ እነዚያ እነርሱ አመጸኞቹ ናቸው፡፡›› (አል-ሐሽር፡19)

~ በእርግጥም አላህን በማስታወስ ያልታነጸ መንፈስና ልብ የሰይጣን መጫወቻ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ሁልጊዜም ሲሆን አላህን ማስታወስና ሞትን መፍራት ልብን (ቀልብን) ሕያው ያደርጋል፡፡

~ ይህ እንዳይሆን የሚፈልገውና የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት ኢብሊስ (ሰይጣን) ሁልጊዜም እኛን ለማጨናነቅና አላህን የምናስታውስበት ጊዜ እንዳናገኝ ለማድረግ ይረባረባል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ጉዳዮች መንፈሳችን እንዲያዝ ያደርጋል።

~ አላህ ይህን ሁሉ ነገር ስለሚያውቅ ከሰይጣን ተንኮል እንድንጠበቅ እንዲህ የሚሉ የቁርአን አንቀፆችን አውርዷል..

7•{ w ««የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን? ተገዙኝም ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው (በማለትም)፡፡ ከእናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል የምታውቁም አልነበራችሁምን?››
(ያሲን ፡ 60-62)

~ ኃያሉ አላህ በብዙ የቁርዓን አንቀፆች በግልጽ የሚያስጠቀቅቀን ድርጊቶቻችን፣ ፍላጎቶቻችንና አጠቃላይ ፀባያችንን እንድንቆጣጠርና እንድናርም ነው። ይህን የማናደርግ ከሆነ ሕይወታችን በሀዘን ማሳረጓ የማይቀር ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡..

««እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅን ተጠንቀቁት፤ እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡ ››
(አሊኢምራን ፡ 102)

~ እዚህ ላይ አጽንኦት ሊያገኝ የሚገባው ሃሳብ ሁላችንም ቁርዓን ባበጀልን የሕይወት ዘይዮ እንመራ የሚል ነው፡፡ ይህች ዓለም አታላይ ነች፡፡ ሰው ነፋስን እንደመከተል በሚቆጠር ሩጫ ሲባዝንና ከኋላ ከኋላዋ ሲሮጥ ፈጽሞ ሊጨብጣት አልቻለም፡፡ በመጨረሻ በሞት መዳፎች ሲጨመደድና በፍርዱ ቀን ከአላህ ፊት መቅረቡን ሲገነዘብ ነው የሚባንነው፡፡

«እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ምሽቷን ወይም ረፋዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡»
(አን-ናዚአት፡ 46)

««እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና፡፡ በምታዩዋት ቀን አጥቢ ሁሉ ከአጠባችው ልጅ ትፈዛለች፡፡ የእርግዝና ባለቤት የሆነችም ሁሉ እርጉዟን ትጨነግፋለች፡፡ ሰዎቹንም (በድንጋጤ ብርታት) የሰከሩ ሆነው ታያለህ፡፡ እነርሱም (ከመጠጥ) የሰከሩ አይደሉም፡፡ ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ከመሆኑ እንጂ››
(አል-ሐጅ : 1-2)

~ ~
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech