Get Mystery Box with random crypto!

ወርቃማ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ golden_speech — ወርቃማ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @golden_speech
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.15K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።
አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot
https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2022-09-17 07:53:22 የአላህ ቸርነት
<~~~~>

ፀጋህን አብዝተህ ቸርከኝ፣
እኔ ግን አመስጋኝ መሆን ከበደኝ፣
ፈተንከኝ ታጋሽ መሆን አቃተኝ፣

ባለማመስገኔ የሠጠኸኝን ፀጋ አልወሰድክብኝም፣
ባለመታገሴም ችግሬንም አላረዘምክብኝም፣

ጌታዬ ሆይ! ቸርነት የሚታሰበው ቸር ከሆነው አምላክ ነው፣
ንፉግነትና ስስትማ የሰው ባህሪ ነው፡፡
ቸርነትህ ምንኛ በዛ!!!

https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
1.8K viewsedited  04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 14:02:37 ተስፋ አትቁረጥ


አሏህ በጭንቅ ላይ ያለን ካፊር ዱዓ ይቀበላል ። ታዲያ ከእሱ ጋር አጋርን ያላበጀ ሙስሊም ምን ያህል የበለጠ ነገር ነው የሚጠብቀው ? በህንድ ከቡድሀ ቀጥሎ ሁለተኛው ዝነኛ ሰው ማህተመ ጋንድ በጠንካራ ፀሎት ላይ የሙጥኝ ባይል ኖሮ ስህተት ውስጥ ይወድቅ ነበር ። ይህንን ልል የቻልኩት ራሱ ከተናገረው ንግግር በመነሳት ነው ። 《ፀሎት ባላደርግ ኖሮ ከብዙ ጊዜያት በፊት አብድ ነበር》 ሲል ተናግሯል ። ይህ የፀሎት ውጤት ነው ።

ﻓَﺈِﺫَا ﺭَﻛِﺒُﻮا ﻓِﻲ اﻟْﻔُﻠْﻚِ ﺩَﻋَﻮُا اﻟﻠَّﻪَ ﻣُﺨْﻠِﺼِﻴﻦَ ﻟَﻪُ اﻟﺪِّﻳﻦَ ﻓَﻠَﻤَّﺎ ﻧَﺠَّﺎﻫُﻢْ ﺇِﻟَﻰ اﻟْﺒَﺮِّ ﺇِﺫَا ﻫُﻢْ ﻳُﺸْﺮِﻛُﻮﻥَ

በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡
(አል_ዐንከቡት )

ﺃَﻣَّﻦ ﻳُﺠِﻴﺐُ اﻟْﻤُﻀْﻄَﺮَّ ﺇِﺫَا ﺩَﻋَﺎﻩُ ﻭَﻳَﻜْﺸِﻒُ اﻟﺴُّﻮءَ ﻭَﻳَﺠْﻌَﻠُﻜُﻢْ ﺧُﻠَﻔَﺎءَ اﻷَْﺭْﺽِ ۗ ﺃَﺇِﻟَٰﻪٌ ﻣَّﻊَ اﻟﻠَّﻪِ ۚ ﻗَﻠِﻴﻼً ﻣَّﺎ ﺗَﺬَﻛَّﺮُﻭﻥَ

ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡
(አን_ነሕል )

ﻫُﻮَ اﻟَّﺬِﻱ ﻳُﺴَﻴِّﺮُﻛُﻢْ ﻓِﻲ اﻟْﺒَﺮِّ ﻭَاﻟْﺒَﺤْﺮِ ۖ ﺣَﺘَّﻰٰ ﺇِﺫَا ﻛُﻨﺘُﻢْ ﻓِﻲ اﻟْﻔُﻠْﻚِ ﻭَﺟَﺮَﻳْﻦَ ﺑِﻬِﻢ ﺑِﺮِﻳﺢٍ ﻃَﻴِّﺒَﺔٍ ﻭَﻓَﺮِﺣُﻮا ﺑِﻬَﺎ ﺟَﺎءَﺗْﻬَﺎ ﺭِﻳﺢٌ ﻋَﺎﺻِﻒٌ ﻭَﺟَﺎءَﻫُﻢُ اﻟْﻤَﻮْﺝُ ﻣِﻦ ﻛُﻞِّ ﻣَﻜَﺎﻥٍ ﻭَﻇَﻨُّﻮا ﺃَﻧَّﻬُﻢْ ﺃُﺣِﻴﻂَ ﺑِﻬِﻢْ ۙ ﺩَﻋَﻮُا اﻟﻠَّﻪَ ﻣُﺨْﻠِﺼِﻴﻦَ ﻟَﻪُ اﻟﺪِّﻳﻦَ ﻟَﺌِﻦْ ﺃَﻧﺠَﻴْﺘَﻨَﺎ ﻣِﻦْ ﻫَٰﺬِﻩِ ﻟَﻨَﻜُﻮﻧَﻦَّ ﻣِﻦَ اﻟﺸَّﺎﻛِﺮِﻳﻦَ

እርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው፡፡ በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች፡፡ ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል፡፡ እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል፡፡
(ዩኑስ )

የሙስሊም ባለታሪኮች ፣ ምሁራንና ፀሀፊወች የህይወትን ታሪክ በደንብ ብናስስ አንዳቸውም ለጭንቀት ፣ ለመረበሽና ለአዕምሮ ህመም ተጋልጠው አናገኝም ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሰላማዊ ፣ የተረጋጋና ከሁሉም አይነት ማስመሰል ነፃ የሆነ አስተሳሰብ ህይወት ስለኖሩ ነው ።

ﻭَاﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮا ﻭَﻋَﻤِﻠُﻮا اﻟﺼَّﺎﻟِﺤَﺎﺕِ ﻭَﺁﻣَﻨُﻮا ﺑِﻤَﺎ ﻧُﺰِّﻝَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻣُﺤَﻤَّﺪٍ ﻭَﻫُﻮَ اﻟْﺤَﻖُّ ﻣِﻦ ﺭَّﺑِّﻬِﻢْ ۙ ﻛَﻔَّﺮَ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﺳَﻴِّﺌَﺎﺗِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﺻْﻠَﺢَ ﺑَﺎﻟَﻬُﻢْ

እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡
(ሙሀመድ )

【ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰላም 《አሏህ ሆይ ! ዛሬን ጥሩ እንድታደርግልኝ እጠይቅሀለሁ ፤ በበረካ ፣ በስኬት ፣ በብርሀንና በመመሪያ》 ብለዋል ።】

ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮا ﺧُﺬُﻭا ﺣِﺬْﺭَﻛُﻢْ ﻓَﺎﻧﻔِﺮُﻭا ﺛُﺒَﺎﺕٍ ﺃَﻭِ اﻧﻔِﺮُﻭا ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄያችሁን ያዙ፡፡ ክፍልፍልም Ñድ ሆናችሁ (ለዘመቻ) ውጡ፡፡ ወይም ተሰብስባችሁ ውጡ፡፡
(አል_ኒሳዕ )

ﻭَﻟْﻴَﺘَﻠَﻄَّﻒْ ﻭَﻻَ ﻳُﺸْﻌِﺮَﻥَّ ﺑِﻜُﻢْ ﺃَﺣَﺪًا

ቀስም ይበል፡፡ በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ» ፡፡
(አል_ከህፍ )

ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﻗَﻮْﻟَﻬُﻢْ ﺇِﻻَّ ﺃَﻥ ﻗَﺎﻟُﻮا ﺭَﺑَّﻨَﺎ اﻏْﻔِﺮْ ﻟَﻨَﺎ ﺫُﻧُﻮﺑَﻨَﺎ ﻭَﺇِﺳْﺮَاﻓَﻨَﺎ ﻓِﻲ ﺃَﻣْﺮِﻧَﺎ ﻭَﺛَﺒِّﺖْ ﺃَﻗْﺪَاﻣَﻨَﺎ ﻭَاﻧﺼُﺮْﻧَﺎ ﻋَﻠَﻰ اﻟْﻘَﻮْﻡِ اﻟْﻜَﺎﻓِﺮِﻳﻦَ

ንግግራቸውም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ለእኛ ማር፣ ይዞታችንንም አደላድል፣ በከሓዲዎችም ሕዝቦች ላይ እርዳን» ማለታቸው እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡
(አል_ዒምራን )
2.0K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 14:02:37 አሁን የምነግራችሁ ሦስት ነገሮች ምየ አረጋግጥላችኃለሁ በልባችሁ ያዟቸው ፡፡

∼የአንድ ሰው ገንዘብ በሶደቃምክንያት አትጎድልም ፡፡

∼አንድ ሰው በደል ደርሶበትአይታገስም ÷ አላህ ክብርን የጨመረለት ቢሆን እንጂ፡፡

∼አንድ ሰው የልመናን በር አይከፍትም÷ አላህ የድህነትንበር የከፈተበት ቢሆን እንጂ።

∼አንድ ጠቃሚ ነገርም አክልላችኃለሁ፡፡በልባችሁ ያዙት፡፡

⇝ይህች ዓለም ለሦስት የሰው አይነቶች ናት፡፡⇜



∼አንደኛው አላህ ገንዘብም እውቀትም የለገሰው ሰው ነው፡፡ በዚህ ፀጋ ጌታውን ይፈራበታል፡፡ ዝምድናን ይቀጥልበታል። የአላህን መብት ይጠብቅበታል። ይህ ሰው ደረጃው (ከሁሉም) የላቀ ነው፡፡

∼(ሁለተኛው ደግሞ) አላህ እውቀትን የለገሰው ገንዘብን ያለገሰው ሰው ነው። ፍፁም እና ቅን የሆነ ሀሳብ አለው።ገንዘብ ቢኖረኝና እገሌ የሚሰራውን (መልካም ስራ)በሰራሁ በማለት ይመኛል። የሁለቱ ሰዎች ምንዳ እኩልነው፡፡

∼(ሦስተኛው) አላህ ገንዘብን እንጂ እውቀት ያልሰጠው ሰው ሲሆን÷ በገንዘቡ ያለ እውቀት ይዋዥቃል። በርሱ ጌታውን አይፈራበትም፡፡ ዝምድናን አይቀጥልበትም። የአላህን መብት አይጠብቅበትም፡፡ ይህ እጅግ በከፋ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡( አራተኛውና የመጨረሻው ) አላህ አውቀትም ገንዘብም ያልለገሰው ሰው ነው። ገንዘብ ቢኖረኝ እንደ እገሌ(እኩይ ሥራወችን)እሠራበት ነበር፡፡ በማለት (ክፉ ምኞት) ይመኛል፡፡

የነኝህየሁለቱ ሰዎች ኃጢያት እኩል ነው መልዕክተኛዉﷺ
1.8K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 06:28:21 ብዙ እህቶቻችን ዲን ያስተምራሉ፣ ተምሳሌት ይሆናሉ ተብለው በሚታሰቡ፣ ለትዳር ተገቢውን ክብር በማይሰጡ #ኡስታዞች በየጊዜው በደል እየተፈፀመባቸው፣ ደም እንባ እያለቀሱ ነው። መናገርም ዝም ማለትም አስቸጋሪ ሆነ። ሁለቱንም ብናደርግ ፈተና ይከተላል። ምን ይሻላል?
ለማንኛውም እህቶች ሆይ! ማንም "ኡስታዝ ነው" ስለተባለ ብቻ ዘው ብላችሁ አትግቡ። በሚታመን ሰው ላይ የባህሪን ጉዳይ አጣሩ። መልካም ባህሪ የሌለው ሰው ጋር በየትኛውም ሰበብ (ሀብት፣ ዝና፣ እውቀት) ስሙ ቢገን እንኳን አብሮ መኖር ከባድ ነው። "ኋላ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ።" ትዳርም ስኬትም በአላህ እጅ ቢሆንም ሰበብ ማድረሱን ግን እንደ ቀላል አንመልከተው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
2.0K views03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 06:19:03 ኢና አዕጠይና ከልከውሰር...

የዚህች ሱራ ታሪክ
.
ሁላችንም እንደምናውቀው ለረሱል ሰዐወ ሶስት ወንድ ልጆች ነበሯቸው።በጣም እሚዐጅበው ሁሌም ወንድ ልጅ ሲወልዱ ወድያው ይሞትባቸው ነበር።

የሆነ ቀን ረሱል ሰዐወ በመካ ከተማ ሲዘዋወሩ አንድ ሙሽሪክ ይመለከታቸውና፦‹‹አንተ አብተር (ዘሩ ማይበረክትለት)››ብሎ አፌዘባቸው።

ማለትም ዘርህን ካልተካህ ልክ ስትሞት ትረሳለህ። ምክንያቱም ባንተ የሚጠራ ልጅ ስለሌለህ እሚያስታውስህም የለም።

እሳቸው ደግሞ ስማቸውን ሚያስጠራ ልጅ አልበረክት ብሏቸው አንዱ ሲሞት ሌላው እየተከተለ እየሞተባቸው ልጅ አልባ ሁነዋል።

ረሱል ሰዐወ ይህን ስድብ ከሰውዬው ሲሰሙ ሀዘን ወረራቸው። ይህን ግዜ አላህም፦"ኢና አዕጠይና ከልከውሰር...." የምትለዋን ሱራ አወረደላቸው።

‹‹ሙሀመድ ሆይ!!! እኛ ከውሰር የተባለን ጅረት ሰጥተንሃል። ከውሰር ማለት ጀነት ውስጥ የሚገኝ ጅረት ሲሆን፤ ካንተ ሌላ ማንም አይቀምሰውም። በሚያፌዙብህ ነገር እንዳታዝን...

ሰላትህንም ስገድ እርዶችንም በኔ ስም እያረድክ ለድሆችም አከፋፍል።

ሙሀመድ ሆይ!!! ያ አንተን (ዘረ ማይበረክትለት) ብሎ የዘለፈህን ሰውዬማ እሱን ራሱ ዘር አልባ አደርገዋለሁ። የቂያማ እለትም ሆነ በዱንያ ህይወት ስለሱ ሚያወሳም እሱን ሚጠይቅም እንዳይኖርብአድርጌ እተውልሃለሁ።››

ይህን ግዜ ረሱል ልባቸው በሀሴት ተሞላ። እንዴት አይደሰቱ !!? ምንም እንኳን ወንድ ልጅ ባይበረክትላቸውም በጀነት ከውሰርን ተዘጋጅቶላቸዋል።

ነቢ ሰዐወ በስማቸው ሚጠራ ወንድ ልጅ ባይኖራቸውም ከ1400 አመታት በላይ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ቀን ማታ በብዙ ቢልየን ሰለዋት ሚያወርድ ኡመት ሰጥቷቸዋል።

Sefwan sheik ahmedin
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
1.9K viewsedited  03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 09:19:23 "ከእለታት አንድ ቀን አንዲት ልጅ መጣችና የሆነ ከሐራም እና ሐላል ጋር የተያያዘ ጥያቄ ጠየቀችኝ። ጥያቄውን ሳልነግራችሁ ልለፈው። «እንዲህ እንዲህ ማድረግ ሐራም ነው ወይ? ምን ታስባለህ?» አለችኝ። «ምንም ማሰብ አያሻኝም፤ ሸይኽ እገሌን ጠይቂ» አልኳት። እሷ ግን መልሳ «ይህንን ጥያቄ ካሁን በፊት ሸይኹን ጠይቀሃቸው ታውቃለህ?» አለችኝ። «መጠየቁንስ ጠይቄያቸው ነበር» አልኳት። «ምን አሉ?» አለችኝ። «ያው ‹ሐራም ነው› ነው ያሉት» አልኳት። ይህኔ «እስቲ ሌላ የምጠይቀው ዓሊም ካለህ ጠቁመኝ» ብላኝ አረፈች!

ልጂቱ ሐላል የሚያደርግላት ዓሊም እስከምታገኝ እየጠበቀች ነው ማለት ነው። «በቃ በዚህም በዚያም ብላችሁ፣ ኺላፍ ካለበትም በሆነ መልኩ አጣርታችሁ ሐላል የሚያደርግ ሰው ፈልጉልኝና የሠላም አየር ልተንፍስ» ዓይነት አቋም ነው የያዘችው። ሱብሐን አላህ! «ላ ተስአሉ ዓን አሽያአ ኢን ቱብደለኩም ተሱእኩም - መልሱ ቢነገራችሁ የምትከፉበትን ጥያቄ አትጠይቁ» ይለናል የቁርኣን አንቀጹ። ምንም ዓይነት መልስ ቢሰጠን ለመቀበል አዕምሯዊ ዝግጁነት ሳይኖረን መጀመሪያውኑ ለምን እንጠይቃለን? ስሜታችንን የሚያጸድቅልን ዓሊም ፍለጋ ለምን እንዳክራለን? ፈትዋ የምንጠይቀውኮ አንድን ነገር ሐራም ወይ ሐላል ለማድረግ መሆን የለበትም። ሐራም ወይ ሐላል መሆኑን ለማወቅ ነው መጠየቅ ያለብን።"

ኡስታዝ ኑዕማን አሊ
https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
2.2K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 09:17:56 ሌባው እኔው ነኝ
⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡

ተራኪው እንዲህ ይላል...

" መጥረብያዬን አጣሁት ፣ ጎረቤቴ ሰርቆኛል ብዬም ተጠራጠርኩ ። በድብቅ እሱን መከታተልም ጀመርኩ ። አካሄዱ ሁሉ የሌባ ነው ። ሊያውም የመጥረብያ ሌባ። አነጋገሩ ሁሉ የሌባ ነው ። የመጥረብያ ሌባ ። እንቅስቃሴዎቹ ፣ የእጁጆቹ አነሳስ አንድም ሰው ከሱ ውጪ መጥረብያዬን እንዳሰረቀ ያስረዳሉ ።

ያቺን ለሊት በንዴት እንዴት እንቅልፍ ይውሰደኝ። እንዴት ልይዘው እንደምችል ሳስብ ሳሰላስል አደርኩ ። ይሁንና ጠዋት ሲነጋ መጥረብያዬን አገኘሁት ። ትንሹ ልጄ ገለባ ከምሮበት ተደብቆ ነበር ።

ጎረቤቴን በሚቀጥለው ቀን አየሁት ። ምንም አይነት የመጥረብያ ሌባ ምልክት አላየሁበትም ። አካሄዱም ፣ አነጋገሩም ፣ የእጆቹም እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ የነፃ ሰው ናቸው ።

ከዚያ ግን የደረስኩበት ነገር ሌባው እኔ መሆኔን ነው ። ከጎረቤቴ አማናውን ሰረቅሁት ። ነፃነቱን ቀማሁት ። ንፁህን ሰው በመጠርጠር ከዕድሜዬ አንዲትን ሙሉ ለሊት በክፋት በማሳለፍ ሰረቅሁ "

#Moral of the ቂሳ ፡- የነገሮችን ዕውነታ ምንረዳው በአቅላችን መሆን አለበት። ስሜት ምናስብበት መሳርያ አይደለም !


https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
1.8K viewsedited  06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 05:53:33 ጎህ ቀደደ። የሱብሒ ሰላት በነቢያችን ሰዐወ ኢማምነት ተሰገደ...ልክ ረሱል ሰዐወ ሲያሰላምቱ ከደጅ በኩል ከፍ ባለ ድምፅ፦ «አዋጅ!!! አቡል ዓስን በኔ ከለላ አስገብቼዋለሁ....» የሚል ጥሪ መስጅዱን አስተጋባ።

«ሰዎች የሰማሁትን ሰማችሁ...?» በማለት ረሱል ሰዐወ ጠየቁ።
«አዎን አንቱ ያላህ መልዕክተኛ ሰምተናል» የሰሀቦቹ ምላሽ ነበር።

ከወደኋላ በኩል ዘይነብ ንግግሯን ቀጠለች፦ «አንቱ ያላህ መልዕክተኛ! አቡል ዓስ የአክስቴ ልጅ ከመሆኑም ባሻገር የልጆቼ አባት ነው፤ ከለላዬን ሰጥቼዋለሁ»

ነቢያችን ቁጭ ካሉበት ብድግ አሉ፤ ከሰሓባዎች ፊትም ቆሙ፦ «ሰዎች ሆይ! ይህ ሰው ዝምድናው አላታለለኝም። አወራኝ፣ እውነትም ነገረኝ። ቃል ገባልኝ፤ ቃሉንም ሞላልኝ።

ፍቃዳችሁ ከሆነ ንብረቱን መልሳችሁለት እሱንም ብትለቁት እኔ እደሰታለሁ፤ ግና እንቢ ካላችሁ ያሻችሁን አድርጉ። አልወቅሳችሁም፣ ሀቁ የናንተ ነው።» ብለው ንግግር አደረጉ።

«አንቱን ካስደሰተማ ንብረቱን እንሰጠዋለን፤ እንለቀዋለንም።» በማለት ታዛዥነታቸውን አስመሰከሩ።

ረሱልም ሰዐወ «ዘይነብ! ከለላ የሰጠሽውን ሰው ከለላ ሰጥተናል።» ብለው ሸኟት። ገና ቤቷ ከመግባቷ በሯ ተንኳኳ፤ ረሱል ነበሩ፦ «ልጄ! ጥሩ አስተናግጂው። የልጆችሽ አባት ነው፤ የአክስትሽም ልጅ ነው። ነገር ግን እንዳትቀራረቡ እስኪሰልም እሱ ላንቺ እርም ነው» ብለው መከሯት።

ያለ ምንም ማስተባበያ «እሺ የአላህ መልዕክተኛ» ብላ መለሰችላቸው። በሩ ተዘጋ፤ ወደ አቡል ዓስ ዞር ብላ፦ «መለያየትን እንዲህ እንደቀላል ተመለከትከውን...? ምናለ ብትሰልም» በማለት ታግባባው ጀመር።

«በፍፁም» የአቡል ዓስ ምላሽ ነበር።

አቡል ዓስ ንብረቱ ተመልሶለት ወደ መካ ተመለሰ። ልክ ከተማዋን እንደገባ ሰዎችን ሰብስቦ፦ «ሰዎች ሆይ! ይኸው ንብረቶቻችሁ።እኔ ጋር የቀረ ንብረት አላችሁ? » በማለት ጠየቀ።

«በመልካም ተመንዳ፤ ቃልህን ሞልተኻል።» ብለው መለሱለት።

እዚያው መሃላቸው ቁሞ፦ «አሽሀዱ አላ ኢላሃ ኢለላህ....» በማለት እስልምናን በይፋ ተቀበለ።

ጉዞ ወደ ነቢዩ ሰዐወ መገኛ መዲና....

ሌሊት ላይ ከመዲና ደረሰ።
«ያረሱለላህ! ትናንት ከለላዎን ሰጡኝ፤ እኔም ዛሬ ከልቤ እስልምናን ተቀብዬ መጥቻለሁ።» አላቸው።

ንግግሩን ቀጥለ፦ «አንቱ ያላህ መልዕክተኛ! ዘይነብን ዳግም ልቆራኛት ይፈቅዱልኛል...?»

እጁን ያዝ አደረጉት'ና፦ «ና ተከተለኝ።» ብለው ከዘይነብ ደጃፍ አደረሱት።
በሌሊት በሯ ተንኳኳ፤ ስትከፍተው አባትዋ እና ተናፋቂ ባሏ በር ላይ ናቸው።

«የአክስትሽ ልጅ ዳግም ካንች ጋር እንዳቆራኘው ጠይቆኛል። ፍቃደኛ ነሽ?» በማለት አባቷ ጠየቋት።

የደስታ ፊቷ ቀልቶ ምትለው ቢጠፋት ፈገግ አለች። ዳግም ከስድስት አመታት በኋላ ፍቅር ፍቅሯን አቀፈች።

አንድ የፍቅር ህዳሴ አመት ተቆጠረ። አቡል ዓስ ፅጌረዳዋን አሽትቶ ሳይጠግብ ሞት ነጠቀው።

ረሱል ሰዐወ ሲያፅናኑትም፦ «ያ ረሱለላህ! ወላሂ እኔ ያለሷ ዱንያን አልችልም» እያለ እዬዬ ይል ነበር።

አንድ ሙሉ የሀዘን አመትን ካሳለፈ በኋላ አቡል ዓስ ፍቅሩን ተከትሎ ወዳሸለበችበት እሱም አሸለበ።

ፍቅርም መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ተመለሰ!

Sefwan Ahmedin
_________

ምንጭ፦
صور من حياة الصحابة عبد الرحمن رأفت الباشا
2.4K views02:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 05:53:33 አቡል ዓስ ወደ ረሱላችን ሰዐወ ሂዶ፦ «ትልቋን ልጅህን ዘይነብን እንድትድረኝ እጠይቅሀለሁ» አላቸው።
#አደብ

እሳቸውም፦ «ፍቃዷን ሳላረጋግጥ አልድርህም» አሉት።
#ህግ

ረሱላችን ሰዐወ ወደ ልጃቸው ዘይነብ ሂደው፦ «የአክስትሽ ልጅ እኔ ዘንድ መጥቶ አንችን ለምኖኛል፤ ባልሽ እንዲሆን ትፈቅጃለሽ ወይ?» ብለው ጠየቋት።አፍራ ፈገግ በማለት አጎነበሰች።
#ሀያእ

ጋብቻቸው ተፈፅሞ አስደናቂውን የትዳራቸውን ህይወት ሊጀምሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ።
#ስኬት

አባቷ በነብይነት ሲበሰር ዕውነተኝነቱን ያመነችው ልጅት ዘይነብ ባሏ ለንግድ ጉዞ በሄደበት እስልምናን ተበብላ ጠበቀችው።
#ዕምነት

ልክ ከጉዞው ተመልሶ እቤቱ ሲገባ፦ «ትልቅ የምስራች ይዠልሀለሁ» ስትለው ምንም ሳይል ትቷት ከቤት ወጣ።
#አክባሪነት

ልጅት ዘይነብ ደንግጣ ባሏን እየተከተለች በመውጣት፦ «አባቴ በነብይነት ተልኳል፤ እኔም ሰልሚያለሁ» ስትለው
«ታድያ መጀመሪያውኑ አትነግሪኝም ነበር» ብሎ መለሰላት።

ልጅት ዘይነብም፦ «አባቴን ፍፁም አላስተባብልም፤ እሱም አይዋሽም። እኔ ብቻም ሳልሆን እናቴ እና እህቶቼም ጭምር ነን የሰለምነው» ብላ ንግግሯን ቀጠለች።
#አቋም

«የአጎቴ ልጅ ዐሊይ ሰልሟል፤ የአጎትህ ልጅ ዑስማንም እንደዝያው...ጓደኛህ አቡ በክርም ከኛው ነው» በማለት አብራራችለት።

እሱም፦ «እኔ እንደሆን ሚስቱን ለማስደሰት ሲል የጎሳውን ሀይማኖት ትቶ ሰለመ ተብሎ እንዲወራብኝ አልሻም። ይቅርታ አድርጊልኝ'ና አባትሽም ቢሆን ቀጣፊ እንዳልሆኑ አውቃለሁ» አላት።
#የሰከነ_ውይይት

እሷም፦ « እኔ ይቅር ካላልኩህ ማን ይልሀል?...ነገር ግን ዕውነት እስኪገለፅልህ ድረስ እረዳኻለሁ።» አለችው።
#መናበብ

(ለ20 አመታት ያህል ቃሏን ጠብቃ አብራው ቆየች።)

ዘይነብ በእስልምናዋ፤ ባሏ በክህደቱ ላይ ፀንተው ትዳራቸውን ባሟሟቁበት ግዜ ከመካ ወደ መዲና የሚደረገው የስደት ጉዞ ተደነገገ።

ልጅት ዘይነብም ወደ አባቷ ዘንድ ሂዳ፦ «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! እዚሁ ከባሌ ጋር እንድቀር ይፈቅዱልኛል» ስትል ጠየቀቻቸው።
#ፍቅር

ፈቀዱላትም።
#እዝነት

ሙስሊሞች ከመካ ወደ መዲና ተሰደው ልጅት ዘይነብ እዚሁ መካ ላይ ከባሏ ጋር ቀረች። ከግዜያት በኋላ ሙሀመድን ሰዐወ እና የመካ መሳፍንቶችን በአንድ የጦር ሜዳ ላይ የምታፋጥጠው የበድር ዘመቻ ቀጠሮዋ ቀረበ።

የልጅት ዘይነብ ባለቤት አቡል ዐስ'ም ከመካ መሳፍንቶች ተርታ ተሰልፎ የሚስቱን አባት ሊዋጋ ወሰነ።

ባለቤቷ አባቷን ሊዋጋ ሄደ፤ እሷ ቤቷ ቁጭ ብላ እያለቀሰች፦ «አላህ ሆይ! የድል ጮራህ ፈንጥቃ ልጆቼን የቲም እንዳታደርግብኝ ስፈራ፤ አባቴንም እንዳላጣው ሰጋሁ» ስትል ትውላለች።
#ምርጫ_አልባ

የበድር ጦርነት ዘመቻ ተጀመረ፤ በድር የድል ዙፋኗን ለሙሀመድ ሰዐወ ሸልማ፤ የመካ መሳፍንቶችን አስክሬን ከጦርነት አውድማው በመበተን የተቀሩትን መሳፍንት በሙሀመድ ሰዐወ ምርኮኛ አድርጋ የጦር ድንኳኗን አፈረሰች።

የጦርነት ዜናው የመካ መንደሮችን አጥለቀለቀ፤ ልጅት ዘይነብ ዜናውን ለመስማት ወጣ ብላ፦ «አባቴ እንዴት ሆነ...?» ስትል ትጠይቃለች። «ድልን ተጎናፅፏል» ስትባል ሱጁድ ትወርዳለች።

ከሱጁዷ ብድግ ብላ፦«ባለቤቴስ እንዴት ሆነ...?» ብላ ስትጠይቅ «የሙሀመድ ምርኮኛ ሁኗል» የሚል መርዶ ትሰማለች።

«እንግዲህ ባለቤቴን የምቤዥበት መስዋዕተ-ምትክ ወደ መዲና እልካለሁ» ብላ ትወስናለች።
#ብልሀት

ውድ ባለቤቷን ከተማረከበት ነፃ ለማስወጣት የምትቤዥለትን ውድ እቃዎች ስታሰላስል ከእናቷ ከዲጃ በኩል የተሰጣትን የአንገት ሀብል ብቁ ሆኖ ታያት'ና ወሰነችበት።

የባሏን መቤዥያ ይዞ ወደ መዲና የሄደው የባሏ ወንድም ልክ መዲና ሲገባ ሙሀመድን ሰዐወ ቁጭ ብለው መቤዥያዎችን እየተረከቡ ምርኮኞችን ሲለቁ ደረሰ።

እሱም ከዘይነብ የተረከበውን የባለቤቷን መቤዥያ ከሙሀመድ ሰዐወ ዘንድ ከተደረደሩት መቤዥያዎች መሀል ቁጭ አደረገ።

ሙሀመድም ሰዐወ መቤዥያዎችን ሲቆጥሩ በመሀል የድሮ የወጣትነት የፍቅር ዘመናቸውን የሚያስታውሳቸውን አንድ የአንገት ሀብል ተመለከቱ። ውድ ሟች ሚስታቸው ትዝ አለቻቸው።

በለሰለሰ ድምፅ፦ «ይህ የማን ነው...?» ሲሉ ጠየቁ።

«ይህ የአቡል ዓስ መቤዥያ(መስዋዕተ-ምትክ) ነው።» ተብሎ ተነገራቸው።
«ይህ የከዲጃ ሀብል ነበር» ብለው እቀረቀሩ።

አንገታቸው ዝቅ አለ፣ ፍቅርት ከዲጃ ትዝታዎቿ ከመቃብር በላይ ዳግም ህያው ሆነው የነቢዩን ጉንጮች በእንባ አራሳቸው።

ፊታቸውን ጠራርገው ከዙርያዎቻቸው የተሰበሰቡትን ሰሀቦች እየተመለከቱ፦ «ይህ ሰው በዝምድና ተቆራኝተነዋል፤ ፍቃዳችሁ ከሆነ እንፍታው...? ለዘይነብም ሀብሏን እንመልስላት...?» በማለት ጠየቁ።
#መተናነስ

«አዎ ይመለስ አንቱ ያላህ መልዕክተኛ» የሰሀባዎች ምላሽ ነበር።
#ስነስርአት

መልዕክተኛው ሰዐወ አቡል ዓስን አስጠሩት፦ «ይህን ሀብል ለዘይነብ መልሰህ ስጣት "በከዲጃ ሀብል አትጫወችብኝ" በላትም» ብለው ለቀቁት።

ዳግም ጠሩት፦ «አንተ አቡል ዓስ! አንዴ ለብቻህ ላናግርህ...?» ወደ ዳር ወሰዱት.....

«ይኸውልህ አቡል ዓስ! አላህ በካፊሮች እና በሙስሊሞች መካከል እንድለያይ አዞኛል። ስትመለስ ልጄን ትልክልኝ...?» በማለት ጠየቁት።

«እሺ እልካለሁ» አለ።
#ወንድነት

ጉዞውን ቀጠለ...፤ በመዲና እና በመካ መካከል ያሉትን በረሃዎች አቋርጦ የመካ ከተማ መዳራሻዎች ላይ ሲቀረብ ሚስቱ ዘይነብ ልትቀበለው ወጥታ አገኛት።

ገና ሲገናኙ፦«ልለይሽ ነው» ብሎ አስደነገጣት።
«ወዴት ነው የምትለየኝ...?» ድንጋጤ ፊቷ ላይ እየተነበበ።

«እኔ አይደለሁም የምለይሽ፤ አንቺ ነሽ የምትለዪኝ። ወደ አባትሽ እልክሻለሁ» አላት።
#ቃል_ኪዳን

ድንጋጤዋ እየጨመረ፦ «ለምን...?» አለችው።
«እንድንለያይ ተወስኗል'ና ወደ አባትሽ ትመለሻለሽ» አላት።

«እባክህ ስለም'ና አብረን እንሂድ» ስትል ተማፀነችው።
«በፍፁም» የሱ ምላሽ ነበር።

ሁለት ልጆቿን ይዛ የአባቷ መገኛ ወደሆነችው መዲና ተመመች። ልክ መዲና ገብታ ከአባቷ ጓዳ ከማረፏ ነበር የትዳር ጥያቄዎች ይጎርፉላት የጀመረው።

ምንም እንኳን ለ 6 ተከታታይ አመታት የትዳር ጥያቄዎች ከትላልቅ ሰሀባዎች ቢቀርቡላትም የባሏን የ"ይመለሳል" ተስፋ የሰነቀችው ዘይነብ በብቸኝነቷ ፀንታ ጠበቀች።

ከ 6 አመታት በኋላ ከመካ ወደ ሻም ከሚሄዱት የሲራራ ነጋዴዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን አቡል ዓስ ጉዞ ጀመረ።

በጉዞ ላይ ሳሉ ከውስን ሰሀባዎች ጋር መዲና ላይ ፊት ለፊት ተገጣጠሙ። ንብረታቸው መካ ላይ ተወርሶ የግር ሳት የሆነባቸው ሰሀባዎችም ያገኙትን እድል ተጠቅመው የጫኑትን ግመሎች ማረኩባቸው።

ሰዓቱ ከሱብሒ በፊት ነው፣ የነቢዩ ሰዐወ ከተማ ነዋሪያን ቤታቸው ገብተው ከተማዋ ፀጥ...ብላለች። በዚህ መሀል አቡል ዓስ የዘይነብን ቤት አጠያይቆ በውድቅት ሌሊት በሯን አንኳካ።

ልክ በሯን ከፍታ እሱ መሆኑን ስታረጋግጥ፦ «ሰልመህ ነው የመጣኸው...?» በማለት ጠየቀችው።
#ተስፋ

«ኧረ አምልጬ ነው የመጣሁት...» ብሎ መለሰላት።
ጥያቄዋን ይቀበላት ዘንድ በስስት እያየችው፦ «እና ትሰልማለህ...?» አለችው።

«በፍፁም...» ብሎ ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ መለሰላት።
በዲን ማስገደድ የለም'ና «እንግዲያውስ አብሽር እንኳን ደህና መጣህ የልጆቼ አባት፣ የአክስቴ ልጅ....» ብላ አስገባችው።
#ውለታ
2.0K views02:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 19:45:00 አስደንጋጩ ፍጻሜ አላህ ይጠብቀን !

ከታሪካቸው በርግጥም ትምህርት አለ
በዚህ በሽታ የተፈተነ ሰው ታሪክ እነሆ!
መንሱር ኢብን ዑባድ የተሰኙ ሊቅ እንዲህ ይላሉ፦
“አንድ ወንጀል የሚያበዛ ጓደኛ ነበረኝ፤ ከዚያም ወደ አላህ ተመለሰ። የሌሊት ሶላትና ሌሎች ዒባዳዎችን በብዛት ሲፈፅም እመለከተዋለሁ። አንድ ቀን ከዓይኔ ተሰወረ። እንደታመመ ሰማሁ። ፊቱ ጠቁሯል። ዓይኖቹ ደም መስለዋል፤ ከንፈሮቹ አብጠዋል። በፍርሃት ተሞልቼ፦ “ወንድሜ ሆይ! ላ ኢላሀ ኢልለላህ የሚለውን ቃል አብዛ” አልኩት። ዐይኑን ከፍቶ ወይ እኔ ተመለከተና ራሱን ሳተ። ሸሃደተይን በደጋገምኩለት ቁጥር ዐይኑን ከፍቶ ይመለከተኝና ራሱን ይስታል። በመጨረሻም እንዲህ አለኝ፦ “በእኔና በሸሃዳ መካከል ግርዶሽ ተደርጓል።”
“ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ! ለምን?!! ሶላቱ፣ የሌሊት ሰዓታት አምልኮውና ቁርአኑ የት ሄደ?” አልኩት።
ቀጠለና፦
“ብቻዬን በምሆንበት ጊዜ መጋረጃዬን ጣል አደርጋለሁ፤ ኸምር እጠጣለሁ፤ ለሞት ያደረሰኝ ከባድ በሽታ ላይ እስከምወድቅ ድረስ በዚሁ ሁኔታ ቀጠልኩ። ልጄን “ቁርአን አቀብይኝ” አልኳት።
“ጌታዬ ሆይ! ከዚህ በሽታዬ አድነኝና ወደ ወንጀል ፈፅሞ አልመለስም።” ብዬ ተማፀንኩት። አላህ ከበሽታው አዳነኝ። ጤናዬ ሲመለስልኝ ወደ ነበርኩበት ወንጀል
185
ተመለስኩ። ከጌታዬ ጋር የገባሁትን ቃልኪዳን ካድኩ። በበሽታ አላህ እስኪፈትነኝ ድረስ በዚያው ሁኔታ ቀጠልኩ። በበሽታው ከባድነት ለሞት ተቃረብኩ። በመጀመሪያው ሀመሜ እንዳደረግኩት አደረግኩ፤ አላህንም ተማፀንኩ፦ “ጌታዬ ሆይ! ከበሽታዬ አድነኝ፤ ካለሁበት መከራ ገላግለኝ፡” አላህ ካለሁበት መከራ ገላገለኝ። ጤናዬ ከተመለሰልኝ በኋላ ወደነበርኩበት ሁኔታ ተመለስኩ። በመጨረሻም በዚህ በሽታ ወደቅኩ። እንደምትመለከተኝ ቤተሰቦቼ በቤቴ መሃል ላይ እንዲያስተኙኝ አደረግኩ። ቁርአን ለማንበብ እንዲያቀብሉኝ ጠየቅኳቸው። አንዲትንም ፊደል መለየት አልቻልኩም። ይህኔ አላህ ከባድ ቁጣን እንደተቆጣብኝ አወቅኩ። ዐይኔን ወደ ሰማይ አንስቼ፦
“ጌታዬ ሆይ! አንተ የሰማያትና የምድር ኃያል ካለሁበት መከራ ገላግለኝ።” አልኩ። ከዚያም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፦
ያመመህ ጊዜ ከወንጀል ራቅህ ጤናህ ሲመለስ ቀጠለ ኃጢአትህ
ከስንት መከራ ጌታህ ገላገለህ?! ከስንትስ ፈተና በሰላም አወጣህ?
ስንቴ ቃል ገብተህ ፈረሰ ቃልህ?! ውለታን ሁሉ ጭራሽ ዘንግተህ
አትፈራም እንዴ ቢመጣ ሞትህ? በወንጀል ብዛት እንዲህ ተክበህ?!
መንሱር እንዲህ ይላሉ፦
“በአላህ እምላለሁ - ከርሱ ዘንድ ዐይኔ እንባ እያዘነበ ወጣሁ። በሩ ላይ እንደደረስኩ እንደሞተ ተነገረኝ።”
ተመልከት! አላህ ይጠብቅህና - ምኞትን ማስረዘም እንዴት መጨረሻን እንዳበላሸ። ከዚህ ታሪክ ላይ መጨመር አያስፈልገም። ዓይኑ ደካማ የሆነ ሰው እንኳ ማየት በሚያስችለው ያህል ቃላት በታሪኩ መስመር ላይ ጎልተው ይታያሉ።
በሌሎች መመከር ያልቻለ፤ ሌሎች በርሱ ይመከራሉ።
------
አላህ እውነተኛ ተውበትን ይወፍቀን ያረብ !
ፍኖተ-ጀነት በሚል በኡስታዝ በድሩ ሁሴን ከተተረጎመው የዶክተር አቡሻዲ መጽሃፍ የተወሰደ

https://t.me/Golden_Speech
https://t.me/Golden_Speech
1.9K viewsedited  16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ