2022-07-14 08:14:34
የረበና ሰላም በናንተ ላይ ይሁን አሁበኩም ፊላህ።
ትዳር ወይስ ስራ...
በሰው ሃገር ባይዋተር የሆንሺው ውድ እሄቴ ስለ አንቺ ሳስብ የማወራው የምፀፈው ሁሉም ይደባለቅብኛል። ብዙ እህቶች የእድሜ ገሚሳቸውን በአረብ ሃገር ተቀጥረው በማገልገል ነው የሚጨርሱት። ስራሽን ሃሳብሽን ሳላደንቅ የማላልፍበት መንገድ የለኝም አለማድነቅ አለማመስገን ንፉግነት ነውና። አዎን ከዛም አልፎ መታወር ነውና።....
ከርእሳችን ሳልወጣ ወደ ጥያቄው መልስ ይሆናል ያልነውን ሃሳብ እናጋራ ይህ ሃሳብ የኔ ብቻም አይደለም የአብዛህኞቹ መልስ ይህ ነበር። ታግባ የሚል ነው። እኔም ከዚህ ውስጥ ነኝ። ከስራ ይልቅ ትዳርን ነው ለሴት ልጅ የምመርጠው።
እድሜሽን በስራ ገፍተሽ አሁንም በስራ መወጠርሽ ከምን የመጣ ነው። ከስራ ይልቅ ትዳር መፈለጉ ላይ ትኩረት አድርጊ ጥሩ ወንድ የለም ታማኝ የለም በሚል ፈሊጥ ህይወትሽን በእንቶ ፈንቶ ሃሳብ ራስሽን አትግደይ። አንቺ ከአላህ ጋር እስከሆንሽ ድረስ ይህ ነገር አያሳስብሽም የኢማን ልቅናሽን ዘለበትሽን እንዳትለቂ የአላህ ፍቅርም በልብሽ ይንገስ ምን አልባት የሰው ፍቅር ቢመጣ ልብሽ አይናወጥምና። ልብሽን የአላህ ፍቅር ከተቆጣጠረው ስለ ሰው ፍቅር አላህ ይሆንልሻል። ስለ ሰው ፍቅርም ልክ እና ገደብ ያበጅልሻል ያሳይሻል።
ትዳር በመቅረቱም አትብሰይሰይ የአንቺ ያለው ይመጣል። ከሃገር ከገባሽ ቡሃላ ወደ ትዳርሽ ይሁን ዝንባሌሽ። ግዜ ህይወት ነው። አንቺ የቀናት ጥርቅም ነሽ ከትዳርሽ እርቀሽ ስራ ስራ ስትይ እድሜሽ ላይመለስ እያከተመ መሆኑን እሰቢበት እናም አግቢ። ወደ ትዳር ለመግባት ብዙ አመት የሰራሻቸው ገንዘቦችም አይከስሩብሽም ለሴት ልጅ ወደ ትዳር ለመግባት ወጪ ወይም ኢንቨስት አያስፈልግም እና ይህን እድል ለማን ታሳልፊያለሽ።
ወደ ስራው ከገባሽ ቡሃላስ ብትከስሪስ ተስፋ ቆርጠሽ ተናደሽ የማይሆን ወንድ ላይ ትዳሩን ልየው ብለሽ ልትገቢ ትችያለሽ እድሜሽም ሲሄድ ለመውለድ ብለሽ የማይሆ ጥምረት ታደርጊያለሽ። ወደትዳር ስትገቢ ምርጫሽን አስተካክይ ቤተሰብ የወደድልሽን በመልካም የሚያኖርሽን ስራ የማይንቀውን ትጉውን አብራችሁ መለወጥ የምትችይውን አግቢ። ትዳርሽን በመልክ እና በኡዝታዝ በሚል ፌዝ ሰዎች በመፈለግ እንዳታበላሺ መልክ ያለውም ካሰኘሽ ስራ የሚሰራ የማይንቅ አንቺን የሚያኖር ይሁን። ኡዝታዝም ካልሽ እየከሰበ የሚያኖሽ በኢልሙ እራሱንም የሚመክር የሚተገብር አይነት ይሁን። አለበለዚያ ግን ከማይሰራ ኡዝታዝ ወይም ቆንጆ የቀን ስራ የሚሰራን ምረጪ ገንዘብሽን ብሰጪው ያበዛልሻል። ልብሽን ብትሰስጪው ይንከባከብልሻል። አካልሽን ስትጪው ልጅ ይሰጥሻል። ስራ የሚሰራ ስልሽ ታዲያ ሶላቱ ላይ ኢማኑ ላይ ደካማ የሆነውን አይደለም። ወይም እየሰራ የሚቅመውንም አይደለም ለመለወጥ ጥሩ ትዳር ለመመስረት አስቦ ደፋ ቀና የሚለውን ቢሆን እንጂ በዛውም የሚወደድ ስራ ሰራሽ።...
አገር እንደገባሽ ስራ ለመጀመር የሃገርሽን ሁኔታ ወይም ፍላጎትና አቅርቦትን ስታጠኚ ገንዘብሽንም ትጨርሻለሽ ሳታውቂው በሰዎች ያልሆነ ያልወደድሺው ስራ ላይ ብትገቢ ራስሽን ነው የምትወቅሺው። ባልሽ ለሰውም ከሃገሩም ከስራውም ጋር ያስተዋውቅሻል።
ሁለት እረካኣ ስገጂ ዱኣ አድርጊ ከዛም አግቢ ነው የምንለው ወንድ ልጅ ነው ደግሞ ቤት አሳዳሪው መሪውም።
እንዳይበዛ ይበቃናል ሃሳብ መደጋገም እንዳይሆንብን አብዛሃኞቻችሁ መልካም ምርጥ ኮሜንት ሰጥታችኋል ሌሎችንም ይቀይርልን ይሆናል።
ወሰላም አለይኩም።
1.4K views05:14